በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎች የራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም፣ የማንበብ ግለብቃት እምነት እና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ጾታ ተኮር ተዛምዶ፤ በተመረጡ የአስራአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2024-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

Addis Ababa University

Abstract

በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ፣ የማንበብ ግለብቃት እምነትና የራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም መካከል ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ነው፡፡ የተዛምዶ ፍተሻውን ለማድረግ ጥናቱ ተዛምዷዊ የምርምር ንድፍን የተከተለ ሲሆን በአዲስ አበባ አስተዳደር በሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የአማርኛ ቋንቋ አፍፈትየሆኑ የአስራአንደኛ ክፍል ተማሪዎች እኩል እድል ሰጭ ንሞና ዘዴ በመጠቀም የጥናቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡ የአንብቦ መረዳት ችሎታ መለኪያ ፈተና፣ የማንበብ ግለብቃት እምነት መጠይቅ እና የራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም መጠይቅ በመጠቀም ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን መሰብሰብ ተችሏል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ ከተጠናቀረ በኋላ ገላጭና ተንባይ ስታትስቲክሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለጥናቱ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የሚያስችል የመረጃ ትንተና ተካሂዷል፡፡ ከመረጃ ትንተናው በተገኘው ውጤት መሰረትየ11ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ በምን ደረጃ ላይ እንደሆነ ለሚጠይቀው የጥናቱ ጥያቄ የፈተናው አማካይ ውጤት(56.65%) እና የውጤት ስርጭቱ አብዛኞቹ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው መካከለኛ እንደሆነ አሳይቷል፡፡ ጾታ በተላውጦዎቹ ላይ ያሳየውን ልዩነት ለማወቅ በተደረገ የቲ ቴስት ፍተሻ ውጤት መሰረት ጾታ በራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም ላይ ብቻ ጉልህ ልዩነት ሲፈጥር በአንብቦ መረዳት ችሎታና በማንበብ ግለብቃት እምነት ላይ ጉልህ ልዩነት አልፈጠረም፡፡ በተላውጦዎቹ መካከል ተዛምዶ መኖሩን ለመፈተሽ በተካሄደ የፒርሰን ተዛምዶ ትንተና መሰረት በአስራ አንደኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና በራስመር መማር ብልሃቶች አጠቃቀም መካከል ተዛምዶ አለመኖሩ(r=.135) ተረጋግጧል፡፡ በአንብቦ የመረዳት ችሎታ እና በማንበብ ግለብቃት እምነት(r=.263) እንዲሁም በራስመር መማር ብልሃቶች እና በተማሪዎች የማንበብ ግለብቃት እምነት መካከል(r=.575) አዎንታዊ ተዛምዶ ተገኝቷል፡፡ በመጨረሻም የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግ አስተያየቶች ተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

Citation