Amharic Language, Literature and Folklore

Permanent URI for this collection

Browse

Recent Submissions

Now showing 1 - 20 of 469
  • Item
    ‹‹ለአሸናፊነት መገዛት›› የተሰኘው የስነልቡና መፀሀፍ ከጥሩ ትርጉም መመዘኛዎች አኳያ
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2001-06) ፍሬህይወት ረጋሳ; መሐሪ ዘመለአክ
    ትርጉም ሀገሮች የራሳቸውን ዕውቀት፣ባህል፣የስልጣኔ ደረጃቸውን እርስ በርስ የሚለዋወጡበት መንገድ ነው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ዓለም ወደ አንድ መንደር ተለውጣለች፤ ሉላዊነት ማለት ነው፡፡ ታዲያ ሰዎችም የራሳቸውን አሻራ ጥለው ለማለፍ በሚያደርጉት ትንቅንቅ ዓለምን ወደ ተሻለች የዕውቀት መንደርነት ለውጠዋታል፡፡ ከጥንት ጀምሮ ሀገሮች የርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠንከር ከሚያከናውኗቸው ስራዎች መካከል የትርጉም ስራ እንደ አንድ ጉዳይ ይነሳል፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ከጥንቱ በተሻለ ዕውቀትና የአስተሳሰብ ደረጃ፣ ትርጉሞች ከአቀባይ ቋንቋ ወደ ተቀባይ ቋንቋ ለህብረተሰቡ ይቀርባል፡፡ የትርጉም መስፋፋት አንድም ስራ በሌላም በኩል የዕውቀት ማሸጋገሪያ ድልድይ ሆኗል፡፡የዚህ ጉዳይ መነሾ ላነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ መንደርደሪያ ይሆነኝ ዘንድ ነው፡፡ ይህም ጥናት በሚያተኩርበት መፅሐፍ ላይ ያሉ ድክመቶችንና ጠንካራ ጎኖችን ከመገኛ ቋንቋው ጋር በማነፃፀር ማቅረብን ይመለከታል፡፡ በዚህም ጥናቱ የመመረቂያ ፅሁፋቸውን ለሚሰሩ ተማሪዎች እንደማጣቀሻነት እንዲሁም ከጥሩ ትርጉም መመዘኛ ነጥቦች አኳያ ግንዛቤን ማስጨበጥ ይሆናል፡፡
  • Item
    የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ፆታተኮር ተዛምዶ፤ በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-06) በለጠ ሕሉፍ; ፕሮፌሰር ጌታሁን አማረ
    የጥናቱ ዋና ዓላማ የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ያላቸውን ተዛምዶ ከጾታ አንጻር መፈተሽ ነበር፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም ጥናቱ በተለዋዋጮቹ መካከል ያለውን ዝምድና የማሳየት አላማ ስላለው የተከተለው ዲዛይን (ስልት) ተዛምዷዊ ነበር፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም በደሴ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ደረጃ የሁለተኛው ሳይክል ካላቸው ትምህርትቤቶች መካከል በመምህር አካለወልድ የነበሩ ከ11ኛ G እስከ L ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ (107 ወንዶችና 69 ሴቶች በአጠቃላይ 176) ተማሪዎች በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎቹ፤ የስሜታዊ ብልህነት መጠይቅና የመጻፍ ተነሳሽነት መጠይቅ እንዲሞሉ እንዲሁም የመጻፍ ችሎታን ለመፈተሽ የሚያገለግል የመጻፊያ ርእስ በመስጠት እንዲጽፉ በማድረግ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተገኙት መረጃዎችም በገላጭ ስታትስቲክስ (በአማካይ ውጤትና በመደበኛ ልይይት)፣ የርስበርስና የጠራ ዝምድናቸውን ለመለየት በፒርሰን የተዛምዶ መለኪያ እንዲሁም በከፊል የተዛምዶ መፈተሻ ዘዴ ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤቶች እንዳመላከቱትም በስሜታዊ ብልህነት፣ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታተኮር ዝምድና ታይቷል፡፡ በሌላ በኩል የስሜታዊ ብልህነት ዘርፎች ከመጻፍ ችሎታ ጋር ተዛምዷቸው ከጾታ አንጻር ልዩነት አላቸው፡፡ እንዲሁም የስሜታዊ ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ከተነሳሽነት አንጻር ልዩነት አሳይተዋል፡፡ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታን መሰረት አድርጎ ልዩነት አልታየም፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም ጾታ ጣልቃገብ ሲሆን በተላውጦዎቹ መካከል ልዩነት ያሳያል ወደሚልና የስሜት ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ተዛምዶ የሚኖራቸው የመጻፍ ተነሳሽነት ሲኖር ነው ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም አስተያየቶች ተጠቁመዋል፤ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡
  • Item
    ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
    (Addis Ababa University, 2024-12) ሕይወት በየነ; ዘላለም መሠረት(ዶ/ር)
    ይኽ ጥናት ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በሚል የተጠና ነው፡፡የጥናቱ መረጃዎች የተሰበሰቡት በዋናነት በምልከታ፣የቅዱሳት ሥዕላት ባለሙያ ጋራ በቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ቅዱሳት ሥዕላት በተመለከተ የተጻፉ ጋዜጣ፣መጽሔት እና መጻሕፍትን በማንበብ፣ የሥዕል ዐውደ ርእይና ዐውደ ጥናት ላይ በመሳተፍ፣በየመደብሩ የሥዕላት መሸጫ ቦታዎች ላይ ምልከታ በማድረግ እንዲኹም በየአብያተ ክርስቲያኑ የሚገኙትን ቅዱሳት ሥዕላትን በመመልከት ነው፡፡በነዚኽ ዘዴዎች የተሰበሰቡት መረጃዎች ጥናቱ ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ያለውን አገልግሎትና የአሣሣል ሥርዐት ለማሳየት ዐላማ አድርጎ በመነሣቱ የአሣሣል ሥርዐቱን ለማሳየት ተግባራዊ እና ሥነ-ልቡናዊ ንድፈ ሐሳብን ተጠቅሟል፡፡በተግባራዊ እና ሥነ-ልቡናዊ ንድፈ ሐሳብ አቅጣጫ መሠረትም በገላጭ ምርምር ስልት መረጃዎች ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ቅዱሳት ሥዕላት የሚያስገኙት ጥቅም፣የቅዱሳት ሥዕላት አሣሣል ታሪካዊ አመጣጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የኾነ ትእዛዝ ያለው መኾኑንና ከጥንት ጀምሮ ሥዕሎቹ ትውፊትን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጁ ሲኾን አኹን ባለንበት ዘመን ግን ትውፊትን ያልጠበቁ እና የእምነቱን አስተምህሮ የማይገልጹ ቅዱሳት ሥዕላት መኖራቸው በጥናቱ ላይ ተረጋግጧል፡፡ቅዱሳት ሥዕላት ከመሣላቸው በፊት ከሠዓሊው የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች አሉ፡፡እነሱም፡-ንስሓ መግባት፣ሥዕላቱ የሚዘጋጁት በእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ጸሎት ማድረግ፣ሥዕሉን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች ማስባረክ እንደሚያስፈልግ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ሠዓሊው መሠረታዊ የኾነ የመንፈሳዊ ዕውቀት ያለው፣ሥዕሎችን የመመልከት፣ሥዓሎቹ የሚሣሉት ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ መነሻ በማድረግ በመኾኑ ገድላትን ስንክሳርን የማንበብ ልምድ ያለው መኾን እንዳለበት በዚኽ ጥናት ተረጋግጧል፡፡ኾኖም ግን አኹን ባለንበት ዘመን ይኽ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደማይዘጋጅ እና የቤተ-ክርስቲያን አሠሪ ኮሚቴዎችም ሥዕሎችን እንዲሣሉ ማድረጋቸውን እንጂ ትውፊቱን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላት እንዲዘጋጁ እንደማያደርጉ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ከሥዕሎቹ ጭብጥ ጋራ የማይዛመዱ ቅዱሳት ሥዕላትንም በስህተት የሚጠሩበት ሥያሜ እና ታሪካቸው የሚለያዩ መኾናቸውን በዚኽ ጥናት ተለይቷል፡፡ይኸውም አኹን ባለንበት ዘመን ኪዳነ ምሕረት ተብለው የሚታዩት ሥዕሎች የማርያምን ንግሥና ስትቀበል የግብጽ የመገለጧ ማርያም የሚያሳዩ ናቸው እንጂ ቃልኪዳን ስትቀበል የሚያመለክት አለመኾኑንና ትክክለኛውን የኪዳነ ምሕረት ምሥል የትኛው እንደኾነ ተለይቷል፡፡በጥንት ዘመን የሥዕል ትምህርት የቀድሞ አባቶቻችን ከፍተኛ የኾነ ትምህርተ ክርስትና የነበራቸው በመኾኑ የሚሥሏቸው ሥዕሎቹ ከትምህርተ ክርስትና ጋራ እንደማይጋጩ vi በአኹኑ ዘመን ግን የሚታዩት ሥዕሎች መሠረታዊ የኾኑ የእምነቱን አስተምህሮ የማይገልጹ እንደኾኑ ተረጋግጧል፡፡ቅዱሳት ሥዕላት በተመለከተ ትምህርት እየተሠጠ እንዳልኾነ፣በየቤተ ክርስቲያናቱ ሰንበት ትምህርት ቤትና በየዐውደ ምሕረቱ ላይ የተሰበኩ ትምህርት አለመኖሩን፣በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ የተጻፉ መጻሕፍት ጥቂት መኾናቸውን በተጨማሪም በመንፈሳዊያት ዩኒቨርስቲዎች ሥዕል ራሱን ችሎ ትምህርት እየተሠጠ አለመኾኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡የሥዕል ትምህርት ቤቶች አኹን እያስተማሩ ያሉት በማኅበረ ቅዱሳን ሥነ-ጥበብ ክፍል፣በሐመረ ብርሃን፣በገርጂ ማርያምና እግዚአብሔር ምስሌነ ደብረገሊላ ብዙ ሥራ እየሠሩ እንደሚገኙ ታይቷል
  • Item
    በመማሪያ ክፍል ውስጥ ተግባቦት የአማርኛ ግብረንግግር ዓይነቶች፣ ቅጣምባር እና ተግባር ትንተና
    (Addis Ababa University, 2024-06) አንዱዓለም ከበደ አደም; ጌታቸው እንዳላማው (ድ/ር)
    የዙህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማርኛ መማሪያ ክፍል ውስጥ ተግባቦት መምህራንና ተማሪዎች የሚጠቀሟቸውን የግብረንግግር ዓይነቶች፣ ቅጣምባር እና ተግባራትን መተንተን ነው፡፡ ይህ ጥናት በዓይነቱ በዓይነታዊ አዴ፣ የገሊጭ ምርምር ዘርፍ የሆነው አሳሽ ጥናት ነው፡፡ የጥናቱ ንድፍ ንጥል ጥናትን የተከተለ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በአመቺ የንሞና ዘዴ በተመረጠው በአማራ ብሔራዊ ክሌሊዊ መንግሥት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደብረብርሃን ከተማ ነው፡፡ የጥናቱ ተተኳሪዎችም በደብረብርሃን ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሥር የሚገኙ፣ በጠቅሊይ ንሞናዘዴ የተመረጡ ሦስት የመንግሥት ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (ኃይለማርያም ማሞ፣ ደብረኤባ እና ደብረብርሃን አጠቃላይ) እና በትምህርት ቤቶቹ የሚያስተምሩ የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራንና ተማሪዎች ናቸው፡፡ በጥናቱ ተተኳሪ የተደረጉት ሥድስት መምህራን በጠቅላይ ንሞና ዘዴ፣ ተማሪዎቻቸው ደግሞ በቀላል እጣ ንሞና እጣ በማውጣት ዘዴ ሥድስት የ10ኛ ክፍል ምድቦች ተመርጠዋል፡፡ የጥናቱ መረጃ በጥናቱ ተተኳሪ ከተደረጉ የአማርኛ መማሪያ ክፍልውስጥ ተራክቦ ሊይ በምሥሌና ዴምጽ ቀረጻ እና በኢ-ተሳትፎዊ የክፌሌ ውስጥ ምሌከታ ተሰብስቧሌ፡፡ በመረጃ ስብሰባው በአንዴ ክፌሌ ውስጥ ሦስት ጊዛ በአጠቃሊይ በሥዴስት ክፌልች አሥራስምንት ጊዛ የምሥሌና ዴምጽ ቀረጻ እና የክፌሌ ውስጥ ምሌከታ ተዯርጓሌ፡፡ ከክፌሌ ውስጥ የምሥሌና ዴምጽ ቀረጻ እና ምሌከታ የተገኘው መረጃም ወዯምዜግብ መረጃነት ተሇውጦ በተራክቦ ትንተና ዗ዳ ተተንትኗሌ፡፡ በጥናቱ መረጃ መሠረት በክፌሌ ውስጥ ተራክቦው በአጠቃሊይ በመምህራንና በተማሪዎች 4064 የንግግር ተራዎች ተወስዯዋሌ፡፡ በእነዙህ ተራዎች በአጠቃሊይ 8234 ዓረፌተንግግሮች በጥቅም ሊይ ውሇዋሌ፡፡ በጥናቱ ግኝት መሠረት በመማሪያ ክፌሌ ውስጥ መምህራንና ተማሪዎች የተጠቀሟቸው የግብረንግግር ዓይነቶች በሥዴስት ዋና ዋና ምዴቦች ማሇትም፤ እሙን መግሇጫ (3785 ዓረፌተንግግሮች ወይም 45.96%)፣ ዴርጊት ማስፇጸሚያ (3641 ዓረፌተንግግሮች ወይም 44.21%)፣ ስሜት መግሇጫ (616 ዓረፌተንግግሮች ወይም 7.48%)፣ ዕቅዴ መግሇጫ (108 ዓረፌተንግግሮች ወይም 1.31%)፣ ውሳኔ መስጫ (18 ዓረፌተንግግሮች ወይም 0.21%) እና ውህዴ (66 ዓረፌተንግግሮች ወይም 0.80%) በሚለ ተዯራጅተዋሌ፡፡ ግብራተንግግሩ የቀረቡባቸው በተዯጋጋሚ የተከሰቱ ቅጣምባሮች በሦስት ዋና ዋና ምዴቦች ማሇትም፤ የግብራተንግግር ተራክቦ ቅጣምባሮች (መክፇቻ ግብራተንግግር፣ የትምህርት ተራክቦ ግብራተንግግር እና መዜጊያ ግብራተንግግር እንዱሁም ጅመራ-ምሊሽ-ግብረመሌስ ዐዯታዊ ወይም ዘርመጥ እና ጅመራ-ምሊሽ-ጅመራ ቅጣምባሮች)፣ የግብራተንግግር ተጓዲኝ ጥንዴ ቅጣምባሮች (ሰሊምታ-ሰሊምታ፣ ጥያቄ-መሌስ እና ትዕዚዜ-መቀበሌ) እና የግብራተንግግር የአጀማመር እና የአጨራረስ ቅጣምባሮች (መጠየቅ-መጠየቅ፣ መጠየቅ-መፌቀዴ፣ ማስተኯር-መጠየቅ፣ ማስተኯር-መፌቀዴ፣ ማስተኯር-ማ዗ዜ፣ መቀበሌ-መጠየቅ፣ ማሞገስ-መፌቀዴ፣ ማሞገስ-መጠየቅ፣ መግሇጽ-መጠየቅ፣ መግሇጽ-መፌቀዴ እና መግሇጽ-መግሇጽ) በሚለ ተሇይተዋሌ፡፡ በግብራተንግግር ተራክቦ እና በተጓዲኝ ጥንዴ ቅጣምባሮች የጥያቄ-መሌስ ቅጣምባር በሰፉው ተዯጋግሞ ተከስቷሌ፡፡ በተጨማሪም በግብራተንግግር ተራክቦ ቅጣምባር የጅመራ-ምሊሽ-ግብረመሌስ የዘርመጥነት ቅጣምባር በሰፉው ተዯጋግሞ የተከሰተ ሲሆን፣ በግብራተንግግር የአጀማመር እና የአጨራረስ ቅጣምባር ዯግሞ በሰፉ ዴግግሞሽ ተከስቶ የታየው የመጠየቅ-መፌቀዴ ቅጣምባር ሆኗሌ፡፡ በመማሪያ ክፌሌ ውስጥ ግብራተንግግሩ ያሎቸው ተግባራት በርካታ ሲሆኑ፣ በንዐስ ክፌልቻቸው ሥር ተሇይተው በዜርዜር ተተንትነው ቀርበዋሌ፡፡ የተሇያዩ የግብረንግግር ዓይነቶችን፣ ቅጣምባሮችንና ተግባራትን መረዲቱ መምህራን ሇተግባቦት ብቃት ተስማሚ የማስተማር ስሌቶችን እንዱያበጁ፣ የመማር ማስተማር ውጤታማነትን ሇማጎሌበት የተማሪዎች ተሳትፍንና የተግባቦት ብቃትን ሇማዲበር የሚያስችለ ግንዚቤዎችን ሇመስጠት ይረዲሌ። ጥናቱ በግኝቶቹ ሊይ በመመሥረት የተሇያዩ አንዴምታዎችና አስተያየቶችን እንዱሁም ሇወዯፉት ጥናት የሚያነሳሱ የጥናት ጥቁምታዎችን አቅርቧሌ፡፡
  • Item
    የመጻፍ ክሂል ይዘቶች አደረጃጀት ትንተና (በዘጠነኛ እና በአስረኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ ተተኳሪነት)
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-06) በኀይሉ አባይ; ሙሉሰው አስራቴ (ዶ/ር)
    የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በዘጠነኛና በአስረኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ ያሉ የመጻፍ ክሂል ይዘቶችና የትምህርት ልምዶች የተደራጁበትን መንገድ መፈተሸ ነው፡፡ ለዚህም ጥናቱ አይነታዊ ምርምርን ተግባራዊ አድርጓል፡፡ አደረጃጀቱን በተከታታይነት ስር ተደጋግመው የመጡ ይዘቶች ያላቸውን የድግግሞሽ መጠንና የድግግሞሻቸውን ተገቢነት፣ በተለጣጣቂነት ስር ከቅርብ ወደሩቅ፣ ከቀላል ወደከባድ፣ ከተጨባጭ ወደረቂቅ እና ከቀድሞ መጥ አንጻር እንዴት እንደተደራጁና ከውህደት አንጻር ደግሞ የመጻፍ ክሂል ይዘቶችና የትምህርት ልምዶች ከሌሎች ትምህርቶች ጋር መደራጀት አለመደራጀቱ ተፈትሿል፡፡ የሰነድ ፍተሻ የተነሱትን ጉዳዮች ለማጥናት በመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴነት አገልግሏል፡፡ በሰነድ ፍተሻ የተገኘው መረጃ በብዛት በአይነት በአይነት በመሰብሰቡ ለመረጃ መሰብሰቢያነት ያገለገለው የመረጃ መተንተኛ ስልት በአመዛኙ አይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ስልት ነው፡፡ ጥቂት የቁጥር መረጃዎች ስላሉ፣ ቀላል የድምርና የመቶኛ ስሌቶች በትንተናው ውስጥ ስላገለገሉ በተወሰነ ደረጃ መጠናዊ የመረጃ መተንተኛ ስልትም በጥናቱ ውስጥ አገልግሏል፡፡ በመሆኑም አተናተኑ ቅይጥ ስልትን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ ውጤትም የሚያሳየው በመጻሕፍቱ ውስጥ የተካተቱ ይዘቶችና የትምህርት ልምዶች ተከታታይነታቸውና ተለጣጣቂነታቸው በተገቢውና ንድፈሀሳቡ ላይ በሰፈሩት መልኩ እንዳልቀረቡ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ተተኳሪ ይዘቶችና የትምህርት ልምዶች ተደጋግመው የቀረቡበት መጠን በቂ እንዳልሆነና ተማሪዎችንም የመጻፍ ክሂልን ለማለማመድ ብቁ እንዳልሆኑ በትንተናው ታይቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁለቱም መጻህፍት ውስጥ የተካተቱ ይዘቶችና የትምህርት ልምዶች ከቀላል ወደከባድ፣ ከተጨባጭ ወደረቂቅና ከቀድሞ መጥ አንጻር ከመደራጀት አንጻር በከፊል ጠንካራ ጎን ያላቸው ሲሆን በከፊል ደግሞ ድክመት ታይቶባቸዋል፡፡ ከቅርብ ወደሩቅ ያላቸው አደረጃጀት ግን ጠንካራ ጎኑ እንደሚያመዝን በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም የይዘቶችና የትምህርት ልምዶች ተከታታይነትና ተለጣጣቂነት በአብዛኛው ድክመቱ እንደሚያመዝን የጥናቱ ግኝት አሳይቷል፡፡ ውህደቱን በተመለከተ ግን ጥሩ የሚባል አደረጃጀት እንዳለ የትንተናው ውጤት አመልክቷል፡፡ የመጻፍ ክሂል ትምህርት ሲደራጅ ከሌሎች የትምህርት ይዘቶች ጋርም የጎን ለጎን ግንኙነት እንዲኖራቸውና ተዋህደው እንዲደራጁ የተደረገ በመሆኑ ውህደቱ የሰመረ ነው፡፡ ከዚህ ግኝት በመነሳትም አጥኚው የመጻፍ ክሂል ይዘቶችና የትምህርት ልምዶች ሲደራጁ በበቂ መጠን ተደጋግመው እንዲደራጁ፣ ተደጋግመው የመጡ ይዘቶችም ከቀላል ወደከባድ፣ ከተጨባጭ ወደረቂቅ፣ ከቅርብ ወደሩቅ እንዲሁም አስፈላጊነታቸውን ታሳቢ በማድረግ እንዲደራጁ፣ መማሪያ መጻህፍት አዘጋጆችና አስማሚዎች በመጽሐፍ ዝግጅት ወቅት፣ መምህራንም ትምህርቱን ክፍል ውስጥ በሚያቀርቡበት ወቅት የአደረጃጀት መርሁን ታሳቢ እንዲያደርጉ የመፍትሄ ሀሳቦችን ሰንዝሯል፡፡
  • Item
    ሴትነት በተመረጡ የዘፈን ግጥሞች
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-08) ቤተሌሔም መብራቴ; ሰላማዊት መካ (ረዳት ፕሮፊሰር)
    ይህ ጥናት “ሴትነት በተመረጡ የዘፈን ግጥሞች” በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፤ዋና ዒላማውም በተጠቀሰው ዘመን ሴትነት እንዴት እንደተሳለ በእንስታዊያን የሥነ-ጽሐፍ ሂስ የይዘት ትንተና ማድረግ ነው፡፡ በንድፈ ሐሳቡ መተገጊያነት በግጥሞቹ ውስጥ የሴት አቀራረጽ፣ ውስጣዊ እና ውጫዊ (አካላዊ) ውበት እንዴት እንደተሳለ ተመርምሯል፡፡ በዚህም ሴቶች ከማኅበረ ባህሉ ውጪ በራሳቸው መንገድ በመጓዛቸው መኮነናቸው፣ ውበታቸው በተለምዶዊው የውበት ማወደሻ መቅረቡ፣ ቅንድብ፣ ከንፈር እና ዓይን ወንድን የሚስቡ የቆንጆ ሴት ማሳያ ሆነዋል፡፡ ከውስጣዊ ውበት አንጻርም ሴቶች የሰናይ ባህሪ ባለቤት ተደርገው የሚገለጹት ማኅበረ ባህሉ ባዘጋጀላቸው መመዘኛ መሰረት መሆኑ፣ በብዙዎቹ ግጥሞች ሴቶች በማኅበረ ባህሉ መለኪያት ተመዝነው አታላይ፣ ከሃዱ፣ ተገዢ ተደርገው የተሳሉበት እና በራሳቸው አዲስ ማንነት የሚሄዱ ከአባታዊው ዓለም ልማድ ቀድመው የወጡ ሴቶች ተመልሰው የልማድ እስረኛ መሆናቸው ጥሩ ሰብዕና ሲያስብላቸው ታይቷል፡፡ በአጠቃላይ በወንዶች ስለ ሴቶች የሚገጠሙ ግጥሞች የአባታዊውን ስርዓት የሚያንጸባርቁ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ እንስቶች ለወንድች ደስታ እና ግዞት በሚመች መልኩ ተስለዋል፡፡ የወንዶች ብዕር ብዙውን ጊዜ እንስታዊነትን የሚገልጸው አባታዊው ዓለም በሚፈልገው ሁኔታ ብቻ ሆኗል፡፡ ተተኳሪ ግጥሞቹ የቀረቡበት ይዘት ሴትን ዝቅ አድርጓል፡፡ በእንስታዊው የሥነ-ጽሐፍ ሂስ ዓይን መረዳትም አብዛኞቹ ግጥሞች ሴቶችን ያቀረቡበት ሁኔታ “የተዛባ’ የሚያስብል መሆኑን የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡
  • Item
    የማንበብ ብልሃቶች አጠቃቀም፣ የማንበብ ግለብቃት እምነት እና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ፤ በሸገር ከተማ ውስጥ በሚገኙ ኦሮምኛ ቋንቋ አፍፈት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2016-06) በተግባር እንየው; ጌታቸው እንዳላማው(ዶ/ር)
    የዚህጥናትዋናዓላማየማንበብብልሃቶችአጠቃቀም፣የማንበብግልብቃትእምነትነናየአንብቦመረዳትችሎታያላቸውንተዛምዶአፋቸውንበኦሮምኛቋንቋበፈቱናአማርኛንእንደሁለተኛቋንቋበሚማሩየዘጠነኛክፍልተማሪዎችላይመፈተሽነው፡:የጥናቱተሳታፊዎችምበቀድሞውአዲስአበባዙሪያአሮምያልዩዞንበአሁኑሸገርከተማበሚገኙስምንትሁለተኛደረጃትምህርትቤቶችውስጥበ2013 ዓ.ምበሁለተኛውወሰነትምህርትትምህርታቸውንበመከታተልላይከነበሩ1,837 ተማሪዎችውስጥበስርዓታዊእድልሰጭየናሙናአመራረጥስልትየተመረጡ 369 የዘጠነኛክፍልተማሪዎችናቸው፡፡ለጥናቱጥያቄዎችናዓላማዎችምላሽለመስጠትምመረጃዎችከነዚህየጥናቱተሳታፊዎችላይበጽሑፍመጠይቆችናበፈተናተሰብስበዋል፡፡የጽሑፍመጠይቆቹየተማሪዎቹንየማንበብብልሃቶችንአጠቃቀምናየማንበብግለብቃትእምነትንለመለካትሲያገለግሉፈተናውደግሞየተማሪዎችንአንብቦመረዳትችሎታለመለካትአገልግሎትላይውሏል::በእነዚህየመረጃመሰብሰቢያመሳሪያዎችየተሰበሰቡትመረጃዎችአስተማማኝነትከተረጋገጠበኋላምየተሰበሰቡትመረጃዎችበገላጭናበድምዳሜያዊስታትስቲከስተተንትነዋል::በመሆኑምበተማሪዎችየማንበብብልሃቶችአጠቃቀም፣የማንበብግለብቃትእምነትናየአንበቦመረዳትችሎታመካከልያለውንተዛምዶለመፈተሽስፒርማንርሆፒርሰንየመፈተሻስሌትተግባራዊሲደረግየተማሪዎችየማንበብብልሃቶችአጠቃቀምናየማንበብግለብቃትእምነትአንብቦየመረዳትችሎታንምንያህልእንደሚተነብዩለማወቅደግሞየህብርተዛምዶመፈተሻተግባራዊተደርጓል::የትንተናውውጤትምየተማሪዎችየማንበብብልሃትአጠቃቀማቸው፣የማንበብግለብቃትእምነታቸውእናየአንብቦመረዳትችሎታቸውመካከለኛየሚባልደረጃላይይገኛል፤ከሶስቱየማንበብብልሃትአይነቶች (አጠቃላይብልሃት፣ችግርፈችብልሃትናደጋፊብልሃት) ችግርፈችየማንበብብልሃትንየበለጠተግባራዊያደርጉታል፤የተማሪዎችየማንበብብልሃቶችናየማንበብግለብቃትከአንብቦመረዳትችሎታጋርእናየማንበብብልሃቶችከማንበብግለብቃትእምነትጋርጉልህየሆነዝቅተኛአወንታዊተዛምዶእናዳላቸውሲያሳይ፤ነፃተላውጦዎቹየማንበብብልሃቶችአጠቃቀምናየማንበብግለብቃትእምነትጥገኛተላውጦየሆነውንአንብቦየመረዳትችሎታምንያህልእንደሚተነብዩየተደረገውየህብርተዛምዶፍተሻደግሞየማንበብብልሃቶችናየማንበብግለብቃትእምነትአንብቦመረዳትችሎታንመተንበይእንደሚችሉአሳይቷል፡፡የማንበብግለብቃትእምነትሆነየማንበብብልሃቶችአጠቃቀምአንብቦየመረዳትችሎታንየመተንበይአቅማቸውምተመጣጣኝነትእንዳለሁውጤቱአሳይቷል፡፡ከማንበብብልሃትአይነቶች(አጠቃላይብልሃት፣ችግርፈችብልሃትናደጋፊብልሃት)ውስጥምስችግርፈችየማንበብብልሃትአጠቃቀምከአጠቃላይየማንበብብልሃትአይነትናከደጋፊየማንበብብልሃትአይነትየበለጠናጉልህበሆነመልኩለአንብቦመረዳትችሎታመጎልበትአስተዋጽኦአለው::ይህጥናትአማርኛንእንደሁለተኛቋንቋበሚማሩኦሮምኛቋንቋአፍፈትበሆኑየዘጠነኛክፍልተማሪዎችላይብቻየተወሰነነው፤በመሆኑምሁሉንአቀፍድምዳሜለመስጠትእንዲያስችልሌሎችሁለተኛቋንቋዎችላይ፣አፍመፍቻቋንቋዎችላይናሌሎችየክፍልደረጃዎችላይጥናቶችቢደረጉ፤እንዲሁምአሁንተግባራዊእየተደረገያለውየንባብትምህርትአሰጣጥአንብቦለመረዳትችሎታመዳበርአስተዋፅያላቸውንየማንበብብልሃቶችአጠቃቀምናየማንበብግለብቃትእምነትተላውጦዎችሊያጎለብትየሚችልየንባብትምህርትአሰጣጥመሆኑቢፈተሽናቢረጋገጥመልካምነው፡፡
  • Item
    የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ፆታተኮር ተዛምዶ፤ በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2016-06) በለጠ ሕሉፍ; ፕሮፌሰር ጌታሁን አማረ; ዶክተር ማረው ዓለሙ(ተባባሪ ፕሮፌሰር)
    የጥናቱ ዋና ዓላማ የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ያላቸውን ተዛምዶ ከጾታ አንጻር መፈተሽ ነበር፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም ጥናቱ በተለዋዋጮቹ መካከል ያለውን ዝምድና የማሳየት አላማ ስላለው የተከተለው ዲዛይን (ስልት) ተዛምዷዊ ነበር፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም በደሴ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ደረጃ የሁለተኛው ሳይክል ካላቸው ትምህርትቤቶች መካከል በመምህር አካለወልድ የነበሩ ከ11ኛ G እስከ L ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ (107 ወንዶችና 69 ሴቶች በአጠቃላይ 176) ተማሪዎች በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎቹ፤ የስሜታዊ ብልህነት መጠይቅና የመጻፍ ተነሳሽነት መጠይቅ እንዲሞሉ እንዲሁም የመጻፍ ችሎታን ለመፈተሽ የሚያገለግል የመጻፊያ ርእስ በመስጠት እንዲጽፉ በማድረግ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተገኙት መረጃዎችም በገላጭ ስታትስቲክስ (በአማካይ ውጤትና በመደበኛ ልይይት)፣ የርስበርስና የጠራ ዝምድናቸውን ለመለየት በፒርሰን የተዛምዶ መለኪያ እንዲሁም በከፊል የተዛምዶ መፈተሻ ዘዴ ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤቶች እንዳመላከቱትም በስሜታዊ ብልህነት፣ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታተኮር ዝምድና ታይቷል፡፡ በሌላ በኩል የስሜታዊ ብልህነት ዘርፎች ከመጻፍ ችሎታ ጋር ተዛምዷቸው ከጾታ አንጻር ልዩነት አላቸው፡፡ እንዲሁም የስሜታዊ ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ከተነሳሽነት አንጻር ልዩነት አሳይተዋል፡፡ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታን መሰረት አድርጎ ልዩነት አልታየም፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም ጾታ ጣልቃገብ ሲሆን በተላውጦዎቹ መካከል ልዩነት ያሳያል ወደሚልና የስሜት ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ተዛምዶ የሚኖራቸው የመጻፍ ተነሳሽነት ሲኖር ነው ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም አስተያየቶች ተጠቁመዋል፤ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡
  • Item
    ነገረ-ህላዌ በተመረጡ የአማርኛ ግጥሞች ውስጥ
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2017-10) አንለይ ጥላሁን; ሰላማዊት መካ (ረ/ፕሮፌሰር)
    ነገረ-ህላዌ በተመረጡ የአማርኛ ግጥሞች ውስጥ የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ ጥናት፣ የነገረ-ህላዌ ንድፈ ሃሳብን መሰረት አድርጎ ነፃነት፣ ኃላፊነት፣ ውሳኔ፣ ምርጫ እና ተግባርን በመለየት እነዚህ ጉዳዮች በአማርኛ የግጥም መድበሎች ውስጥ በተካተቱ የተመረጡ ግጥሞች ውስጥ በምን መልኩ እንደተገለጹ ተንትኗል፡፡ ይህን ጥናት ለማከናወን በዓበይትነት የተመረጠው የነገረ-ህልውና ንድፈ-ሃሳብ በመሆኑ በትንተና ዘዴ መረጃዎቹ ተተንትነዋል፡፡ እነዚህ ግጥሞች ከ1980 እስከ 2012 ዓ.ም ከታተሙ አስራ አምስት መድበሎች ውስጥ የተመረጡ ሲሆን ግጥሞቹ በጭብጥ ደረጃ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሳዩ ናቸው። ጥናቱ፣ የተመረጡት ግጥሞች ‹‹ማደሪያውን ጠርቶ መኖሪያውን›› ወይም በተገላቢጦሽ የሆነ የአንድምታ ትርጉም የያዙ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው፣ ለጥናቱ የተመረጡት የአማርኛ ግጥሞች ውስጥ ጎልተው የታዩት የህልውና ጉዳዮች ነፃነት፣ ኃላፊነት፣ ምርጫ፣ ውሳኔ እና ተግባር ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች ውስጥ የፈጣሪ ህልውና እንዲሁም ዋና ዋና የሕብረተሰብ እሴቶች በመተቸታቸው እንግዳ የሆኑ አዳዲስ እይታዎች ተስተውለዋል፡፡ በአዳዲስ እይታዎቹ አማካኝነትም ግጥሞቹ የነገረ-ህላዌ ጉዳዮችን ያዘሉ ሆነው ተገኝቷል። በመጨረሻም የግጥሞቹ ዋና ማሰሪያ ነፃነት ሆኖ ፖለቲካን፣ እምነትንና ባህልን ሳይጮሁ የሚንዱ፣ እንዲሁም የግለሰብን ነፃነት የሚያፀድቁ መሳሪያዎች መሆናቸው በጥናቱ ታይቷል፡፡
  • Item
    አንብቦ መረዳት እና የመጻፍ ክሂል ቅንጅታዊ የይዘት አቀራረብ ትንተና በ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ተተኳሪነት (በ2015 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የታተመ)
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2024-08) ሰይድ አሊ ይመር; አቶ ደረጀ ገብሬ
    ይህ ጥናታዊ ፅሑፍ ዋና ዓላማው በ2015 ዓ/ም ታትሞ በስራ ላይ የዋለው የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ መፅሀፍ ውስጥ የአንብቦ መረዳትና የመፃፍ ክሂሎች ቅንጅታዊ የይዘት አቀራረብ መፈተሽ በ8ኛ ፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሀፍ ተተኳሪ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካትም በሰነድ ፍተሻ እና በቃለመጠይቅ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የጥናቱ ዓላማ በተማሪው መማሪያ መፅሀፍ ውስጥ የመፃፍ ክሂልና የአንብቦ መረዳት ክሂልን አዋህዶ ይዘቶችንና መልመጃዎችን መቅረባቸውና አለመቅረባቸው መመርመር ፤የአንብቦ መረዳት እና የመፃፍ ክሂል አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡ ምንባቦች የቋንቋ ግልፅነት ማየትና ሁለቱን ክሂሎች አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡትን መልመጃዎች ግልፅነት መመርመር ነው፡፡ ይህንን ጥናታዊ ፅሁፍ ከፍፃሜ ለማድረስ አጥኝው የተጠቀመ የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎች መጠናዊ የምርምር ዘዴ እና ዓይነታዊ የምርምር ዘዴዎች ናቸው፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ሰነድ ፍተሻ እና ቃለ መጠይቅ ናቸው። ከመረጃዎቹ የተገኙት ውጤቶች የሚያመለክቱት አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂልን የሚመለከቱ ይዘቶች አቀራረብ ለመማር ማስተማሩ ሂደትም ሆነ ለተማሪዎቹ ልምምድ አመቺ መሆናቸውን፤ አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂልን የሚመለከቱ ይዘቶችና መልመጃዎች አቀራረብ የተማሪዎችን ደረጃ፣ዕድሜና ችሎታ እንዲሁም ዳራዊ እውቀታቸውን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ መሆናቸውን፤የመማሪያ መጽሀፉ አቀራረብ አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂሎች በተቀናጀ መልኩ እንደተዘጋጁና የማስተማሪያ መሳሪያዎቹ አንብቦ የመረዳትንና የመጻፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ለማስተማር እገዛ እንዳላቸው ጥናቱ ፍተሻ አድርጓል፡፡ በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ መጨረሻ ውጤት የሚያሳየው የአንብቦ መረዳት እና ለፅህፈት ክሂል አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡት ምንባቦች ቋንቋውን እንደሚረዱት ሆኖ ቀርቧል፡፡ቢሆንም የተወሰኑ ይዘቶች እና መልመጃዎች የቋንቋ ግልፅነት የሌላቸው መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡ በመጨረሻም ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ የሚሰጠው ማሻሻያ ሃሳብ ፤ተማሪዎች አንብበው የተረዱትን ሀሳብ በፅሁፍ ለመግለፅ ይዘቶች እና መልመጃዎች በሰፊው ቢዘጋጅ እና ተቀናጅተው ቢቀርቡ፡፡ የአንብቦ መረዳት እና የፅህፈት ክሂልን በቅንጅት ለማስተማር የቀረቡት ምንባቦች የሃሳብ ግልፅነት የሌላቸው መሆኑን ሲያሳይ ፤ምንባቦች ተሻሽላው ቢቀርቡ በማለት ጥናታዊ ፅሁፍ የመፍትሔ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
  • Item
    የወላይታ ብሔረሰብ ተረቶች ክዋኔ ምደባና የይዘት ትንተና
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2024-03) ትሬዛ ዮሴፍ; ዓለሙ ካሣዬ (ዶ/ር)
    ይህ ጥናት "ወላይታ ብሔረሰብ ተረቶች ክዋኔ ፣ ምደባ እና የይዘት ትንተና" ላይ የተሰራ ሲሆን ዓላማውም በወላይታ ብሔረሰብ የሚተረቱ ተረቶችን በመሰብሰብ ክዋኔያቸውን ማሳየት፣ ምደባ ማካሄድ እና የይዘት ትንተና ማድረግ ነው። ተረቶቹ የተሰበሰቡት ከብሔረሰቡ መረጃ አቀባዮች ሲሆን፤ መረጃ ለመሰብሰብ ምልከታ፣ ቃለመጠይቅ እና የተተኳሪ ቡድን ውይይት ዘዴዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። የተሰበሰቡ ተረቶች ክዋኔያቸው ለማሳየት ተሞኳሯል። 67 ተረቶች ከመስክ ላይ የተሰበሰቡ ሲሆን ተግበራዊ ምርምርን (Functional research) እና ክዋኔን ማዕከል ያደረገ (Performance centered approach) ዘዴን በጥምረት በመጠቀም ተጠንተው በገላጭና በይዘት ትንተና ስነዘዴ ተተንትነዋል። በጥናቱ ግኝት ተረቶቹ በአከባቢያዊ መጠሪያቸው "Tumuba woyko Taarikiyaa" እውነተኛ ታሪክ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ እና "Leemisuwaa" የፈጠራ ተብለው ይታወቃሉ። "Tumubaa woyko Taarikiyaa" ተብለው የሚታወቁ ተረቶች በብሔረሰቡ ዘንድ እውነት ናቸው ተብሎ የሚታመንባቸው ሲሆን ፤ ስለብሔረሰቡ አመጣጥ ፣ ብሔረሰቡ ስላካሄዳቸው ጦርነቶች፣ ስለ ቦታ እና ጎሳ ስያሜዎች፣ ስለ የጎሳ መሪዎች ጀግንነት የሚተርኩ ናቸው። "Leemisuwaa" በመባል የሚታወቁት ደግሞ ፈጠራዊ መሆናቸውን የሚታመንባቸው ሲሆን ፤ አእምሮን እያዝናኑ ስነምግባር የሚያስተምሩ ፣ የብሔረሰቡን ባህል፣ ልማድ እና አኗኗር ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚያደርጉ ናቸው። ተረቶቹ ምሁራን በተከተሉት የአመዳደብ ስልት አንጻር ሲታዩ ደግሞ ሌጀንድ፣ ገላጭና ፋቡላ ናቸው። ተረቶቹ በይዘታቸው በአምስት ዋና ዋና ምድቦች የተከፋፈሉ ሲሆን እነሱም ብልህነትን፣ መጥፎ ባህሪያትን፣ ኢፍትሃዊነት፣የእንጀራ እናትን እና ሞኝነትን የሚመለከቱ ናቸው። እኩይ የሚባሉ ተግባራትን በመኮነን እንዳይስፋፉ የሚገታባቸው፣ መልካም የሚባሉትን ደግሞ በመደገፍ ቀጣይነት እንዲኖራቸው በማድረግ ታሪክ እና ባህል የሚተከልባቸው መሆናቸውን ጥናቱ አሳይቷል። ጥቂቶቹ ደግሞ የብሔረሰቡ ባህል የማስቀጠል እና የመተርጎም ጥቅም ያላቸው፣ የብሔረሰቡ አባላት ለሚያነሷቸው ፍልስፍናዊ የሆኑ ጥያቄዎችን የሚሰጥባቸው መሆናቸው ጥናቱ አመላክቷል።
  • Item
    ራስን ፍለጋ፣ በአለማየሁ ገላጋይ ሶስት የተመረጡ ልቦለዶች ውስጥ፣ ስነልቦናዊ ንባብ
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2024) ገ/ጻዲቅ ቢያዝን; አየለ ፍቅሬ ( ዶ/ር)
    ሥነፅሁፍ እና እንደ ስነልቦና አይነት ሌሎች የትምህርት መስኮችን ወስዶ የሥነፅሁፍ ንባብ ማድረግና ጹሁፋዊ ትንተና መከወን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተለመደ የመጣ የሥነፅሁፍ የጥናት መስክ ሁኗል፡፡ ነገር ግን አብዚኞቹ ጥናቶች በብለይ ሚቶልጅና በፍሩድያን ንድፈ ሀሳብ ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው፡፡ ስለዙህ ራስን ፍለጋ የሚለውን ጽንሰሀሳብ ከዩንጊያን ንድፈ ሀሳብ አንጻር መመልከት ለመስኩ ተጨማሪ እይታ ይዞ ይመጣል፡፡ በመሆኑም ይህ ጥናትም ዋና አሊማው በአለማየሁ ገሊጋይ በፍቅር ሥም፣ታለ በዕውነት ሥም እና ሐሰተኛው በእምነት ሥም ልቦለዶች ውስጥ የራስን ፍለጋ ስነልቦናዊ እሳቤን በይነ-ቴክስታዊ ንባብ በማድረግ መተርጎም፣ማሳየትና መፈከር ነው፡፡ ይህ ጥናት ጽሑፍ ትንተና(Text analysis) ከሚባለው የጥናት አይነት ውስጥ ይመደባል፡፡ ለጥናቱ የተመረጡ ሶስት ልቦለዶች በታላሚ የናሙና አመራረጥ ዘዳን በመጠቀም የተመረጡ ሲሆን ይህን ጥናት ከግብ ለማዲረስ የሹሜትን የዩንጊያን የራስን ፍለጋ እሳቤ ዋና መገለጫዎች እና ሥረመሰረታዊያን በማቀናጀት የጽሑፍ ትንተና ተደርጓል፡፡ የሶስቱም ታላሚ ልቦለዶች ዋና ገፀባህርይ ታለ በራስን ፍለጋ በሁለት ዋና የህይወት አጋማሽ ሂደት ውስጥ የነበረ ሲሆን በመጀመሪያው አጋማሽ ህይወት የራሱን ግላዊ ክብር መገንባት ላይ አተኩሯል፡፡ ይኸውም በማህበረሰቡ ወንድ የሚያስብለውን ጉዳዮች መፈጸም እና ራሱን በሌሎች ዘንዴ የአዋቂነትን ክብር( በፍልስፍና ተከራክሮ የሚያሸንፍ) ሁኖ መገኘት ነበር፡፡ ከዙህ በመቀጠሌ ወደ ሁለተኛው አጋማሽ ህይወት በስኬት የተሸጋገረ ሲሆን ይህ ደግሞ በዙህ ምድር የመጣበትን ዓላማ መጠየቅ፣ ፈጣሪን መርምሮ ለመረዳት እና የፈጣሪና የተፈጥሮን ግንኑኘት የፈለገበት ነበር፡፡ በታለ የራስን ፍለጋ ህይወት ያጋጠሙ ፀረራስን ፍለጋዎች መኖራቸውን ጥናቱ አረግጧሌ፡፡ ይህም በመጀመሪያ አጋማሽ ህይወት ያደጉ ኢጎዎችን በሁለተኛው አጋማሽ ህይወት ካለማስገዛት የመነጨ ሲሆን ራስን ፍለጋው በቶሎ መልስ ካላገኘሁ የሚል በህይወት ተስፋ መቁረጥና ፍርሃት ናቸው፤ ራስን እስከማጥፊት ማሰብና መፀፀት የፀረራስን ፍለጋው ውጤቶች ናቸው፡፡ የዩንግ ሥረመሰረታዊያን ማለትም ፐርሶና፣ ሻድው፣ አኒማ እና ሰልፍ በታለ የራስን ፍለጋ ህይወት ወስጥ በጉልህ እንደተስተዋሉ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ የዩንጊያን የራስንፍለጋ መገለጫ እሳቤዎች እና ሥረመሰረታዊያን ለልቦለዶቹ ጭብጥ መዳበር ከፍተኛ አስተዋፆ ነበራቸው፡፡ ይህን በእያንዳንዱ እሳቤዎች ስር የተጠየቁ የራስን ፍለጋ ጥያቄዎችና የተገኙ መልሶች፣ እንዲሁም ሂደቶች ልቦለዱ እንዲዳብር ከፍተኛ አስተዋጽዎ አድርገዋል
  • Item
    አንብቦ መረዳት እና የመጻፍ ክሂል ቅንጅታዊ የይዘት አቀራረብ ትንተና በ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ተተኳሪነት (በ2015 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የታተመ)
    (አዲስ አባባ ዩኒቨርሲት, 2023-08) ሰይድ አሊ ይመር; አቶ ደረጀ ገብሬ
    ይህ ጥናታዊ ፅሑፍ ዋና ዓላማው በ2015 ዓ/ም ታትሞ በስራ ላይ የዋለው የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ መፅሀፍ ውስጥ የአንብቦ መረዳትና የመፃፍ ክሂሎች ቅንጅታዊ የይዘት አቀራረብ መፈተሽ በ8ኛ ፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሀፍ ተተኳሪ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካትም በሰነድ ፍተሻ እና በቃለመጠይቅ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የጥናቱ ዓላማ በተማሪው መማሪያ መፅሀፍ ውስጥ የመፃፍ ክሂልና የአንብቦ መረዳት ክሂልን አዋህዶ ይዘቶችንና መልመጃዎችን መቅረባቸውና አለመቅረባቸው መመርመር ፤የአንብቦ መረዳት እና የመፃፍ ክሂል አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡ ምንባቦች የቋንቋ ግልፅነት ማየትና ሁለቱን ክሂሎች አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡትን መልመጃዎች ግልፅነት መመርመር ነው፡፡ ይህንን ጥናታዊ ፅሁፍ ከፍፃሜ ለማድረስ አጥኝው የተጠቀመ የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎች መጠናዊ የምርምር ዘዴ እና ዓይነታዊ የምርምር ዘዴዎች ናቸው፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ሰነድ ፍተሻ እና ቃለ መጠይቅ ናቸው። ከመረጃዎቹ የተገኙት ውጤቶች የሚያመለክቱት አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂልን የሚመለከቱ ይዘቶች አቀራረብ ለመማር ማስተማሩ ሂደትም ሆነ ለተማሪዎቹ ልምምድ አመቺ መሆናቸውን፤ አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂልን የሚመለከቱ ይዘቶችና መልመጃዎች አቀራረብ የተማሪዎችን ደረጃ፣ዕድሜና ችሎታ እንዲሁም ዳራዊ እውቀታቸውን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ መሆናቸውን፤የመማሪያ መጽሀፉ አቀራረብ አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂሎች በተቀናጀ መልኩ እንደተዘጋጁና የማስተማሪያ መሳሪያዎቹ አንብቦ የመረዳትንና የመጻፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ለማስተማር እገዛ እንዳላቸው ጥናቱ ፍተሻ አድርጓል፡፡ በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ መጨረሻ ውጤት የሚያሳየው የአንብቦ መረዳት እና ለፅህፈት ክሂል አቀናጅቶ ለማስተማር የቀረቡት ምንባቦች ቋንቋውን እንደሚረዱት ሆኖ ቀርቧል፡፡ቢሆንም የተወሰኑ ይዘቶች እና መልመጃዎች የቋንቋ ግልፅነት የሌላቸው መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡ በመጨረሻም ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ የሚሰጠው ማሻሻያ ሃሳብ ፤ተማሪዎች አንብበው የተረዱትን ሀሳብ በፅሁፍ ለመግለፅ ይዘቶች እና መልመጃዎች በሰፊው ቢዘጋጅ እና ተቀናጅተው ቢቀርቡ፡፡ የአንብቦ መረዳት እና የፅህፈት ክሂልን በቅንጅት ለማስተማር የቀረቡት ምንባቦች የሃሳብ ግልፅነት የሌላቸው መሆኑን ሲያሳይ ፤ምንባቦች ተሻሽላው ቢቀርቡ በማለት ጥናታዊ ፅሁፍ የመፍትሔ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
  • Item
    በ2012 ዓ.ም በፋና“ጉዞ ኢትዮጵያ”ና በኢቢኤስ “ኢትዮጵያን እንወቅ” ሳምንታዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ውስጥ የተካተቱ ፎክሎራዊ ጉዳዮች ትንተና
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-08) ሸዋቀና ታህለው; ዓለሙ ካሣዬ (ዶ/ር)
    ይህ ጥናት “በ2012 ዓ.ም በፋና“ጉዞ ኢትዮጵያ”ና በኢቢኤስ “ኢትዮጵያን እንወቅ” ሳምንታዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ውስጥ የተካተቱ ፎክሎራዊ ጉዳዮች ትንተና” በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ተተኳሪ በሆኑት ሁለቱ የቴሌቨዥን ተቋማት ሳምንታዊ ፕሮግራሞች ውስጥ የትኞቹ የፎክሎር ዘውጎች ተካተዋል?፤ ፎክሎራዊ ዘውጎቹ ለቴሌቭዥን ጣቢያዎቹ ምን ፋይዳ አላቸው?፤ ለጥናቱ በተለዩት ጣቢያዎች የፎክሎር መካተት ለመስኩ የምርምር ዘርፍ የሚኖረው ፋይዳ ምንድን ነው?። ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተችሏል፡፡ጥናቱ የተከተለው አይነታዊ የአጠናን ዘዴን ሲሆን፤በሰነድ ፍተሻና በቪዲዮ ምልከታ የተሰበሰበው መረጃ በገለጻና በትረካ ስልት ትንተና ተደርጎበታል፡፡በመጨረሻም አራቱ የፎክሎር ዘውጎች ሥነ-ቃል፣ ሀገረሰባዊ ልማድ፣ ሀገረሰባዊ ትውን ጥበብና ቁሳዊ ባህል በተተኳዋሪ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መካተታቸው በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ ፎክሎሮቹ የሚያስገኟቸውን ፋይዳዎች በተመለከተም ማሕበረሰብን ከማስተማር፣ከቱሪዝም፣ከቴሌቭዥን ፕሮግራም፣ከጥናትና ምርምር፣ከመቀስቀስና ከማንቃት አኳያ አይተኬ ሚና ያላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡ እንዲሁም የትረካ ስልትን የማሳመር፣የፕሮግራም ተደማጭነትን የማሳደግ ሚና ያላቸው መሆኑ፤ ለማስታወቂያ ስራዎች ተደራሽነትና አይረሴነት የሚጫወቱት ሚና መኖሩ፣ የታሪክ ጭብጥን ለማጉላትና ገጸ-ባህርያትን ለማቅረብም የማይናቅ ድርሻ ያላቸው መሆኑ፣ አድማጭና ተመልካቾች ለጣቢያዎቹ አድማጮችና ተመልካች ደንበኞች ሆነው እንዲቀጥሉ የማድረግ ሚና እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡በመጨረሻም አጥኚው ፎክሎር ለማኅበረሰብ የሚያሰገኛቸው ጠቀሜታዎች ዘላቂነት ይኖራቸው ዘንድ በዚህ ጥናት ተተኳሪ የሆኑትን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች የተሰማሩ የፕሮግራም አቅራቢ ጋዜጠኞች ፎክሎሮችን በመዘገብና ሰንዶ በማቅረብ ተግባር በመትጋት ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ማህበረሰባዊ እሴቶችን ለትውልድ ለማሻገር ቢሞክሩ በሚል የመፍትሄ ሐሳቡን ለመጠቆም ሞክሯል፡፡
  • Item
    የሴቶች ተሞክሮ በተመረጡ የአማርኛ ግለታሪኮች
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ, 2024-08) ብሌን መንግስቱ; የወንድወሰን አውላቸው(ዶ/ር)
    የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተመረጡ የሴቶች ተሞክሮ በአማርኛ ግለ ታሪክ ፍተሻ ነው፡፡ ጥናቱ ንድፍ አይነታዊ ገላጭ የጥናት ንድፍ የተከተለ ነው፡፡ የመረጃ ምንጮች ሁለተኛ ደረጃ (ዳህራይ) የመረጃ ምንጭ ነው፡፡ ይህም ማለት በግለሰቦች በግላቸው የተፃፉ የአማረኛ ግለ ታሪኮች ትሙት ግድ የለም በዶ/ር ትግስት ግርማ ፣የፀሐይ ጉዞ ወ/ሮ ፀሐይ ይትባረክ የውብ የውብ ድንበር እውተኛ ታሪክ በወ/ሮ ውብ ድንበር ነጋሽ የተፃፈ የአማረኛ ግለ ታሪክ መጽሀፍት መሰረት አድርጎ የተሰራ ጥናት ነው፡፡ የናሙና አመራረጥ አላማ ተኮር ነው፡፡ የተመረጡ የአማረኛ ግለ ታሪክ መፅሀፍት በዓላማ በራሱ አነሳሽነት በቀላሉ በገበያ ላይ የሚገኙ የቅርብ የታተሙ መጽሀፍት በመሆኑ ጭምር ነው፡፡ የመረጃው ትንተና ዘዴ ይዘት ትንተና ላይ አተኩሯል፡፡ ማለትም በመጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ በተለዩት ርእሰ ጉዳዮች አንፃር ተተንትኗል፡፡ በዚህ ባሻገር ግለ ታሪኮች በእንስታዊ (ሴትነት ግዴ ትግል) አንፃር በአምስት ቁልፍ ርእሰ ጉዳዮች ማለትም ፓትሪያሊክ(አባዊ) ሥርአት ኢንተርሴክሽናሊቲ ፣የሥርአት ፆታ አፈጻፀም፣ ማህበራዊ ግንባታና የወንድ ዕይታ በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች አንፃር ፍተሸ ተደርጋል፡፡ በመሆኑም ግለ ታሪክ አፃፃፍ ላይ የሚመለከተው ክፍል ትኩረት ቢያደርግ የሕይወት ተሞክሮ ማህራዊ ግንኙነት እና የፆታ እኩልነት እዲሁም ጥበብና ትምህርትን በማስፋት ከጾታ ጋር ተያያዞ የሚፈጠሩ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ ችግሮች ላይ መፍትሔ ለማበጀት ይረዳል፡፡ ቁልፍ ቃላት ፡- የሴቶች ተሞክሮ፣ ግለ ታሪክ አማርኛ እንስታዊ ጽንሰ ሀሳብ፡፡
  • Item
    የሴቶችና የወንዶች አለባበስና አጊያጊያጥ በመርሐቤቴ ወረዳ
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-09) ፍስሃ ጌታቸው; የኔዓለም አረዶ(ዶ/ር)
    ይህ ጥናት በመርሐቤቴ ወረዳ የሴቶችና የወንድች አለባበስና አጊያጊያጥ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ አልባሳትና ጌጣጌጦች በማጥናት የተጠኚውን ማህበረሰብ ፈጠራ ውጤት፣ እምነት፣ መለያና የአኗኗር ዘይቤን መመርመር የመጀመሪያው አነሳሽ ምክንያት ሲሆን በቁሶቹ ላይ የሚስተዋለውን የለውጥ ምክንያት መፈተሸና ቁሶቹን ለቀጣይ ትውልድ በመረጃነት ሰንድ ማቆየት ደግሞ ሁለተኛው የጥናቱ መነሻ ምክንያት ነው፡፡ የዚህ ጥናት ዓብይ ዓላማ ለጥናት በተመረጠው አካባቢ የሚከወኑ የሴቶችና ወንድች አለባበስና አጊያጊያጥ ፋይዳን መመርመር ነው፡፡ እንዲሁም የቁሶቹን አካላዊ ገፅታ ማሳየት፣ ትዕምርታዊ ትርጉም መግለፅ፣ ለውጥ የተስተዋለባቸውንም ሆነ ያልተስተዋለባቸውን ቁሶቹ መመርመር እና ቁሶቹን ለመጪው ትውልድ እንዲሸጋገሩ ሰንድ ማቆየት የሚሉ ንዐሳን ዓላማዎች አሉት፡፡ ጥናቱ ከዓይነታዊ የምርምር ዘዴአንደ የሆነው ገላጭ የምርምር ስሌትን የተከተለ ሲሆን ቀዳማይና ካልዓይ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀምና ለጥናቱ አስፈላጊ መረጃዎችን በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ የቡድን ውይይት መረጃዎቹ ተሰብስበዋል፡፡ እንዲሁም ዘጠኙ (9) የSchlereth መተንተኛ ሞዴሎች ለመረጃ መተንተኛነት፣መዋቅራዊ ተግባራዊነት እና ለውጥና ቀጣይነት ንድፈ ሃሳቦች ዳግሞ ለጥናቱ መቀንበቢያነት ውለዋል፡፡ በታላሚ ናሙና (Purposive sampling) አመራረጥ ዘዴ መሰረት በወረዳው ከሚገኙ 23 ቀበሌዎች ቁሶቹ እስካሁን ድረስ ሳይበረዙ ያቆዩና ባላቸው የአየር ንብረት ልዩነት መሰረት አምስት ቀበሌዎች፣ እንዲሁም ከወጣት እስከ አዛውንት ያለና ባህሉን በደንብ የሚያውቁ 23 ወንዶችና 13 ሴቶች በድምሩ 36 መረጃ አቀባዮች በሀገር ሽማግሌዎችና በባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት መረጃ ሰጭነት ተመርጠዋል፡፡ በተመረጡ 22 አልባሳት እና 24 ጌጣጌጦች እንዲሁም 9 የፀጉር አሰራር ዓይነቶች ላይ ትንተና ተደርጓል፡፡ ጥናቱ በማህበረሰቡ የሚታወቁ አልባሳትና ጌጣጌጥ የትኞቹ ናቸው? የአለባበስ ሥርዓታቸው ምን ይመስላል? የመልበሻ አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? ቁሶቹ በማን መቼ እንዴትና ለምን ይሰራሉ? በየዕዴሜ ደረጃቸው ያለ አልባሳትና ጌጣጌጦች መለያቸው ምንድነው? በአልባሳቱና ጌጣጌጡ ላይ ለሚታዩ ለውጦች ምክንያታቸው ምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎችን መልሷል፡፡ ከዚህ አንፃር የሚከተለትን ነጥቦች በጥናቱ ግኝት የተመላከቱ ናቸው፡፡ እነሱም የማህበረሰቡ አልባሳትና ጌጣጌጦች በአካባቢው ከሚገኙ ጥሬ ዕቃዎችና የፊብሪካ ምርት ከሆኑ ግብዓቶች በአካባቢው ሸማኔ፣ ልብስ ሰፉዎች፣ በእደ ጥበብ ሙያተኞች የሚጋጁና ገበያው በሚያቀርባቸው መሰረት የሚገኙ ናቸው፡፡ ከአገልግሎት አኳያ የለባሹን ደህንነት የማስጠበቅ፣ ውበትን የማጉላት፣ ፆታን፣ ማንነትን፣ ዕድሜን፣ ጀግንነትን ኃይማኖትን፣ ማህበራዊ ግንኙነትን፣ ማህበራዊ ደረጃዎችን የሚገልፁ ሲሆን ከመዋቅር አኳያ ደግሞ ቁሶቹ ሰርዓተ ማህበሩ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የቁሶቹ ተምሳሌታዊ ትርጉም የማህበረሰቡን አመለካከት፣ ፍልስፍና፣ እውቀት፣ እምነት፣ ማንነት፣ ማህበራዊ ደረጃ፣ ውበት፣ ፆታ ወዘተ ጉዳዮችን የሚገልፁ ሲሆኑ አሰራራቸው ደግሞ ጥበባዊ፣ ታሪካዊ፣ አካባቢያዊ፣ መዋቅራዊ፣ ማህበረሰባዊ ወዘተ መለያ ያላቸው ናቸው፡፡ እንዲሁም ከለውጥና ቀጣይነት አኳያ ምንም ያልተለወጡ፣ በከፉል የተለወጡ፣ ሙሉ ለሙሉ የተለወጡ ቁሶች መኖራቸው የጥናቱ ግኝት ያመላክታል፡፡ በዚህም መነሻነት የማህበረሰቡ ማንነት መገለጫ የሆኑትን ቁሶች የማልማትና ጠቃሚነታቸውን የማጉላት ስራ በድግግሞሽ ቢሰራ ማህበረሰቡን ለማስተዋወቅ፣ ማንነቱን በዘላቂነት ይዞ ለማስቀጠልና ከባህሉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ የሚያደርገው ይሆናል የሚል የይሁንታ ሃሳብ በማቅረብ ጥናቱ ተጠናቋል፡፡
  • Item
    ፕሮጀክት ተኮር መማር፣ በመጻፍ ችሎታና ተነሳሽነት ላይ ያለው ተፅዕኖ፤ በ10ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት
    (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-09) ስመኝ አለምነህ; ጌታሁን አማረ (ፕ/ር)
    የዚህ ጥናት ዓላማ ፕሮጀክት ተኮር መማር፣ ለተማሪዎች የመጻፍ ችሎታ እና ተነሳሽነትመሻሻል ያለውን ሚና መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ከግብ ለማድረስም ቅድመ ትምህርትናድኅረ ትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ከፊል ሙከራዊ (quasi-expermental) ስልትተግባራዊ ሆኗል፡፡ በጥናቱ የትግበራ ሂደትም አማራ ክልል በአላማ ተኮር ንሞናተመርጧል፤ ደብረማርቆስ ከተማ የሚገኘው ንጉስ ተክለሃይማኖት አጠቃላይ ሁለተኛደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ደግሞ በአመቺ ንሞና ከተመረጠ በኋላ በዚህ ትምህርትቤት የሚገኙ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በዕጣ ተመርጠው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ክልሉ በዓላማተኮር ንሞና የተመረጠው ጥናቱ አፍፈት ተማሪዎች ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ነው።ትምህርት ቤቱ በአመቺ ንሞና የተመረጠበት ምክንያትም ጥናቱ ከፊል ፍትነታዊእንደመሆኑ መጠን ትምህርት ቤቱን እና የአማርኛ ቋንቋ መምህራንን ልዩ ትብብር እናድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳዮችን የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህም የትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣መምህራንና ተማሪዎች ለጥናቱ ፈቃደኛ በመሆናቸው ነው፡፡ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በዕጣየተመረጡበት ምክንያት ደግሞ ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በስተቀር ጥናቱ በ9ኛ፣ 10ኛ እና11ኛ ክፍልተማሪዎች ላይ ቢካሄድ በተማሪዎች መረጃ የመሰብሰብ ሂደት ላይ ችግርአይኖርም ተብሎ ስለታሰበ ነው፡፡ መረጃዎች ከተሳታፊ ተማሪዎች በመጻፍ ችሎታ ፈተናእና በመጻፍ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ ተሰብስበዋል፡፡ የተገኙትመረጃዎችምየመተንተኛ ስልቱ እሙኖች በገላጭ ስታቲስቲክስ ከተፈተሹ በኋላ በሙከራና በቁጥጥርቡድኖች መካከል ልዩነት መኖር አለመኖሩን ለመፈተሽ የቅድመና ድኅረ ትምህርትአጠቃላይ የመጻፍ ችሎታ፣ ንዑሳን ችሎታዎች (ይዘት፣ አደረጃጀት፣ የቃላት አመራረጥናአጠቃቀም፣ የቋንቋ አጠቃቀም እና ስርዓተ አጻጻፍ) አማካይ ውጤቶችና የመጻፍ ተነሳሽነትየጽሑፍ መጠይቅ አማካይ ውጤቶች በባለብዙ ተላውጦ ልይይት ትንተና ዘዴ (Multivariate Analysis of Variance, MANOVA) ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ በተገኙትውጤቶች መሠረትም፣ የተማሪዎች አጠቃላይ የመጻፍ ችሎታ እና ንዑሳን ችሎታዎች(ይዘት፣ አደረጃጀት፣ የቃላት አመራረጥና አጠቃቀም፣ የቋንቋ አጠቃቀም እና ስርዓተአጻጻፍ) እንዲሁም የመጻፍ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ ውጤቶች የሙከራ ቡድንተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች አማካይ ውጤቶች ተሽለውና ጉልህ (p<.05) ልዩነት ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል። በዚህም መሠረት ፕሮጀክት ተኮር መማር የተማሪዎችንአጠቃላይ የመጻፍ ችሎታ እና ንዑሳን ችሎታዎች እንዲሁም የመጻፍ ተነሳሽነት ለማሻሻልሚና እንዳለውና ሚናውም ከፍተኛ እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በመሆኑም፣ የመጻፍትምህርትን በፕሮጀክት ተኮር መማር ተግባራት ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡
  • Item
    የየምወድሽ በቀለ ወልደገብርኤል የሕይወት ታሪክና ስራዎቿ
    (Addis Ababa University, 2024-06) ዙፋን ካሳው; ሙሐመድ አሊ (ዶ/ር)
    ‹‹የየምወድሽ በቀለ የሕይወት ታሪክና ስራዎቿ›› ጥናት በየምወድሽ በቀለ በስራና የሙያ የሕይወት ታሪክ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡ ጥናቱ በዋናነት ከጋዜጠኛነት ሙያ ጋር የተሳሰረችበትን አጋጣሚና የሰራችበትን የህይወት ጉዞ፣ ከድርሰት መጻፍ ጋር የተዋወቀችበትንና ድርሰቶቿ ከጋዜጠንነት ሙያዋ ጋር ያላቸውን ትስስር የሚመረምር ነው፡፡ ለዚህም ሲባል በአንድ በኩል ተጠኝዋን ግለሰብና ቤተሰብ እንዲሁም የቅርብ ጓደኞች ቃለመጠይቅ በማድረግ የህይወት ታሪኳ ክፍል መረጃ ተሰብስቧል፡፡ የሙያዋንና የድርሰት ስራዎቿን ትስስር ለመመርመርም ከህይወት ታሪኳ ጋር ትስስር ያላቸውን የድርሰት ስራዎች በጥልቅ ምንባብ ተመርጠዋል፡፡የምወድሽ በቀለ ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2014 ዓ.ም.ድረስ አስር ረጅም እና አጫጭር ልቦለዶች፣የግጥም መድብሎችና የእውነተኛ ታሪኮች ስብስቦች አሳትማለች፡፡ከሌሎች ደራሲያን መድብሎች ጋር ደግሞ 6 አጫጭር ልቦለዶች ፣ግጥሞችና እውነተኛ ታሪኮች አሏት፡፡በጥናቱ በተመረጡት ልቦለዶች በግል ህይወቷና ከስራ አለም ከነበሯት ገጠመኞቿ ተነስታ በሴቶች ላይ እንደምታተኩር ፤በአፃፃፍ ስልት ደግሞ የወንጀል አፃፃፍን እንድትከተል ተፅእኖ አድርጎባታል::
  • Item
    በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎች የራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም፣ የማንበብ ግለብቃት እምነት እና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ጾታ ተኮር ተዛምዶ፤ በተመረጡ የአስራአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
    (Addis Ababa University, 2024-06) ይድነቃቸው ገረመው ዓለሙ; ገረመው ለሙ (ዶ/ር); ሰይድ ይመር (ዶ/ር)
    በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ፣ የማንበብ ግለብቃት እምነትና የራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም መካከል ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ነው፡፡ የተዛምዶ ፍተሻውን ለማድረግ ጥናቱ ተዛምዷዊ የምርምር ንድፍን የተከተለ ሲሆን በአዲስ አበባ አስተዳደር በሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የአማርኛ ቋንቋ አፍፈትየሆኑ የአስራአንደኛ ክፍል ተማሪዎች እኩል እድል ሰጭ ንሞና ዘዴ በመጠቀም የጥናቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡ የአንብቦ መረዳት ችሎታ መለኪያ ፈተና፣ የማንበብ ግለብቃት እምነት መጠይቅ እና የራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም መጠይቅ በመጠቀም ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን መሰብሰብ ተችሏል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ ከተጠናቀረ በኋላ ገላጭና ተንባይ ስታትስቲክሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለጥናቱ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የሚያስችል የመረጃ ትንተና ተካሂዷል፡፡ ከመረጃ ትንተናው በተገኘው ውጤት መሰረትየ11ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ በምን ደረጃ ላይ እንደሆነ ለሚጠይቀው የጥናቱ ጥያቄ የፈተናው አማካይ ውጤት(56.65%) እና የውጤት ስርጭቱ አብዛኞቹ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው መካከለኛ እንደሆነ አሳይቷል፡፡ ጾታ በተላውጦዎቹ ላይ ያሳየውን ልዩነት ለማወቅ በተደረገ የቲ ቴስት ፍተሻ ውጤት መሰረት ጾታ በራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም ላይ ብቻ ጉልህ ልዩነት ሲፈጥር በአንብቦ መረዳት ችሎታና በማንበብ ግለብቃት እምነት ላይ ጉልህ ልዩነት አልፈጠረም፡፡ በተላውጦዎቹ መካከል ተዛምዶ መኖሩን ለመፈተሽ በተካሄደ የፒርሰን ተዛምዶ ትንተና መሰረት በአስራ አንደኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና በራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም መካከል ተዛምዶ አለመኖሩ(r=.135) ተረጋግጧል፡፡ በአንብቦ የመረዳት ችሎታ እና በማንበብ ግለብቃት እምነት(r=.263) እንዲሁም በራስመር መማር ብልሃቶች እና በተማሪዎች የማንበብ ግለብቃት እምነት መካከል(r=.575) አዎንታዊ ተዛምዶ ተገኝቷል፡፡ በመጨረሻም የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግ አስተያየቶች ተጠቁመዋል፡፡