በ2012 ዓ.ም በፋና“ጉዞ ኢትዮጵያ”ና በኢቢኤስ “ኢትዮጵያን እንወቅ” ሳምንታዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ውስጥ የተካተቱ ፎክሎራዊ ጉዳዮች ትንተና
No Thumbnail Available
Date
2024-08
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
ይህ ጥናት “በ2012 ዓ.ም በፋና“ጉዞ ኢትዮጵያ”ና በኢቢኤስ “ኢትዮጵያን እንወቅ” ሳምንታዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ውስጥ የተካተቱ ፎክሎራዊ ጉዳዮች ትንተና” በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ተተኳሪ በሆኑት ሁለቱ የቴሌቨዥን ተቋማት ሳምንታዊ ፕሮግራሞች ውስጥ የትኞቹ የፎክሎር ዘውጎች ተካተዋል?፤ ፎክሎራዊ ዘውጎቹ ለቴሌቭዥን ጣቢያዎቹ ምን ፋይዳ አላቸው?፤ ለጥናቱ በተለዩት ጣቢያዎች የፎክሎር መካተት ለመስኩ የምርምር ዘርፍ የሚኖረው ፋይዳ ምንድን ነው?። ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተችሏል፡፡ጥናቱ የተከተለው አይነታዊ የአጠናን ዘዴን ሲሆን፤በሰነድ ፍተሻና በቪዲዮ ምልከታ የተሰበሰበው መረጃ በገለጻና በትረካ ስልት ትንተና ተደርጎበታል፡፡በመጨረሻም አራቱ የፎክሎር ዘውጎች ሥነ-ቃል፣ ሀገረሰባዊ ልማድ፣ ሀገረሰባዊ ትውን ጥበብና ቁሳዊ ባህል በተተኳዋሪ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መካተታቸው በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ ፎክሎሮቹ የሚያስገኟቸውን ፋይዳዎች በተመለከተም ማሕበረሰብን ከማስተማር፣ከቱሪዝም፣ከቴሌቭዥን ፕሮግራም፣ከጥናትና ምርምር፣ከመቀስቀስና ከማንቃት አኳያ አይተኬ ሚና ያላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡ እንዲሁም የትረካ ስልትን የማሳመር፣የፕሮግራም ተደማጭነትን የማሳደግ ሚና ያላቸው መሆኑ፤ ለማስታወቂያ ስራዎች ተደራሽነትና አይረሴነት የሚጫወቱት ሚና መኖሩ፣ የታሪክ ጭብጥን ለማጉላትና ገጸ-ባህርያትን ለማቅረብም የማይናቅ ድርሻ ያላቸው መሆኑ፣ አድማጭና ተመልካቾች ለጣቢያዎቹ አድማጮችና ተመልካች ደንበኞች ሆነው እንዲቀጥሉ የማድረግ ሚና እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡በመጨረሻም አጥኚው ፎክሎር ለማኅበረሰብ የሚያሰገኛቸው ጠቀሜታዎች ዘላቂነት ይኖራቸው ዘንድ በዚህ ጥናት ተተኳሪ የሆኑትን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች የተሰማሩ የፕሮግራም አቅራቢ ጋዜጠኞች ፎክሎሮችን በመዘገብና ሰንዶ በማቅረብ ተግባር በመትጋት ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ማህበረሰባዊ እሴቶችን ለትውልድ ለማሻገር ቢሞክሩ በሚል የመፍትሄ ሐሳቡን ለመጠቆም ሞክሯል፡፡