AAU Institutional Repository (AAU-ETD)
Addis Ababa University Institutional repository is an open access repository that collects,preserves, and disseminates scholarly outputs of the university. AAU-ETD archives' collection of master's theses, doctoral dissertations and preprints showcase the wide range of academic research undertaken by AAU students over the course of the University's long history.
How to Submit Your Work
The repository contains scholarly work, both unpublished and published, by current or former AAU faculty, staff, and students, including Works by AAU students as part of their masters, doctoral, or post-doctoral research
- All AAU faculty, staff, and students are invited to submit their work to the repository. Please contact the library at your college.
You may contact digirep@aau.edu.et.with any questions about the repository
Colleges,Institutes in AAU-ETD
Select a college,institute to browse its collections.
Recent Submissions
የድጋፍ ብልሃቶች በአንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ተፅዕኖ፤ በ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2016) ራሔል ሲሳይ ተገኘ; ፕሮፌሰር ተስፋየ ሸዋየ
የዚህ ጥናት ዓላማ የድጋፍ ብልሃቶች የተማሪዎችን በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ መፈተሸ ነበር፡፡ ጥናቱ በዓይነቱ ቅደምተከተላው ቅይጥ (በአመዛኙ መጠናዊ) ሲሆን ቅድመና ድህረ ትምህርት በለቁጥጥር ቡድን ፍትነት ቡድን ፍትነት መሰል ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ በ2015 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር፡ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአድስተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ መረጃዎችን ለመሰብሰብም አንብቦ የመረዳት ችሎታ ፈተናና የግለመር ማንበብ መጠይቅ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ሌላው በአግዥነት ድህረቡድን ተኮር ውይይት ተግባራዊ ሆኗል ፡፡ እንዲሁም ሁለቱ ቡድኖች በተቀመጠላቸው የማስተማሪያ መንገድ መማርቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ምልከታ ተካሂዷል ፡፡በቅድመ ፈተናና መቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድና ነፃ ቲ-ትስቶች የትንተና ስልት እንዲሁም በድኀረ ፈተናና በድኀረ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድ፡ ነፃ ቲ- ትስቶችና በአበር ልይይት ትንተና ስልቶች ተተንትነዋል፡፡ በተጨማሪም ከድህረቡድን ተኮር ውይይት የተገኙት ውጤቶችም እንደሚያመለክቱት በቅድመፈተናና በቅድመየጽሑፍ መጠይቅ ቡድኖች ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሲሆን በድኀረ የጽሑፍ መጠይቅ ገለመር ማንበብ የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥት ቡድኑ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይተዋል (P= <0.05):: ይህም ውጤት በድጋፍ ብልሀቶች መማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና ግለመር ማንበብን ከማሻሻል አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁሟል፡፡ በተገኙት ውጤቶች በመመስረት የመፍትሄ ሀሳቦችና የጥናት ጥቆማዎች ተሰጥተዋል፡፡
የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ፆታተኮር ተዛምዶ፤ በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2016) በለጠ ሕሉፍ ኪሮስ; ፕሮፌሰር ጌታሁን አማረ
የጥናቱ ዋና ዓላማ የስሜታዊ ብልህነት፣ የመጻፍ ችሎታና የመጻፍ ተነሳሽነት ያላቸውን ተዛምዶ ከጾታ አንጻር መፈተሽ ነበር፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም ጥናቱ በተለዋዋጮቹ መካከል ያለውን ዝምድና የማሳየት አላማ ስላለው የተከተለው ዲዛይን (ስልት) ተዛምዷዊ ነበር፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም በደሴ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ደረጃ የሁለተኛው ሳይክል ካላቸው ትምህርትቤቶች መካከል በመምህር አካለወልድ የነበሩ ከ11ኛ G እስከ L ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ (107 ወንዶችና 69 ሴቶች በአጠቃላይ 176) ተማሪዎች በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎቹ፤ የስሜታዊ ብልህነት መጠይቅና የመጻፍ ተነሳሽነት መጠይቅ እንዲሞሉ እንዲሁም የመጻፍ ችሎታን ለመፈተሽ የሚያገለግል የመጻፊያ ርእስ በመስጠት እንዲጽፉ በማድረግ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተገኙት መረጃዎችም በገላጭ ስታትስቲክስ (በአማካይ ውጤትና በመደበኛ ልይይት)፣ የርስበርስና የጠራ ዝምድናቸውን ለመለየት በፒርሰን የተዛምዶ መለኪያ እንዲሁም በከፊል የተዛምዶ መፈተሻ ዘዴ ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤቶች እንዳመላከቱትም በስሜታዊ ብልህነት፣ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታተኮር ዝምድና ታይቷል፡፡ በሌላ በኩል የስሜታዊ ብልህነት ዘርፎች ከመጻፍ ችሎታ ጋር ተዛምዷቸው ከጾታ አንጻር ልዩነት አላቸው፡፡ እንዲሁም የስሜታዊ ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ከተነሳሽነት አንጻር ልዩነት አሳይተዋል፡፡ በመጻፍ ችሎታና በመጻፍ ተነሳሽነት መካከል ጾታን መሰረት አድርጎ ልዩነት አልታየም፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም ጾታ ጣልቃገብ ሲሆን በተላውጦዎቹ መካከል ልዩነት ያሳያል ወደሚልና የስሜት ብልህነትና የመጻፍ ችሎታ ተዛምዶ የሚኖራቸው የመጻፍ ተነሳሽነት ሲኖር ነው ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም አስተያየቶች ተጠቁመዋል፤ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡
ፕሮጀክት ተኮር መማር፣ በመጻፍ ችሎታና ተነሳሽነት ላይ ያለው ተፅዕኖ፤ በ10ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2016) በስመኝ አለምነህ; ጌታሁን አማረ (ፕ/ር); ግርማ ገብሬ (ዶ/ር)
የዚህ ጥናት ዓላማ ፕሮጀክት ተኮር መማር፣ ለተማሪዎች የመጻፍ ችሎታእናተነሳሽነትመሻሻል ያለውን ሚና መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ከግብ ለማድረስምቅድመትምህርትናድኅረ ትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ከፊል ሙከራዊ (quasi-expermental) ስልትተግባራዊ ሆኗል፡፡ በጥናቱ የትግበራ ሂደትም አማራ ክልል በአላማተኮርንሞናተመርጧል፤ ደብረማርቆስ ከተማ የሚገኘው ንጉስ ተክለሃይማኖትአጠቃላይሁለተኛደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ደግሞ በአመቺ ንሞና ከተመረጠበኋላ በዚህትምህርትቤት የሚገኙ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በዕጣ ተመርጠው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ክልሉበዓላማተኮር ንሞና የተመረጠው ጥናቱ አፍፈት ተማሪዎች ላይ የሚያተኩርበመሆኑነው።ትምህርት ቤቱ በአመቺ ንሞና የተመረጠበት ምክንያትምጥናቱከፊልፍትነታዊእንደመሆኑ መጠን ትምህርት ቤቱን እና የአማርኛ ቋንቋ መምህራንን ልዩትብብርእናድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳዮችን የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህም የትምህርትቤቱአስተዳደር፣መምህራንና ተማሪዎች ለጥናቱ ፈቃደኛ በመሆናቸው ነው፡፡ የ10ኛ ክፍልተማሪዎችበዕጣየተመረጡበት ምክንያት ደግሞ ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በስተቀር ጥናቱበ9ኛ፣ 10ኛእና11ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ቢካሄድ በተማሪዎች መረጃ የመሰብሰብሂደትላይችግርአይኖርም ተብሎ ስለታሰበ ነው፡፡ መረጃዎች ከተሳታፊ ተማሪዎችበመጻፍችሎታፈተናእና በመጻፍ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ ተሰብስበዋል፡፡ የተገኙትመረጃዎችምየመተንተኛ ስልቱ እሙኖች በገላጭ ስታቲስቲክስ ከተፈተሹ በኋላ በሙከራናበቁጥጥርቡድኖች መካከል ልዩነት መኖር አለመኖሩን ለመፈተሽ የቅድመና ድኅረትምህርትአጠቃላይ የመጻፍ ችሎታ፣ ንዑሳን ችሎታዎች (ይዘት፣ አደረጃጀት፣ የቃላትአመራረጥናአጠቃቀም፣ የቋንቋ አጠቃቀም እና ስርዓተ አጻጻፍ) አማካይ ውጤቶችና የመጻፍተነሳሽነትየጽሑፍ መጠይቅ አማካይ ውጤቶች በባለብዙ ተላውጦ ልይይትትንተናዘዴ(Multivariate Analysis of Variance, MANOVA) ተሰልተውተተንትነዋል፡፡ በተገኙትውጤቶች መሠረትም፣ የተማሪዎች አጠቃላይ የመጻፍ ችሎታእና ንዑሳንችሎታዎች(ይዘት፣ አደረጃጀት፣ የቃላት አመራረጥና አጠቃቀም፣ የቋንቋ አጠቃቀምእናስርዓተአጻጻፍ) እንዲሁም የመጻፍ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ ውጤቶችየሙከራቡድንተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች አማካይ ውጤቶች ተሽለውና ጉልህ (p<.05) ልዩነትያላቸው ሆነው ተገኝተዋል። በዚህም መሠረት ፕሮጀክት ተኮር መማርየተማሪዎችንአጠቃላይ የመጻፍ ችሎታ እና ንዑሳን ችሎታዎች እንዲሁም የመጻፍተነሳሽነትለማሻሻልሚና እንዳለውና ሚናውም ከፍተኛ እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በመሆኑም፣ የመጻፍትምህርትን በፕሮጀክት ተኮር መማር ተግባራት ማቅረብ እንደሚያስፈልግተጠቁሟል፡፡
የአፍ መፍቻ ቋንቋን በትምህርት መስጫነት የመጠቀም አመለካከቶችና ተግዳሮቶች፤ በስልጤ፣ በሀድያ፣ በከምባታና በወላይታ ቋንቋዎች ተተኳሪነት
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2010) በጎሰው የሽዋስ መንግስት; ፕ/ር ባየ ይማም
የጥናቱ ዋና ዓላማ የአፍ መፍቻ ቋንቋን በትምህርት መስጫነት በመጠቀም ረገድ እየታዩ ያሉ አመለካከቶችንና እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ማጥናት ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም የጥናቱ ንድፍ ውህድ ዘዴን የተከተለ ሲሆን ከውህድ ጥናት ንድፍ ንኡስ ክፍሎችም ባለትይዩ አቻ ውህድ ዘዴ (convergent parallel mixed method) ተግባራዊ የተደረገበት ነው፡፡ ለጥናቱ አስተማማኝ መረጃዎችን ለማግኘትም ቅንጅታዊ የምርምር ዘዴ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ቦታም የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልልን ሲሆን፣ በዚህ ክልል ውስጥ “medium MT exit model”ን (ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል) ከሚጠቀሙ ዞኖች መካከል ስልጤን፣ ወላይታን፣ ከምባታንና ሀድያን በእጣ ንሞና በመምረጥ በጽሁፍና በቃል መጠይቅ መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በእነዚህ ዞኖች ውስጥም በ18 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በስምንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በሁለት የመምህራን ኮሌጆች፣ በስምንት የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች፣ በ12 የዞንና የወረዳ ትምህርት መምሪያዎች ከወላጆች፣ ከመምህራን፣ ከተማሪዎች፣ ከትምህርት ባለሞያዎችና ሀላፊዎች መረጃ ተሰብስቧል፡፡
የተገኙ መረጃዎችም በየንዑስርዕሰ ጉዳዮች ስር ተደራጅተው በገላጭ የትንተና ስልት ተተንትነዋል፡፡ ትንተናውን ለማካሄድም የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት መረጃዎችን ለመተንትን የተዘጋጀው የኮምፒተር ፕሮግራም SPSS /Statistical Package for the Social Science/ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የጥናቱ ግኝቶች እንዳመለከቱትም አብዛኞቹ የጥናቱ ተተኳሪዎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ በመሰጠቱ ደስተኞች እንደሆኑና እንደሚደግፉ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል) ባለፈ ግን ለትምህርት መስጫነት ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ይልቅ እንግሊዝኛን እንደሚመርጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአመለካከቶቹ መንስኤዎችም ባብዛኛው ኢኮኖሚያዊ፣ ስነትምህርታዊና ስነልቦናዊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ሌላው የተግዳሮት ጉዳይ ሲሆን፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋ በማስተማር ሂደት ላይ አብይ ተግዳሮት ሆኖ በዚህ ጥናት የተገኘው ስነትምህርታዊ ተግዳሮት ነው፡፡ የዚህም መንስኤው ባብዛኛው የፖለቲካ ቁርጠኝነት አለመኖር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመጨረሻም ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳት አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተጠቁመዋል፡፡
ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል፣ ማህበራዊ ክሂልና የመፃፍ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለው ሚና (አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ በባሌ ዞን በዘይበላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2009) ግርማ ኃይሉ; ዶ/ር ጌታቸው እንዳላማው
የጥናቱ ዓላማ ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል፣ ማህበራዊ ክሂልና የመፃፍ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለውን ሚና መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱም የተከናወነው አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ በባሌ ዞን በዘይበላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት ነው፡፡ ጥናቱ ከፊል ፍትነታዊነት መሰል የምርምር (Quasi Experimental Research) ስልትን ተከትሏል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎቹም ፈተና፣ የጽሑፍ መጠይቅና ቃለመጠይቅ ናቸው፡፡ የፈተናዎቹ ውጤት በt- ቴስት አማካይነት ተነጻጽሯል፡፡ ውጤቱንም ለማነጻጸር የስህተት ይሁንታ መጠኑ በ0.05 (5%) ባለሁለት ጫፍ ነው፡፡ ከዋናው ጥናት በፊት የቁጥጥር ቡድኑና የሙከራ ቡድኑ የነበራቸውን የቅድመሙከራ የመጻፍ ክሂል ችሎታ ከወዲሁ ለማወቅ የቅድመትምህርት ፈተና ተፈትነዋል፡፡ በቅድመትምህርት የፈተና ውጤታቸውም በአማካይ የቁጥጥር ቡድኑ 52.67 እንደዚሁም የሙከራ ቡድኑ 52.42 ሆኗል፡፡ ይህ ውጤት ሁለቱም ቡድኖች በድህረትምህርት ፈተና የመጻፍ ችሎታቸው ተቀራራቢ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በቀጣይ የቁጥጥር ቡድኑ በተለመደው መንገድ፣ የሙከራ ቡድኑ በትብብራዊ መማር ለአንድ ሴሚስተር ያህል ከተማሩ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች የድህረትምህርት ፈተና ተፈተኑ፡፡ የተሳታፊዎቹ የድህረትምህርት ፈተና ውጤት በአማካይ የቁጥጥር ቡድኑ 53.13፣ እንደዚሁም የሙከራ ቡድኑ 59.38 ነው፡፡ ይህ የውጤት ልዩነት በt-ቴስት ስታትስቲክስ (p= 0.046) ጉልህ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እንደዚሁም ትኩረት በተደረገባቸው ንዑሳን የመጻፍ ክሂሎች ላይ የሙከራ ቡድኑ የቅድመና የድህረትምህርት አማካይ የፈተና ውጤቶች ልዩነት በt-ቴስት ስታትስቲክስ ተሰልቶ ውጤቱም በተሰጡ ቃላትና ሀረጋት ዐረፍተነገር በማዋቀር ንዑስ ክሂል (p= 0.001)፣ የዐረፍተነገር ክፍሎችን ቅደም ተከተል በማስተካከል ንዑስ ክሂል (p= 0.00)፣ ጅምር ዐረፍተነገሮችን በማጠናቀቅ ንዑስ ክሂል (p= 0.000)፣ አያያዥ ቃላትን ተጠቅሞ ዐረፍተነገርን በማደራጀት ንዑስ ክሂል (p= 0.000)፣ ጅምር አንቀጽን በማጠናቀቅ ንዑስ ክሂል (p= 0.00) ጉልህ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን ማህበራዊ ክሂልና የመጻፍ ተነሳሽነትን ለማሳደግ ያለው ተፅዕኖ ምን እንደሚመስል በጽሑፍ መጠይቅና በቃለመጠይቅ አማካይነት መረጃ ተሰብስቧል፡፡ ማህበራዊ ክሂልን በተመለከተ የጽሑፍ መጠይቁን ከሞሉ መላሾች መካከል 81.18% የሚሆኑት ማህበራዊ ክሂላቸው እንዳደገ በምላሻቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህም ውጤት በt- ቴስት ተሰልቶ 4.31 አማካይ ውጤት አሳይቷል፡፡ ይህ ውጤት ደግሞ Peta (2001) ባስቀመጠው ቀመር መሰረት ከፍተኛ ነው፡፡ ከቃለመጠይቁም የተገኘው ምላሽ የጽሑፍ መጠይቁን ውጤት የሚያጠናክር ሆኗል፡፡ እንደዚሁም የመጻፍ ተነሳሽነትን በተመለከተ የጽሑፍ መጠይቁን ከሞሉ መላሾች መካከል 83.83% የሚሆኑት የመጻፍ ተነሳሽነታቸው እንዳደገ በምላሻቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህም ውጤት በt- ቴስት ተሰልቶ 4.4 አማካይ ውጤት አሳይቷል፡፡ አሁንም ይህ ውጤት Peta (2001) ባስቀመጠው ቀመር መሰረት ከፍተኛ ነው፡፡ ከቃለመጠይቁም የተገኘው ምላሽ የጽሑፍ መጠይቁን ውጤት የሚያጠናክር ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ ከጽሑፍ መጠይቁና ከቃለመጠይቁ ከተገኘው መረጃ መገንዘብ የተቻለው ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን ማህበራዊ ክሂልንና የመጻፍ ተነሳሽነትን ለማሳደግ ያለው ተፅዕኖ ጉልህ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ትብብራዊ መማር የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂልን፣ ማህበራዊ ክሂልንና የመፃፍ ተነሳሽነትን ለማሳደግ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የሚመለከታቸው አካላት ለማስተማሪያ ዘዴው ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አጥኚው ይጠቁማል፡፡