የወላይታ ብሔረሰብ ተረቶች ክዋኔ ምደባና የይዘት ትንተና

No Thumbnail Available

Date

2024-03

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

ይህ ጥናት "ወላይታ ብሔረሰብ ተረቶች ክዋኔ ፣ ምደባ እና የይዘት ትንተና" ላይ የተሰራ ሲሆን ዓላማውም በወላይታ ብሔረሰብ የሚተረቱ ተረቶችን በመሰብሰብ ክዋኔያቸውን ማሳየት፣ ምደባ ማካሄድ እና የይዘት ትንተና ማድረግ ነው። ተረቶቹ የተሰበሰቡት ከብሔረሰቡ መረጃ አቀባዮች ሲሆን፤ መረጃ ለመሰብሰብ ምልከታ፣ ቃለመጠይቅ እና የተተኳሪ ቡድን ውይይት ዘዴዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። የተሰበሰቡ ተረቶች ክዋኔያቸው ለማሳየት ተሞኳሯል። 67 ተረቶች ከመስክ ላይ የተሰበሰቡ ሲሆን ተግበራዊ ምርምርን (Functional research) እና ክዋኔን ማዕከል ያደረገ (Performance centered approach) ዘዴን በጥምረት በመጠቀም ተጠንተው በገላጭና በይዘት ትንተና ስነዘዴ ተተንትነዋል። በጥናቱ ግኝት ተረቶቹ በአከባቢያዊ መጠሪያቸው "Tumuba woyko Taarikiyaa" እውነተኛ ታሪክ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ እና "Leemisuwaa" የፈጠራ ተብለው ይታወቃሉ። "Tumubaa woyko Taarikiyaa" ተብለው የሚታወቁ ተረቶች በብሔረሰቡ ዘንድ እውነት ናቸው ተብሎ የሚታመንባቸው ሲሆን ፤ ስለብሔረሰቡ አመጣጥ ፣ ብሔረሰቡ ስላካሄዳቸው ጦርነቶች፣ ስለ ቦታ እና ጎሳ ስያሜዎች፣ ስለ የጎሳ መሪዎች ጀግንነት የሚተርኩ ናቸው። "Leemisuwaa" በመባል የሚታወቁት ደግሞ ፈጠራዊ መሆናቸውን የሚታመንባቸው ሲሆን ፤ አእምሮን እያዝናኑ ስነምግባር የሚያስተምሩ ፣ የብሔረሰቡን ባህል፣ ልማድ እና አኗኗር ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚያደርጉ ናቸው። ተረቶቹ ምሁራን በተከተሉት የአመዳደብ ስልት አንጻር ሲታዩ ደግሞ ሌጀንድ፣ ገላጭና ፋቡላ ናቸው። ተረቶቹ በይዘታቸው በአምስት ዋና ዋና ምድቦች የተከፋፈሉ ሲሆን እነሱም ብልህነትን፣ መጥፎ ባህሪያትን፣ ኢፍትሃዊነት፣የእንጀራ እናትን እና ሞኝነትን የሚመለከቱ ናቸው። እኩይ የሚባሉ ተግባራትን በመኮነን እንዳይስፋፉ የሚገታባቸው፣ መልካም የሚባሉትን ደግሞ በመደገፍ ቀጣይነት እንዲኖራቸው በማድረግ ታሪክ እና ባህል የሚተከልባቸው መሆናቸውን ጥናቱ አሳይቷል። ጥቂቶቹ ደግሞ የብሔረሰቡ ባህል የማስቀጠል እና የመተርጎም ጥቅም ያላቸው፣ የብሔረሰቡ አባላት ለሚያነሷቸው ፍልስፍናዊ የሆኑ ጥያቄዎችን የሚሰጥባቸው መሆናቸው ጥናቱ አመላክቷል።

Description

Keywords

Citation