ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
No Thumbnail Available
Date
2024-12
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
Addis Ababa University
Abstract
ይኽ ጥናት ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በሚል የተጠና ነው፡፡የጥናቱ መረጃዎች የተሰበሰቡት በዋናነት በምልከታ፣የቅዱሳት ሥዕላት ባለሙያ ጋራ በቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ቅዱሳት ሥዕላት በተመለከተ የተጻፉ ጋዜጣ፣መጽሔት እና መጻሕፍትን በማንበብ፣ የሥዕል ዐውደ ርእይና ዐውደ ጥናት ላይ በመሳተፍ፣በየመደብሩ የሥዕላት መሸጫ ቦታዎች ላይ ምልከታ በማድረግ እንዲኹም በየአብያተ ክርስቲያኑ የሚገኙትን ቅዱሳት ሥዕላትን በመመልከት ነው፡፡በነዚኽ ዘዴዎች የተሰበሰቡት መረጃዎች ጥናቱ ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ያለውን አገልግሎትና የአሣሣል ሥርዐት ለማሳየት ዐላማ አድርጎ በመነሣቱ የአሣሣል ሥርዐቱን ለማሳየት ተግባራዊ እና ሥነ-ልቡናዊ ንድፈ ሐሳብን ተጠቅሟል፡፡በተግባራዊ እና ሥነ-ልቡናዊ ንድፈ ሐሳብ አቅጣጫ መሠረትም በገላጭ ምርምር ስልት መረጃዎች ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ቅዱሳት ሥዕላት የሚያስገኙት ጥቅም፣የቅዱሳት ሥዕላት አሣሣል ታሪካዊ አመጣጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የኾነ ትእዛዝ ያለው መኾኑንና ከጥንት ጀምሮ ሥዕሎቹ ትውፊትን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጁ ሲኾን አኹን ባለንበት ዘመን ግን ትውፊትን ያልጠበቁ እና የእምነቱን አስተምህሮ የማይገልጹ ቅዱሳት ሥዕላት መኖራቸው በጥናቱ ላይ ተረጋግጧል፡፡ቅዱሳት ሥዕላት ከመሣላቸው በፊት ከሠዓሊው የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች አሉ፡፡እነሱም፡-ንስሓ መግባት፣ሥዕላቱ የሚዘጋጁት በእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ጸሎት ማድረግ፣ሥዕሉን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች ማስባረክ እንደሚያስፈልግ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ሠዓሊው መሠረታዊ የኾነ የመንፈሳዊ ዕውቀት ያለው፣ሥዕሎችን የመመልከት፣ሥዓሎቹ የሚሣሉት ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ መነሻ በማድረግ በመኾኑ ገድላትን ስንክሳርን የማንበብ ልምድ ያለው መኾን እንዳለበት በዚኽ ጥናት ተረጋግጧል፡፡ኾኖም ግን አኹን ባለንበት ዘመን ይኽ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደማይዘጋጅ እና የቤተ-ክርስቲያን አሠሪ ኮሚቴዎችም ሥዕሎችን እንዲሣሉ ማድረጋቸውን እንጂ ትውፊቱን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላት እንዲዘጋጁ እንደማያደርጉ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ከሥዕሎቹ ጭብጥ ጋራ የማይዛመዱ ቅዱሳት ሥዕላትንም በስህተት የሚጠሩበት ሥያሜ እና ታሪካቸው የሚለያዩ መኾናቸውን በዚኽ ጥናት ተለይቷል፡፡ይኸውም አኹን ባለንበት ዘመን ኪዳነ ምሕረት ተብለው የሚታዩት ሥዕሎች የማርያምን ንግሥና ስትቀበል የግብጽ የመገለጧ ማርያም የሚያሳዩ ናቸው እንጂ ቃልኪዳን ስትቀበል የሚያመለክት አለመኾኑንና ትክክለኛውን የኪዳነ ምሕረት ምሥል የትኛው እንደኾነ ተለይቷል፡፡በጥንት ዘመን የሥዕል ትምህርት የቀድሞ አባቶቻችን ከፍተኛ የኾነ ትምህርተ ክርስትና የነበራቸው በመኾኑ የሚሥሏቸው ሥዕሎቹ ከትምህርተ ክርስትና ጋራ እንደማይጋጩ
vi
በአኹኑ ዘመን ግን የሚታዩት ሥዕሎች መሠረታዊ የኾኑ የእምነቱን አስተምህሮ የማይገልጹ እንደኾኑ ተረጋግጧል፡፡ቅዱሳት ሥዕላት በተመለከተ ትምህርት እየተሠጠ እንዳልኾነ፣በየቤተ ክርስቲያናቱ ሰንበት ትምህርት ቤትና በየዐውደ ምሕረቱ ላይ የተሰበኩ ትምህርት አለመኖሩን፣በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ የተጻፉ መጻሕፍት ጥቂት መኾናቸውን በተጨማሪም በመንፈሳዊያት ዩኒቨርስቲዎች ሥዕል ራሱን ችሎ ትምህርት እየተሠጠ አለመኾኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡የሥዕል ትምህርት ቤቶች አኹን እያስተማሩ ያሉት በማኅበረ ቅዱሳን ሥነ-ጥበብ ክፍል፣በሐመረ ብርሃን፣በገርጂ ማርያምና እግዚአብሔር ምስሌነ ደብረገሊላ ብዙ ሥራ እየሠሩ እንደሚገኙ ታይቷል