የሴቶችና የወንዶች አለባበስና አጊያጊያጥ በመርሐቤቴ ወረዳ

No Thumbnail Available

Date

2024-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት በመርሐቤቴ ወረዳ የሴቶችና የወንድች አለባበስና አጊያጊያጥ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ አልባሳትና ጌጣጌጦች በማጥናት የተጠኚውን ማህበረሰብ ፈጠራ ውጤት፣ እምነት፣ መለያና የአኗኗር ዘይቤን መመርመር የመጀመሪያው አነሳሽ ምክንያት ሲሆን በቁሶቹ ላይ የሚስተዋለውን የለውጥ ምክንያት መፈተሸና ቁሶቹን ለቀጣይ ትውልድ በመረጃነት ሰንድ ማቆየት ደግሞ ሁለተኛው የጥናቱ መነሻ ምክንያት ነው፡፡ የዚህ ጥናት ዓብይ ዓላማ ለጥናት በተመረጠው አካባቢ የሚከወኑ የሴቶችና ወንድች አለባበስና አጊያጊያጥ ፋይዳን መመርመር ነው፡፡ እንዲሁም የቁሶቹን አካላዊ ገፅታ ማሳየት፣ ትዕምርታዊ ትርጉም መግለፅ፣ ለውጥ የተስተዋለባቸውንም ሆነ ያልተስተዋለባቸውን ቁሶቹ መመርመር እና ቁሶቹን ለመጪው ትውልድ እንዲሸጋገሩ ሰንድ ማቆየት የሚሉ ንዐሳን ዓላማዎች አሉት፡፡ ጥናቱ ከዓይነታዊ የምርምር ዘዴአንደ የሆነው ገላጭ የምርምር ስሌትን የተከተለ ሲሆን ቀዳማይና ካልዓይ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀምና ለጥናቱ አስፈላጊ መረጃዎችን በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ የቡድን ውይይት መረጃዎቹ ተሰብስበዋል፡፡ እንዲሁም ዘጠኙ (9) የSchlereth መተንተኛ ሞዴሎች ለመረጃ መተንተኛነት፣መዋቅራዊ ተግባራዊነት እና ለውጥና ቀጣይነት ንድፈ ሃሳቦች ዳግሞ ለጥናቱ መቀንበቢያነት ውለዋል፡፡ በታላሚ ናሙና (Purposive sampling) አመራረጥ ዘዴ መሰረት በወረዳው ከሚገኙ 23 ቀበሌዎች ቁሶቹ እስካሁን ድረስ ሳይበረዙ ያቆዩና ባላቸው የአየር ንብረት ልዩነት መሰረት አምስት ቀበሌዎች፣ እንዲሁም ከወጣት እስከ አዛውንት ያለና ባህሉን በደንብ የሚያውቁ 23 ወንዶችና 13 ሴቶች በድምሩ 36 መረጃ አቀባዮች በሀገር ሽማግሌዎችና በባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት መረጃ ሰጭነት ተመርጠዋል፡፡ በተመረጡ 22 አልባሳት እና 24 ጌጣጌጦች እንዲሁም 9 የፀጉር አሰራር ዓይነቶች ላይ ትንተና ተደርጓል፡፡ ጥናቱ በማህበረሰቡ የሚታወቁ አልባሳትና ጌጣጌጥ የትኞቹ ናቸው? የአለባበስ ሥርዓታቸው ምን ይመስላል? የመልበሻ አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? ቁሶቹ በማን መቼ እንዴትና ለምን ይሰራሉ? በየዕዴሜ ደረጃቸው ያለ አልባሳትና ጌጣጌጦች መለያቸው ምንድነው? በአልባሳቱና ጌጣጌጡ ላይ ለሚታዩ ለውጦች ምክንያታቸው ምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎችን መልሷል፡፡ ከዚህ አንፃር የሚከተለትን ነጥቦች በጥናቱ ግኝት የተመላከቱ ናቸው፡፡ እነሱም የማህበረሰቡ አልባሳትና ጌጣጌጦች በአካባቢው ከሚገኙ ጥሬ ዕቃዎችና የፊብሪካ ምርት ከሆኑ ግብዓቶች በአካባቢው ሸማኔ፣ ልብስ ሰፉዎች፣ በእደ ጥበብ ሙያተኞች የሚጋጁና ገበያው በሚያቀርባቸው መሰረት የሚገኙ ናቸው፡፡ ከአገልግሎት አኳያ የለባሹን ደህንነት የማስጠበቅ፣ ውበትን የማጉላት፣ ፆታን፣ ማንነትን፣ ዕድሜን፣ ጀግንነትን ኃይማኖትን፣ ማህበራዊ ግንኙነትን፣ ማህበራዊ ደረጃዎችን የሚገልፁ ሲሆን ከመዋቅር አኳያ ደግሞ ቁሶቹ ሰርዓተ ማህበሩ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የቁሶቹ ተምሳሌታዊ ትርጉም የማህበረሰቡን አመለካከት፣ ፍልስፍና፣ እውቀት፣ እምነት፣ ማንነት፣ ማህበራዊ ደረጃ፣ ውበት፣ ፆታ ወዘተ ጉዳዮችን የሚገልፁ ሲሆኑ አሰራራቸው ደግሞ ጥበባዊ፣ ታሪካዊ፣ አካባቢያዊ፣ መዋቅራዊ፣ ማህበረሰባዊ ወዘተ መለያ ያላቸው ናቸው፡፡ እንዲሁም ከለውጥና ቀጣይነት አኳያ ምንም ያልተለወጡ፣ በከፉል የተለወጡ፣ ሙሉ ለሙሉ የተለወጡ ቁሶች መኖራቸው የጥናቱ ግኝት ያመላክታል፡፡ በዚህም መነሻነት የማህበረሰቡ ማንነት መገለጫ የሆኑትን ቁሶች የማልማትና ጠቃሚነታቸውን የማጉላት ስራ በድግግሞሽ ቢሰራ ማህበረሰቡን ለማስተዋወቅ፣ ማንነቱን በዘላቂነት ይዞ ለማስቀጠልና ከባህሉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ የሚያደርገው ይሆናል የሚል የይሁንታ ሃሳብ በማቅረብ ጥናቱ ተጠናቋል፡፡

Description

Keywords

Citation