Amharic Language, Literature and Folklore
Permanent URI for this collection
Browse
Browsing Amharic Language, Literature and Folklore by Title
Now showing 1 - 20 of 443
Results Per Page
Sort Options
Item ሀገረሰባዊ የአስተዳደር ስርአትና የግጭት አፈታት ዘዴዎች በአኝዋ ብሔረሰብ(AAU, 1999-07) ኃይሉ, አበበ; አዘዘ, ፈቃደ (ዶ/ር)ሀገረሰባዊ የአስተዳደር ስርአትና የግጭት አፈታት ዘዴዎች በአኝዋ ብሔረሰብItem ሀገረሰባዊ የዕፅዋት መዴሀኒቶች እውቀት፣አዘገጃጀት እና አሰጣጥ በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢዋ “ከመድሀኒት አዋቂዎች አንጻር”(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2012-05) ደባይ, ብርቱካን; አረዶ, ደ/ር የኔዓለምይህ ጥናት “ሀገረሰባዊ የዕፅዋት መዴሀኒት እውቀት፣አዘገጃጀት እና አሰጣጥ በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢዋ” በሚሌ ርዕስ የቀረበ ሲሆን የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት የአካባቢው ማህበረሰብ ሀገር በቀሌ የህክምና እውቀትና ሌማዴ መመርመር ነው፡፡ የምርምሩ ዋና አሊማ የማህበረሰቡን ሀገረሰባዊ የዕፅዋት መዴሀኒቶች እውቀት፣ አዘገጃጀት እና አሰጣጥ በመመርመር ባህሊዊ ሌማደን ገሌጾ ማሳየት ሲሆን በአካባቢው በባህሊዊ ህክምና የሚፇወሱ በሽታዎችን መሇየት፣ ሇሀገረሰባዊ መዴሀኒት መቀመሚያ የሚውለ ግብዓቶች ከምን ከምን እንዯሚገኙ መግሇጽ፣ የመዴሀኒቶቹን አዘገጃጀት እና አጠቃቀም ማሳየት እና በአካባቢው የሚገኙ ሀገረሰባዊ ሀኪሞች የህክምና እውቀት ተስተሊሌፍ ሂዯት መግሇጽ የሚለ ዜርዜር አሊማዎች አለት፡፡ እነዙህን አሊማዎች ከግብ ሇማዴረስ የመስክ መረጃ፤በምሌከታ እና በቃሇ መጠይቅ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዳዎች ተሰብስበው በመቅረጸ ዴምፅ፣በማስታወሻ፣ በቪዱዮ ካሜራ እና በፍቶ ተሰንዯዋሌ፡፡ የመስክ መረጃ ሰጪዎች ከክርስትና እምነት ተከታዮች እና ከእስሌምና እምነት ተከታዮች የተውጣጡ ሲሆኑ ከሀገረሰብ ሀኪሞች፣ ከባህሌ መዴሀኒት ተጠቃሚዎች፣ ከመናዊ ሀኪሞች እና ከሀገር ሽማግላዎች፤በአሊማ ተኮር፣ አመቺ እና ጠቋሚ የናሙና አመራረጥ ስሌት ተመርጠዋሌ፡፡ ከቁሌፌ እና ከአጋዥ መረጃ አቀባዮች የተሰበሰቡ መረጃዎች አይነታዊ የምርምር ስሌት በመጠቀም በይትና በምዴብ ተዯራጅተዋሌ፡፡ እነዙህ መረጃዎች የተግባራዊነት ንዴፇ ሀሳብ፣ ክዋኔ ተኮር እና የጤና ሥነ ምህዲር (Medical Ecology) ንዴፇ ሃሳቦችን መሰረት በማዴረግ በገሊጭ እና ተንታኝ ስሌት ተተንትነው ቀርበዋሌ፡፡ በትንታኔው መሰረት ሇጥናት የተመረጠው አካባቢ ቆሊማ መሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ ሇተሇያዩ በሽታዎች እንዱጋሇጥ ምክንያት መሆኑን ጥናቱ አሳይቷሌ፡፡ በአብዚኛው የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚያጠቁ በሽታዎችም፤የቆሊ ቁስሌ፣ አሌማዜ ባሇጭራ፣ ችፋ፣ ሊሽ፣ በእባብ መነዯፌ፣ ሆዴ ቁርጠት (ተቅማጥ)፣ ኪንታሮት፣ ምች፣ አይሬ፣ እከክ (ቁስሌ) እና የወፌ በሽታ መሆናቸው ተዯርሶበታሌ፡፡ በአካባቢው ያለ የሀገረሰብ ህክምና ባሇሙያዎች በሀይማኖት፣ በብሔር እና በአመሇካከት የተሇያዩ መሆናቸውንም ተመሌክቷሌ፡፡ እነዙህ ባሇሙያዎች በእይታ፣ በመነካካት እና በጠየቅ በሽታን እንዯሚሇዩ በጥናቱ ተጠቁሟሌ፡፡ በዙህ መሌኩ ከተሇዩ በኋሊ በሽታዎቹን ሇማከም በአብዚኛው በአካባቢው ያለ ዕፅዋት ጥቅም ሊይ እንዯሚውለ ጥናቱ አሳይቷሌ፡፡ የመዴሀኒቱ አሰባሰብ ፣ አገጃጀት እና አሰጣጥ ስርዓቱም እንዯ ባህሌ ሀኪሙ እውቀት፣ እምነት፣ ሌምዴ እና አመሇካከት፤ ሰዓትና ቀናት ተመርጠው እንዱሁም የተሇያዩ ክንዋኔዎች ከተከናወኑ በኋሊ፤የተሰበሰቡት ዕፆች በመፌጨት፣ በመውቀጥ፣ በመቀቀሌና በማዴረቅ፤በሚጠጣ፣ በሚታሰርና በሚቀባ መሌክ ተጋጅተው የሚሰጥ መሆኑ ተገሌጧሌ፡፡ በጥናቱ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፌልችም በሀይማኖት፣ በብሔር እና በአመሇካከት የተሇያዩ መሆናቸውንና ወዯ ባህሌ ሀኪሞች ሇመሄዴ ሌዩነቱን መሰረት እንዯማያዯርጉ ተረጋግጧሌ፡፡ ይህም በመሆኑ ከተሇያየ ብሔረሰብ፣ ሀይማኖት እና አመሇካከት ያሇው የማህበረሰብ ክፌሌ ጋር በመገናኘት ማህበራዊ ተግባቦትን መፌጠር መቻሊቸውን ጥናቱ አረጋግጧሌ፡፡ በተጠኝው ማህበረሰብ፤በመናዊ ሀኪሞች መዴሀኒት ያሌተገኘሊቸው በሽታዎች በባህሊዊ ህክምና የሚዲኑ መሆናቸው፣ ህክምናውን በፌጥነት ማግኘት የሚችለ መሆኑ እና እርስ በርስ ያሊቸው ቅርርብ የጠበቀ መሆኑ፤ከመናዊ ህክምና ይሌቅ ባህሊዊ ህክምናው ተመራጭ እንዱሆን አዴርጎታሌ፡፡ በአጠቃሊይ ሀገረሰባዊ ህክምና የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤንነት በማስጠበቅ፣ ማህበራዊ መስተጋብር በመፌጠር፣ አርስ በርስ ወዲጅነትን እና አንዴነትን በመገንባት ረገዴ ከፌተኛ እስተዋፅዖ ያሇው መሆኑን ሇማወቅ ተችሎሌ፡፡ በመሆኑም ጉዲዩ የሚመሇከተው የወረዲው የጤና ጽ/ቤት፣ የባህሌና ቱሪዜም ቢሮ እንዱሁም ግሇሰቦች የሀገረሰባዊ ህክምና እውቀቱን ርፇ ብዘ አገሌግልት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀገር በቀሌ የሆነው እውቀት ተጠብቆ እንዱቆይ እና ሇትውሌዴ እንዱተሊሇፌ በማዴረግ የዴርሻቸውን ሉወጡ ይገባል፡፡Item ሂደተ ዘውጋዊ ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ እና አመሇካከት ሊይ የሚኖረው ተፅህኖ፣ በምዕራብ ሸዋ አካባቢ በኤጀሬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት(Addis Ababa University, 2009-06) ለማ, ተካልኝ; ከበደ, ሴይመየዚህ ጥናት ዋና ዓሊማ የሂዯተዘውጋዊ የመፃፌ ትምህርት አቀራረብ የተማሪዎችን ዴርሰት የመፃፌ ችልታ ሇማሳዯግ ያሇውን አሰተዋፅኦ መመርመር እና እንዱሁም ተማሪዎች በዚህ ዘዳ ከተሇማመደ በኋሊ በመፃፌ ሊይ ያሊቸው አመሇካከት ሇውጥ ያሳ እንዯሆነ ፇትሿሌ:: ይህ ጥናት የሂዯተዘውጋዊ ዘዳ ተማሪዎች ዴርሰት የመፃፌ ችልታቸውን የሚያሻሽለበትን ስሌት የተከተሇ ነው:: ከዚህ አጠቃሊይ ግብ ሇመዴረስ መጠናዊና ዓይነታዊ የምርምር ዘዳዎች ሊይ የተመሰረተ ሆኖ ገሊጭ የመረጃ አተናተን ስሌትን ተግባራዊ አዴርጓሌ:: የጥናቱ ተሳታፉዎች በምዕራብ ሸዋ ዞን ከኤጀሬ ሁሇተኛ ዯረጃ የ9ኛ ክፌሌ ተማሪዎች መካከሌ ሁሇት ክፌልች 9ኛ “A” እና “F” በአጋጣሚ የንሞና ስሌት የተመረጡ ሲሆን ከነዚህ ሁሇት ክፌልች አንዯኛው በሂዯተዘውጋዊ ዘዳ የተማረው የተማርው ቡዴን ሲሆን ሁሇተኛው ዯግሞ በሌማዲዊው የማስተማር ዘዳ የተማረው የቁጥጥሩ ቡዴን ነው:: ሇእያንዲንደ ቡዴን ሇአስራሁሇት ሳምንታት ትምህርቱ ተሰጥቷሌ:: ተማሪዎቹ ትምህርቱን ከመማራቸው በፉትና ትምህርቱን ከተከታተለ በኋሊ ፇተና ተሰጥቷቸዋሌ:: እንዯዚሁም እነዚህን ሁሇት ክፌልች የሚያሰተምር አንዴ መምህር በተመሳሳይ የንሞና ዘዳ ተመርጧሌ:: ሇዚህ ጥናት ዋነኛው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ሆኖ ያገሇገለት ቅዴመና ዴህረ ፇተናዎች ናቸው:: በፇተናዎች የተሰበሰበው መረጃ ሲታይ በቅዴመ ፇተና ወቅት የቁጥጥሩና የሙከራ ቡዴኑ ተማሪዎች አማካይ ውጤት በ t- ቴስት ቀመር ተሰሌቶ በተገኘው ውጤት መሰረት ጉሌህ ሌዩነት አሌታየበትም:: በላሊ በኩሌ በዴህረ ፇተና ወቅት የቁጥጥሩና የሙከራ ቡዴኑ ተጠኚዎች አማካይ ውጤት ጉሌህ ሌዩነት ታይቶበታሌ:: በተጨማሪም የፅሁፌ መጠይቅ በአጋዥነት በመረጃ መሰብሰቢያነት ጥቅም ሊይ ውሎሌ:: በፅሁፌ መጠይቅ በተሰበሰበው መረጃ እንዯታየው በአጠቃሊይ ዴርሰት በመፃፌ ረገዴ የሙከራ ጥናቱ ከመካሄደ በፉትና ጥናቱ ከተካሄዯ በኋሊ የጥናቱ ተተኳሪዎች አመሇካከት ሲነፃፃፀር የሙከራ ቡዴኑ ተማሪዎች አዎንታዊ አመሇካከት ፇጥረዋሌ:: በዚህ ጥናት የታየው ግኝት በሂዯተዘውጋዊ ዘዳ የተማሩ ተማሪዎች በሌማዲዊው ዘዳ ከተማሩት ጋር ሲነፃፀሩ የመፃፌ ችልታቸው እና ሇመፃፌ ክሂሌ ያሊቸው አመሇካከት የተሻሇ ሆኗሌ:: በመጨረሻም ቀጣይ ጥናቶች ይኸውም:- አንዴ ዓይነት ዯረጃ ባሊቸው፣ ዝቅተኛ ውጤት ባሊቸው እና በዝቅተኛ የክፌሌ ዯረጃ በሚገኙ ተማሪዎች ሊይ የሂዯተዘውጋዊ የመፃፌ ተምህረት አቀራረብ ተግባራዊ ቢሆን ሉመጣ የሚችሇው ተፅህኖ ቢመረመር የሚሌ አስተያየት ቀርቧሌ::Item ሂደት ተኮር አቀራረብ የተማሪዎችንት የመጻፍ ችሎታ እና ተነሳሽነት ለማሻሻል ያለው አሰተዋጽኦ (በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጅማ ወለኔ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-07) የሰራሽ አደራው; ግርማ ገብሬ (ዶ/ር)ይህ ጥናታዊ ጽሁፋ ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሳው የሂደት ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችየመጻፍ ክሂል ችሎታ እና ተነሳሽነት ከማሻሻል አንጻር ያለውን አስተዋጽኦ ለመፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱም ከፊል ሙከራዊ ሲሆን፣ የተካሄደውም በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሚገኘው በጅማ ወለኔ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል የ9ኛክፍል ተማሪዎች በአመቺ የናሙና ስልት ከተመረጡ በኋላ፣ በተራ ዕጣ የናሙና አመራረጥ ስልት በአንድ መምህር የሚማሩ ሁለት ምድብተማሪዎች ተለይተው በቅድመ ፈተናው ሂደት ተሳትፈዋል፡፡ ከሁለቱ ምድቦች መካከል በቅድመ የመጻፍ ክሂል ፈተና ተቀራራቢ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሁለት ምድቦች ከተለዩ በኋላ በተራ የዕጣ ናሙና ስልት አንዱ የሙከራ ሌላኛው የቁጥጥር ቡድን ሆኖ በጥናቱ ውስጥ እንዲሳተፍ ተደርጓል፡፡ በመረጃ መስብሰቢያ ዘዴነት ፈተና እና የጽሑፍ መጠይቅ ሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ፈተናው፣ ቅድመ እና ድኅረ ፈተናን ያካተተ ነው፡፡ ቅድመ ፈተናው የተሰጠበት ዓላማ ተማሪዎች ከሙከራ ጥናቱ በፊት ያላቸውን የመጻፍ ክሂል ውጤት ተቀራራቢ መሆን አለመሆኑን ለመፈተሽ ሲባል ነው፡፡ የድኅረ ፈተናው ዓላማ ደግሞ የሙከራ እና የቁጥጥር ቡድን ሆነው የተመረጡት ተማሪዎች በተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎች የመጻፍ ክሂልን ከተማሩ በኋላ በመካከላቸው ጉልህ ልዩነት መኖር አለመኖሩን ለመፈተሽ ነው፡፡ በሌላ በኩል የጽሑፍ መጠይቅ የተማሪዎቹን የመጻፍ ተነሳሽነት ለመለካት የቀረበ ነው፡፡ ተተኳሪ የሆኑት ተማሪዎች ከመጻፍ ልምምዱ በፊት (ቅድመ ጽሑፍ መጠይቅ) እና በኋላ (ድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ) እንዲሞሉ ተደርጓል፡፡ በቅድመ ፈተና እና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በዳግም ናሙና ቲ-ቴስት ትንተና ዘዴ እንዲሁም በድኅረ ፈተና እና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በባዓድ ናሙና ቲ-ቴስት ትንተና ዘዴ እንዲሰሉ ተደርጓል፡፡ የተገኙት ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በቅድመ ፈተና እና በቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች የተመዘገበባቸው ቡድኖች፣ በድኅረ ፈተና ይዘት፣ አደረጃጀት፣ ቃላት፣የቋንቋ አጠቃቀም እና ሥርዓተ አጻጻፍ እና በድኅረ የጽሑፍ መጠይቅ ተነሳሽነት የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይተዋል።ይህም ውጤት የሂደት ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ችሎታ እና ተነሳሽነት ከማሻሻል አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ሊጠቁም ችሏል፡፡ ከመጻፍ ክሂልችሎታ እና ተነሳሽኘት አንጻር የተገኙት ውጤቶች ላይ በመመስረት ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ከተደረገ በኋላ፣ የሂደታዊ ዘዴ የመፃፍ ትምህርት አቀራረብ የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል ለማዳበር ጥሩ አስተዋፅዖ ያለው መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ መምህራን ጥሩ ግንዛቤ ኖሯቸው በክፍል ውስጥ በተገቢው ሁኔታ መተግበር እንዲችሉ የሚያደርጋቸው በቂ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የመፍትሄ ሀሳቦች እና የጥናት ጥቆማዎች እንዲቀርቡ ተደርጓል።Item ሂደት ወዘውግ ተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና (በአጋሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2023-09) አካል ግርማ; ግርማ ገብሬ (ዶ/ር)የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የዘጠነኛ ክፍል በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሂደት ወዘውግ ተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ላይ ያለው ሚና ፈትሿል፡፡ ይህን አላማ ከግብ ለማድረስ ሙከራ ቢጤ የጥናት ንዴፍ (Quasi experimental research design) በመጠቀም ለምፈተሸ ይቻል ዘንድ ተማሪዎችን በቁጥጥር እና በሙከራ ቡድን በሁለት በመክፈል ጥናቱ ተካሂዷል፤ በመሆኑም ምሁራን ባነሷቸው ሀሳቦች በማጎልበት በዋነኝነት ፈተና በደጋፊነት ደግሞ የፅሁፍ መጠይቅና ምልከታ በመጠቀም መረጃ በመሰብሰብና መረጃውን የቲ-ቴስት የመተንተኛ ዘዴ በመጠቀም በአግባቡ ተደራጅተው ትንተና የተደረገባቸው ናቸው፡፡ የተገኘውም ውጤት እንዳመለከተው በሂደታዊ ዘውግ የተማሩት የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች በልማዳዊው (በመርሃ ትምህርቱ) ከተማሩት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በተሻለ የመጻፍ ክሂላቸው እንዳሻሻሉ ፣ በቂ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ፣ የመጻፍ ተሳትፏቸው የተሻሻለ መሆኑን አመልክቷሌ ፡፡ በመሆኑም ሂደታዊ ዘውግ የመፃፍ ማስተማሪያ ዘዴን በመጠቀም የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂልን ማሻሻል፣ በቂ ደረጃ ላይ ማዴረስና ተሳትፎቸውን መጨመር ተማሪዎችን ለደረጃቸው የሚመጥን የመጻፍ ክሂል ችሎታ ላይ ማዴረስ ይቻላል የሚል አስተያየት ላይ ተደርሷሌ ፡፡ በዚህም በወጉ ያረሰ እንደልቡ ጎረሰ እንደሚባለው መምህራን ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን በተገቢ ሁኔታ አዲዱስ አሰራሮችን በመጠቀም በተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ላይ መጠቀም ከቻሉ የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በጥናቱ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡Item ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል በተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብ እና አደረጃጀት ከመርሀ-ትምህርቶቹ ጋር ያላቸውን ተጣጥሞሽ መፈተሽ(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2022-08) ደስታ አበጋዝ; ዶ/ር ዳዊት ፍሬህይወትየዚህ ጥናት ዋና አላማ በ2014 ዓ.ም. በ ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አማካኝነት በታተሙት የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብ እና አላረጃጀት ከመርሀ-ትምህርቶቹ ጋር ያሊቸውን ተጣጥሞሽ መፈተሸ ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት ሰነድ ፍተሻ የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ በመሆኑ የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል መማሪያ መጻህፍትና የመምህሩ መምሪያ እንዲሁም ለደረጃው የተዘጋጁ መርሀ-ትምህርቶች በመረጃ ምንጭነት አገልግለዋል፡፡ ጥናቱም ቅይጥ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በሰነድ ፌተሻ የተገኙ መረጃዎች በክለሳ ድርሳን ከተነሱ ንዴፈ-ሃሳቦች አኳያ በገላጭ የምርምር ስልት ተተንትነዋል፡፡በተተኳሪዎቹ መጻህፌትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ ያለ የሰዋስው ይዘቶች በመርሀ-ትምህርቱ ውስጥ ከተካተቱት ይዘቶች ጋር በአብዛኛው የሚጣጣሙ መሆናቸውን ከሰነድ ፍተሻው ለማረጋገጥ ተችሎል፡፡ በተተኳሪዎቹ ሰነድች ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች ከሰዋስው ትምህርት አቀራረብ መርሆዎች አኳያ ሲፈተሹ በአብዛኛው ግልጽ፣ ትክክለኛ፣ተገቢነትና ተመጣጣኝነት ያላቸው ቢሆኑም አልፎ አልፎ ግን ግልጽነት የጎደላቸው ማብራሪያዎች፣ ትእዛዞች፣ ምሳሌዎችና መልመጃዎች፤ ስህተት ያለባቸው የሰዋስው ይዘቶች፤ ከክፍል ደረጃው በላይ የሆኑ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች እና ያልተመጣጠኑ ንኡሳን ይዘቶች እንዳሉ በተደረገው ሰነድ ፍተሻ ለማረጋገጥ ተችሎል፡፡ በተተኳሪዎቹ ሰነድች ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶችና አደረጃጀት በአብዛኛው ተከታታይነትና ተለጣጣቂነት ያላቸው ሲሆኑ አንዳንድ ይዘቶች ግን ምንም ስፋትና ጥልቀታቸው ሳይጨምር የተደገሙ መሆናቸው በደካማ ጎን የሚያይ ነው፡፡ እንዲሁም ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝርና ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ አደረጃጀትን የተከተለ ቢሆንም በአመዛኙ ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ አደረጃጀት ጎልቶ ታይቶባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የ7ኛና የ8ኛ ክፍሌ መማሪያ መጻህፍትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት በአብዛኛው በመርሀ-ትምህርቱ ላይ የተመሠረቱ ቢሆንም የተወሰኑ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ዳግሞ በሚገባ መርሀትምህርቱ ላይ ተመስርተው ያለመቅረባቸውን ከተደረገው ሰነድ ፍተሻ ለማረጋገጥ ተችሎል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግም በጥናቱ ማጠናቀቂያ ላይ ክፍተቱን ለመሙላት ያስችላሉ የተባለ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡Item ለ9ኛና ለ10ኛ ክፍል በተዘጋጁት (ከ1968—2004ዓ.ም)የ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የሰዋሰው ትምህርት አቀራረብ(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2005-06) ማሞ, እምሻው; አማረ, ጌታሁንየዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ከ1968 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ አገልግሎት ላይ ውለው በነበሩና ባሉት የ9ኝና የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ ምን ምን ሰዋሰዋዊ የትምህርት ይዘቶች ከመቼ ጀምሮ ቀርበው እንደነበረ መፈተሸና ከሥነ--ትምህርታዊ ሰዋሰው የማቅረቢያ መርሆዎች አንጻር አንዴት እንደቀረቡ በመመርመር በጊዜ ሂደት ያሳዩትን ለውጥና መሻሻል ወይም አለመሻሻል መገምገም ነበር፡፡Item ለአስረኛ ክፍል የተመረጡ የአማርኛ ቋንቋ የማስተማሪ ምንባቦች የብቃት ደረጃ(አዲስ አበባ ዪንቨርስቲ, 1986-06) ጌታቸዉ, አዱኛ; አረጋ, ሀ/ሚካኤልይህ ጥናት የታለመዉ በ1984 ዓ.ም ታትሞ ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ማገልገል የጀመረዉን የ10ኛ ኪፍል መማሪያ መጻህፍ ምንባቦች ብቃት ለመገምገም ናዉ፡፡ ግምገማዉን ለማካሄድ የመማሪያ መጻሀፉና የመርሃ-ትምህርቱ ግኑኙነት የመጹፉ ምንባቦች ለጸማራዎቹ ፊላጎት ያላቸዉ ቀረቤታ፤ የምንባቦቹ ተነባቢነትና ተማሪዎቹ አንብበዉ ለመረዳት ያላቸዉችሎታ ምን ያህል እንደሆነ የሚጠይቁ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ የመማሪያ መጽሐፉ መልመጃዎች ይዞታዎች የመርሃ-ትምህርቱ የተለያዩ ክፍሎች/ዝርዝር ዓላማዎች፤ይዘቶች፤ክንዉኖችና ግምገማዎች/በተዛምዶ ቀመር ተሰልተዉ የተገኙት ዉጤቶች በ”ቲ” ቴስት ሲፈተኑ ሁለቱ መሳሪያዎች ግንኙነት እንደለላቸዉ ለማርጋገጥ ተችሏል፡፡ የጽሐፉ መንባቦች ከጸማራች ፍላጎት ጋር ስላላቸዉ ቅርበት ለማዎቅ እንዲረዳ መጠይቆች ልመምህራንና ለተማሪዎች ተበትነዋል ፡፡ ከመጥይቆቹ በተሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ምንባቦቹ በቅኔ፤ተረትና ምሳሌዎች፤ዘይባዊ አነጋገሮች…ከሚጎዱሉዋቸዉ በስተቀር በከፊተኛ ደረጃ ለፍላጎታቸዉ እንደሚስማሙ የተማሪዎቹ መልሶች አመልክተዋል፡፡ከመምህራን የተሰጡ መልሶች የሚጠቁሙት ተማሪዎቹ አንብባዉ ባጥረዷቸዉና የተለያዬ ስልቶች /ዘይባዊ አነጋገሮች ፤ ፈሊጦች፤ተረትና ምሳሌዎች፤/ቢጎድላቸዉም ለተማርዎቹ ፍላጎት፤ዕድሜ ፤ችሎታ ልምድና አካባቢ በመካከለኛ ደረጃ እንደሚስማሙ ያስረዳሉ፡፡ ለሁለተኛ ደረጃ ምንባቦች ተነባቢነት መለኪያ ከሚያገለግሉ 4 ቀመሮች መካከል በፍላሽ በቀመር በፍሪ ግራፍ በመጠቀም ተነባቢነታቸዉን ለመለካት ተሞክፘል፡፡ 3 ናሙና ምንባቦችን ከመጽሐፉ መጀመሪያ፤ መካከልና መጨረሻ በመዉሰድ በተደረገዉ ስሌት ከ2ቱም ቀመሮች የተገኘዉ ዉጤት የሚሳየዉ ምንባቦቹ ተነባቢነት እንደለላቸዉ ነዉ፡፡ምንባቦቹ በተናጠልም ሆነ በጋራ ሲታዪ ለድህረ-ምረቃና ለ7ት በላይ የክፍል ደረጃ ላላቸዉ ሰዎቸ ብቻ የሚነበቡ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡ ለመጨሻዉ ጥያቄ የተገኘዉ መልስ አሉታዊ ነዉ፡፡ከመማሪያ መጽሓፉ በተወሰዱ 3ት ዋና ዋና ምንባቦች አማካይነት የተማሪዎቹን አንብቦ የመረዳት ደረጃ ለማወቅ እንዲያስችል 90 ተማርዎች የግንዛቤ ሙከራ ተሰጥቶ ነበር፡፡በተገኘዉ ዉጤት አተረጓም መሰረት በጣት ከሚቆጠሩት ተማሪዎች በስተቀር አብዛኛዎቹ ምንባቦቹን አንብበዉ መረዳት አይችሉም፡፤ ከላይ ከተገኙት ዉጤቶች በመነሳት የመፍትሄ ሀሳቦች ተሰንዝሯል፡፡ 1/የመማሪያ መጽሐፉና የመርሃ-ትምህርቱ የተለያዩ ክፍሎች ግንኙነት ስለላቸዉ፡የመጸሐፉን መልመጃዎች ይዞታዎች ከመርሀ-ትምህርቱ የተለያዩ ክፍሎች አንጻር በማዘጋጀት የግንኙነቸዉ ስፋት የሚጠብበት መንገድ መቀየስ አለበት፡፡ 2//የመማሪያ መጽሐፉና ምንባቦች የሚጎድሏቸዉ የተለያዩ ስልቶች ለክፍሉ ደረጃ በሚመጥን ሁኔታ በመማሪ መጽሐፉ ዉስጥ የሚጨመርበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል፡፡ 3/ቀመሮቹ ለአማርኛ መማሪያነት ማገልገል መቻል አለመቻላቸዉን በጥናት ማረጋገጥ፡የምንባቡ ተነባቢነት ከዚህ አንጻር ከፍ ለማድረግ መሞከር፡፡ 4/የተማሪዎቹን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማጎልበት መጣርና የምንባቦቹንም ክብደት ከተማሪዎቹ አንብቦ የመረዳት ደረጃ ጋር ለማመጣጠን መሞከር፡፡Item ለአንደኛ ደረጃ ሁለተኛ እርከን በተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ መርሀ ትምህርት ውሰጥ የፅህፈት ክሂል የማስተማር ሰነ-ዘዴዎች አተገባበር ፈተሻ(AAU, 2000-06) አዳነ, አንለይ; እንዳለማው, ጌታቸው(ረዳት ፕሮፌሰር )የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ለአንደኛ ደረጃ ሁለተኛ እርከን በተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ መርህ ትምህርት ውስጥ የፅህፈት ክሂልን ለማስተማር የቀረቡትን ስነዘዴዎች አተገባበር መፈተሽ ሲሆን በመርህ ትምህርቱ ፅህፈትን ለማስተማር ተግባር ላይ የዋሉት ስነዘዴዎች በደረጃው ከተዘጋጁት የመማሪያና ማስተማርያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸውን ተያያዥነት በክፍል ውስጥ ያለቸውን አተገባበር የመምህራንንና የተማሪዎችን ሚና መቃኘትና የሚታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመፈተሽ ከደረሰበት ውጤት ተነስቶ የመፍትሔ ሀሳቦቸን መጠቆም ነው፡፡Item ለጽህፈት ክሂል የተመረጡት የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች እንደት ተደራጅተዋል ? (በአዲስ አበባ መስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለመጀመሪያ ደረጃ የሁለተኛ እርከን (5-8) በተዘጋጁት የአማርኛ መማሪያ መፃህፍት ላይ የተደረገ የይዘት ትንተናና ግምገማ)(አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ, 1992-05) ታፈሰ, ጽጌ; ለታ, ደጀኔ (ዶ/ር)የዚህ ጥናት አላማ በአዲስ አበባ መሰተዳድር ትምህርት ቢሮ ለመጀመሪያ ደረጃ የሁለተኛዉ እርከን (5-8) በተዘጋጁት የአማርኛ መማሪያ መጻህፍት ዉስጥ የጽህፈት ክሂል ይዘቶችን አደረጃጀት መተንተንና መገምገም ነዉ፡፡Item “ሊሚናሊቲ” እና ለውጥ በሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች በጃቢ ጠህናን ማኅበረሰብ(Addis Ababa University, 2016-07) ሥራዬ እንዳለው ውበቴ; ዋልተንጉሥ መኮንን (ዶ/ር); ደስታ አማረ (ዶ/ር)ይህ ጥናት “ሊሚናሊቲ እና ለውጥ በሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች በጃቢ ጠህናን ወረዳ ማኅበረሰብ” በሚል ርዕስ ተካሂዷል፡፡ በዋናነት ሊሚናሊቲንና ለውጥን ከሕይወት ሽግግር (ወሊድ፣ ጋብቻና ሞት) ሥርዓተ ክዋኔዎች ጋር አያይዞ አጥንቷል፡፡ የሕይወት ሽግግሮች በአንድ በኩል የግለሰብ በሌላ በኩል የጋራ ጉዳዮች በመሆናቸው ከሽግግሮች ባሕርይና ከማኅበረሰቡ ባህል ጋር በተያያዙ ምክንያቶች አስጊና አሳሳቢ፣ ባለጉዳዮችንም ለልዩ ልዩ ለውጦች የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ በመሆኑም በሕይወት ሽግግሮች ወቅት የተለያዩ ሥርዓተ ክዋኔዎች ይፈጸማሉ፡፡ ጥናቱ እነዚህን ሥርዓተ ክዋኔዎች ሽግግሩን ከሚያካሂዱ ባለጉዳዮች ጋር በማስተሳሰር፣ በዐማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ በጃቢ ጠህናን ወረዳ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ማኅበረሰብ እምነትና ባህል ማሳያነት አጥንቷል፡፡ የሕይወት ሽግግሮች ባለጉዳይን አስጨናቂ ያደረጉባቸውን ሁኔታዎች መለየት፤ በወቅቱ የሚከወኑ ሥርዓቶችን ዓላማ መግለጽ፤ ሽግግሩ ያስከተላቸውን ለውጦች መፈተሽ፣ በሽግግሩ ከተገኙ ለውጦች ጋር የሚያስተዋውቁ ወይም የሚያላምዱ ብልሃቶችን መመርመር እና በሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች ላይ የተገለጡ የጋራ ትዕምርቶችን መተንተን የሚሉ ዓላማዎችን አሳክቷል፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ ሲሆን መረጃዎች ከቀዳማይና ከካልዓይ ምንጮች ተሰብስበዋል፡፡ ምልከታ፣ ቃለ መጠይቅ እና ተተኳሪ የቡድን ውይይት መረጃዎች የተሰበሰቡባቸው ዘዴዎች ሲሆኑ በሂደት አራት ዙር የመስክ ሥራ ተከናውኗል፡፡ በወረዳው ከሚገኙ አርባ አንድ ቀበሌዎች ውስጥ በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት ሥድስት ቀበሌዎች ተጠኝ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ መረጃ በመስጠት ሠላሳ አምስት ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አስራ አራቱ በቁልፍ መረጃ ሰጪነት ተሳትፈዋል፡፡ አመራረጡም ጾታን፣ ማኅበራዊ ደረጃን፣ እድሜን፣ ለጉዳዩ ያለን ተጋላጭነት እና ሀሳብን የመግለጽ ብቃት ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ መረጃው በዲጅታል ካሜራ፣ በመቅረጸ ድምጽ እና በማስታወሻ ደብተር ተይዟል፡፡ ትክክለኛነቱም መረጃ ሰጪዎች በተደጋጋሚ ያነሷቸው፣ በምልከታ ወቅት ያጋጠሙ እና በተተኳሪ የቡድን ውይይት ወቅት ተወያይተው የተስማሙባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን በመለየት ተመሳክሯል፡፡ ከመረጃ ሰጭዎች የተገኙ መረጃዎች ትዕምርታዊ መስተጋብር፣ ተግባራዊ መዋቅራዊ እና ፍካሬ ልቡናዊ ንድፈ ሀሳቦች እንደ አስፈላጊነታቸው ለትንታኔ ማሕቀፍነት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ የመረጃ ትንተናው እንደሚያሳየው የጃቢ ጠህናን ወረዳ ማኅበረሰብ ከሃይማኖቱ፣ ከእምነቱ እና ከባህሉ የወጡ በርካታ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ነው፡፡ የሰውን ልጅ ስጋዊ አፈጣጠርና ባሕርይ ከመሬት አፈጣጠር ጋር፤ መንፈሳዊ አፈጣጠሩን ደግሞ ከነፋስ፣ ከእሳት ከውሃ እና ከመሬት ባሕርያት ጋር ያዛምዳል፡፡ በሌላ በኩል የሰው ልጅ ልባዊት (ሀሳብ)፣ ነባቢት (ንግግር) እና ህያዊት (ዘላለማዊነት/ትንሳኤ)፣ የተባሉ የመንፈሳዊ ሰብዕና መገለጫዎች ወይም ባሕርያተ ነፍስ አሉት ብሎ ያምናል፡፡ የጃቢ ጠህናን ወረዳ ማኅበረሰብ እርስ በእርሱ እንዲተሳሰርና እንደ ማኅበረሰብ እንዲቀጥል ያስቻሉ የተለያዩ የዝምድና መፍጠሪያ እና አብሮ የመኖር ብልሃቶች አሉት፡፡ የሕይወት ሽግግሮች ባለጉዳዩን የደረጃ ሽግግር እና ለውጥ እንዲያካሂድ የሚያደርጉ መሆናቸው፤ ከሽግግሮች ጸባይ እና ከማኅበረሰቡ ባህል በሚነሱ ምክንያቶች ዋናው የሽግግር ወቅት አስጊ እና አሳሳቢ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ከዚህም የተነሳ የሕይወት ሽግግሮች አዲስ እና መለማመጃ የሌላቸው፣ ድንገት ደራሽ፣ ቅጽበታዊ፣ ምሥጢራዊ፣ ራሳቸውን የማይደግሙ፣ አስገዳጅ እና ነጣይ በመሆናቸው ባለጉዳዮችንም ሆነ ማኅበረሰቡን ለጭንቀትና ለግራ መጋባት ይዳርጋሉ፡፡ በወቅቱ የተፈጠረን ጭንቀት እና ግራ መጋባት ለመቀነስ ወይም ለማከም የተለያየ ዓላማና ሚና ያላቸው ሥርዓተ ክዋኔዎች ከቅድመ ሽግግሩ ጀምሮ ዋናው ሽግግር ከተካሄደ በኋላም ይፈጸማሉ፡፡ የሕይወት ሽግግሮች ባለጉዳዮች የስም፣ የአለባበስና የአጊያጊያጥ፣ የቋንቋ አጠቃቀም፣ የማኅበራዊ ደረጃና የስነ ልቡና ለውጥ የሚያካሂዱባቸው መሆናቸውን እና ከእነዚህ ለውጦች ጋር የሚያስተዋውቁ እና የሚያለማምዱ ክዋኔዎችን አሳይቷል፡፡ በሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች ወቅት ከተገለጡ የጋራ ትዕምርቶች መካከል ቀዳሚን ማክበር፣ ጀግናን ማወደስ፣ ሃይማኖትን፣ ሀገርን እና ሥራን መውደድ፣ መልካም ምግባር ማኅበረሰቡ በተለመደው መልክ እንዲቀጥል ያገዙ ዋና ዋና መልካም እሴቶች ናቸው፡፡Item “ልጅነት” በማሕሌትና አለንጋና ምስር፤ ሥነ ልቡናዊ ንባብ(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2006-06) አለበል, ቴዎድሮስ; ገብሬ, ቴዎድሮስ (ረ/ፕ)ይህ ጥናት ልጅነት በማሕሌት እና አለንጋና ምስር፤ ሥነ ልቡናዊ ንባብ በሚል የተደረገ ነው፡፡ የጥናቱ ዘዴ በይነ-ቴክስታዊ ሲሆን ስልቱ ደግሞ ፍካሬ ነው፡፡ ጥናቱ በተመረጡት ቴክስቶች ውስጥ ልጅነት ከሥነ ልቡና ንድፈ ሃሳቦች አንጻር ቢፈተሽ መልካም ነው በሚል ዕምነት የተደረገ ነው፡፡ በቴክስቶቹ የተቀረጹ ልጆች ማኅበረ-ልቡናዊና ሳይኮሴክሿል ማንነት፣ Oedipus complex እና የልቡና ፍርቅነት፣ የጨቅላነት ግንትሮሽ እና የሁለት ሰብዕናዎች መቃየጥ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ሚቶሎጂዎች የተቀዱ መባያዎች ሰብዕናን መርምሮ ለማሳየት ትኩረት የተደረገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡ ጥናቱ ወዲህ በቴክስቶቹ ውስጥ የተቀረጹ ገጸ-ልጆች የብቸኝነት፣ የመከዳትና የመጣል ስሜት የሚስተዋልባቸው እንደሆኑ፣ ወዲህ ደግሞ የአሳዳጊዎቻቸው ሚና አፍራሽ መሆኑ፣ የጨቅላነት ሳይኮሴክሿል ዕድገት ፊክሴሽንና sadistic displacement ማደሪያዎች እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡ ስለሆነም፣ በእነዚህና በትንተናው ውስጥ በ“ተዘነቁ” ሃሳቦች ልጆቹ ማኅበረ-ባህላዊ ኃላፊነትን መሸከም የማይችሉ እንደሆኑ ለማጠቃለል ተሞክሯል፡፡ በመጨረሻም በቴክስቶቹ ውስጥ ልጆቹ የተቀረጹት፣ ማኅበረ-ባህላዊ ሥርዓቶችና ተፈጥሯዊ ማንነቶች በመጎራበት ነው ብሎ ማጠቃለል ይቻላል፡፡ IVItem መሣል- ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ(በአዲስ አበባ ዩኒቨርስት, 2003-06) ቦጋለ, ብርሃኑ; አስፋው, ዘሪሁንይህ ጥናት መሣል- ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ የግጭት አፈታቱን አጠቃላይ ገ ታ እና ባላጋራዎች ሲዳኙ የቻሉበትን ምክንያት ለማወቅ መረጃዎችን በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ሽሆች፤ ካዳምች፤ሽማግሌዎች፤ በተቋሙ ከተዳኙ ግለሰቦች፤ ወንጀል መርማሪ ፓሊሶች እና ከፍርድ ቤት ዳኞች ተሰብስቧል፡፡ የመረጃ ሰብሰባዉም ተፈጥሮአዊ እና ቅንብር ተፈጥሮአዊ መቼቶችን በመጠቀም በቃለ መጠይቅ እና በምልከታ የተከናወነ ሲሆን፤ መረጃዎችም በቪዲዮ፤ በፎቶ፤ በጽሁፍ እና እና በመቅረጸ ድምጽ ተይዘዋል፡፡ የተገኙ መረጃዎች በገላጭ እና በይዘት ትንተና ስልት ተተንትነዎል፡፡ በዚህ መሰረት ከተራ ጠብ እሰከ ግድያ ያሉ የግጭት አይነቶች እንደሚፈቱ የጥናቱ ግኝት ያመለከታል፡፡ በተጠናው አካባቢ የሚከሰቱትም የግጭት አይነቶች ከንብረት ጋር የተያያዙ (መሬት፤ ድንበር፤ የግጦሸ ቦታ፤ የመስኖ ውኃ፤ ከብት ዝርፈያ፤ ቤትና ሰብል ቃጠሎ፤ አትክልት እና ሰብል መቂረጥ ) ፤ የቤተሰብ ጠብ (ከጋብቻ፤ከልጆች እና ከዉርስ) ወንጀል (ግድያ፤ድብደባና ስድብ)፤ተራ ወንጀሎእ (ሰርቆትና ማታለል ፤ ቤት ድብደባና ክህደት) ችና የቡድን ጠብ (የብሔረሰብ) መሆናቸውን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ለግጭቶቹ መፈጠር ምክንያት የሚሆኑት ማኅበራ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፤ እለታዊ ጠብ እና ቂም በቀል እንደሆኑም ጥናቱ አመልክቷል፡፡Item መስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ መስማት በተሳናቸው ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ችሎታና የመማር ፍላጎት ላይ ያለው ተጽዕኖ (በሰባተኛ ክፍል ላይ የተካሄደ ሙከራዊ ጥናት)(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2024-05) እታገኝ ገደፋው; ዶ/ር ጌታቸው እንዳላማውየዚህጥናትዋናኛዓላማ መስተጋብራዊ የማስተማሪያዘዴመስማት የተሳናቸው ተማሪዎችንየመጻፍክሂል ችሎታና የመማር ፍላጎት ከማሻሻልአንጻርያለውንተጽዕኖመመርመርነው፡፡ጥናቱ በአንድ የሙከራ ቡድን ንድፍ(Single Group Experimental Design) ላይ በመመስረት የተከናወነ ሲሆንይህየምርምርንድፍምየጥናት ናሙናን በመምረጥ ሂደት የተጠኚዎች ቁጥር ለሁለት ቡድን ማለትም ለጥብቅ (Control) ለሙከራ (Exprmental) ሳይበቃ ሲቀር የሚመረጥ ነው፡፡ጥናቱየተካሄደው በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ከሚገኙ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ትምህርት ቤቶች መካከል በአልፋ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ትምህርት ቤት ሲሆን በትምህርትቤቱከሚገኙ የክፍል ደረጃዎች መካከል ለጥናቱ የተመረጠው ክፍል ሰባተኛ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱንና የክፍል ደረጃውን በመምረጥ ረገድ አላማ ተኮር ናሙና (purposive Sampling)ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በጥናቱ ተሳታፊ የሆኑት ተማሪዎች በጠቅላይ ናሙና(Comprehensive Sampling)የተመረጡ ሲሆን በዚህም በክፍል ደረጃው የሚማሩ ሁሉም ተማሪዎች (ሰባቱም) በጥናቱ ተካተዋል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ በጥናቱ እንዲሳተፉ የተደረገበት ዋናው ምክንያት ቁጥራቸው ውስንና ከተጠቀሰው በላይ ባለመሆኑ ነው፡፡ለጥናቱ በመረጃመስብሰቢያዘዴነት ተግባር ላይ የዋሉት ፈተና፣የጽሑፍመጠይቅናየተማሪዎች የቡድን ተኮር ውይይት ናቸው፡፡ ፈተናውቅድመናድህረ ትምህርት ፈተና ሲሆን ዋነኛ አላማውም ተጠኚ ተማሪዎችበመስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ ከመማራቸው በፊትና በኋላ ያላቸውየመጻፍክሂልችሎታ ጉልህ ልዩነት ማሳየት አለማሳየቱን ለማወቅ ነው፡፡ የጽሁፍ መጠይቁም በቅድመና ድህረ ትምህርቱ ትግበራ ወቅት የሚሞላ ሲሆን አላማው ተጠኚ ተማሪዎች በመስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ ከመማራቸው በፊትና በኋላ የነበራቸው የመጻፍ ክሂል ትምህርት የመማር ፍላጎት ምን ያህል ጉልህ ልዩነት እንዳሳየ ማረጋገጥ ነው፡፡ ሌላኛው የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሆኖ ያገለገለው የቡድን ተኮር ውይይት ሲሆን አላማው ደግሞ በፈተናና በጽሁፍ መጠይቅ ለተሰበሰቡት መረጃዎች ማጠናከሪያ ሀሳብ ማስገኘት ነው፡፡በዚህም መሰረት የመጻፍ ክሂል ፈተናውና የጽሁፍ መጠይቁ በቅድመና ድህረ ትምህርት ትግበራው ላይ ለተጠኚዎች ቀርበው መረጃ የተሰበሰበባቸው ሲሆን የተገኘው ውጤትም በጥንድ ናሙና ቲ- ቴስት (Paird sample t-test) መጠናዊየመረጃ መተንተኛ ስልት ተሰልቶ ( P< 0.05)የሆነ የጉልህነት መለያ ውጤት ተገኝቷል፡፡ በአንጻሩ በቡድን ተኮር ውይይቱ የተሰበሰበው መረጃም በአይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ተተንትኖ በፈተናውና በጽሁፍ መጠይቁ የተገኘውን የሚደግፍ ውጤት አስገኝቷል፡፡በአጠቃላይ በሶስቱ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ተሰብስበው ከተተነተኑት መረጃዎች የተገኘው ውጤት የሚያመለክተው መስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ መስማት በተሳናቸው ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ችሎታና የመማር ፍላጎት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ መኖሩንና ተጽዕኖውም አዎንታዊ መሆኑን ነው፡፡Item ሙዚቃዊ አስተማስሎ እና ግላጼ በተመረጡ የአማርኛ ልቦለዶች ውስጥ፤ ነገረ ኪናዊ ጥናት(2008-06) ጳውሎስ, ጌራሃዲስ; ገብሬ, ረዳት ፕሮፊሰር ቴዎድሮስ‹‹ሙዚቃዊ አስተማስሎ እና ግላጼ በተመረጡ የአማርኛ ልቦለዶች ውስጥ፤ ነገረ ኪናዊ ጥናት›› በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ጥናት የቆይታ ጊዜያቸው በተቀራረበ አምስት የአማርኛ ረጂም ልቦለድ ድርሰቶች፡-Item ሚናለዋጭ ዘዴ (Reciprocal Teaching) የአማርኛና አፍፈት ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳትን ችሎታና የማንበብን ተነሳሽነት ለማሳደግ የሚኖረው አስተዋጽኦ፡- በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2008-06) መብሬ, ዘውዱ; አለሙ, ዶ/ር ማረውየዚህ ጥናት ዓቢይ ዓላማ ሚናለዋጭ ዘዴ የአማርኛ አፍፈት ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለውን አስተዋጽኦ በከፊል ፍትነታዊ ምርምር መፈተሸ ነበር፡፡Item ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት እና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምድ፤ በአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2023-09-11) በደገሉ ሮቢ; ዳዊት ፍሬሕይወት (ዶ/ር)የዚህ ጥናት ዋና አላማ ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከተማሪዎች አንብቦ የመረዲት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ ነው፡፡ አላማውን ከግብ ለማድረስም ተዛምዶዊ የጥናት ስሌት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ የጥናቱ ተሳታፉዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በእሉ ገላን ወረዲ ከሚገኙ ሶስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የኦዲ ብሲል ትምህርት ቤት ነው፡፡ ይህ ትምህርት ቤት አመቺ የንሞና ዘዳ በመጠቀም ተመርጧሌ፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ በ2015 ዓ.ም በአምስት የመማሪያ ክፍልች ውስጥ ተማሪዎች ተመድበው ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሲሆን ከአምስቱ ምዴብ (ክፍል) ውስጥ 10ኛ “D” የመማሪያ ክፍል ተማሪዎችን በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ ተወስደው በአጠቃላይ 80 ተማሪዎች የጥናቱ ተሳታፉዎች እንዱሆኑ ተዯርጓል፡፡ ከጥናቱ ተሳታፉዎችም ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ በተመለከተ በአንብቦ መረዳት ችሎታ ፈተናና በፅሁፍ መጠይቅ አማካይነት መረጃው ተሰብስቧሌ፡፡ የተሰበሰበው መረጃም በአማካይ ውጤት፣ በመደበኛ ልይይትና በፒርሰን የተዛምዶ ስሌት ተሰልቶ ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተውም ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከተማሪዎች አንብቦ በመረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ አዎንታዊ እንደሆነ አመላክቷል፡፡ የተዛምዶው መጠንም ጭንቀትን መቀነስ (r = 0.846, p= .001) ሲሆን ጥያቄ መጠየቅ(r = 0.642, p= .001) ሆኖ ተገኝቷል፤ በትብብር መስራት (r = 0.701, p= .001) መሆኑን አሳይቷል፡፡ ጭንቀትን መቀነስ፣ ጥያቄ መጠየቅና በትብብር መስራት ከአንብቦ የመረዳት ችሎታ ጋር ያላቸው የተጋርቶ መጠንም R2= 0.521 ወይም 52.1% ነው፡፡ ይህም የሚያመሊክተው የተማሪዎች ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከአንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ጋር ያለው ተዛምዶ R2= 0.521 በመሆን ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህ ከጥናቱ ውጤት በመነሳት ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር አዎንታዊ የሆነ ተዛምድ አለ ከሚለው ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ መምህራን ማንበብን በሚያስተምሩበት ወቅት ማህበረ-ስሜታዊ ብልሃትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ቢያስተምሩ ተመራጭ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህ ርዕሰ ጉዲይ አዎንታዊ እንዲሆን የሚያደርጉ ስራዎች በለሎች ተለውጦዎች፤በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ በርከት ባሉ ናሙናዎች ወደፊት ቢፈተሹ ከዚህ የተሸለ ውጤት ሊገኝ ይችላል የሚል ሃሳብ ተመልክቷል፡፡Item ሠዒሉነት እና ሠዒሉ ገጸ ባሕርያት በተመረጡ የአማርኛ መናዊ ሌብ ወሇድች(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2007-06) አዲነ, አገኘሁ; ገብሬ, ቴዎዴሮስ (ረዲት ፕሮፋሰር)ይኽ ጥናት “ሥዕሌ፣ ሠዒሉነት እና ሠዒሉ ገጸ ባሕርያት በተመረጡ የአማርኛ መናዊ ሌብ ወሇድች” በሚሌ ርዕስ ሥር በተመረጡ የአማርኛ ሌቦሇድች ውስጥ (አዯፌርስ፣ ከአዴማስ ባሻገር፣ ማሕላት እና ግርድሽ) ሥዕሌ እና ሠዒሉነት በምን ሁኔታ እንዯቀረቡ፤ ሠዒሉ ገጸባሕርያት እንዳት እንዯተቀረፁ፤ የሥዕሌ እና ሥነ ጽሐፌ ዱሲፕሉናዊ ተጋቦት በሌቦሇድቹ ውስጥ በምን መንገዴ እንዯተስተማሰሇ ሇመመርመር የሞከረ ነው፡፡ በመታገጊያነት በምገሇገሌባቸው፤ በነገረ-ኪንም ሆነ በኪነ ጥበባት ንዴፇ ሏሳቦች ተሇዋዋጭ ባሕርይ የተነሣ፤ በሥነ ጽሐፌ ዏውዴነት የሚጠኑት ‹‹ሥዕሌ፣ ሠዒሉነት እና ሠዒሉ ገጸ ባሕርያት›› እንዯሚያነሧቸው ርዕሰ ጉዲዮች፣ በቴክስቱ ውስጥ እንዲሊቸው አኗኗር እና መሌክ ወተ. ‹‹በሰበካቸው›› አዋግኜ ሇመመርመር ጥረት አዴርጌያሇሁ፡፡ ሌቦሇድቹ፣ ‹‹ሥዕሌ በሌቦሇዴ ዏውዴ ውስጥ››፣ ‹‹በሌቦሇዴ አውዴ ውስጥ የሠዒሉነትና የሠዒሉ ገጸ ባሕርያት ሚና›› እና ‹‹ሥዕሊዊ (ዕይታዊ) ቴክስት (visual texts)›› በሚለ ሦስት ወገኖች ተፇርጀዋሌ፡፡ በምርምሩ ሇማረጋገጥ እንዯተሞከረውም፣ በሌቦሇድቹ ውስጥ፤ እኩይ ምግባር ኪናዊ ፌትሕ ያገኛሌ፣ የዯነዯነ ሌቡናና ቀሌብ ይፇርሳሌ፡፡ ዴብቅ ማንነት ይጋሇጣሌ፣ ረቂቅ ሰዋዊ ስሜቶች ሇዒይነ-ሥጋ ይበቁበታሌ፡፡ እኩይ ምግባር ሲጋሇጥ፤ የዴርጊቱ ባሇቤት የገነባው ማንነት ይናዲሌ፤ በአዱስ ይዋቀራሌ፣ ፇውስ ያገኛሌ፡፡ ረቂቅ ሰዋዊ ስሜቶች ይገሇጣለ፡፡ ከዙህም ባሻገር ሥዕልቹ በሌቦሇድቹ ፌፃሜ የሚከሰተውን ሌቦሇዲዊ ሁነት ይጠቁማለ፡፡ ዕይታዊ-ንግር ሆነውም ያገሇግሊለ፡፡ ሥዕሌ በርዕሰ ጉዲይነት በተነሣባቸው ሌቦሇድች፤ ምስሌ ከፌተኛ የመናገርያ ቋንቋ እንዯሆነ በተጠኑት ሌቦሇድች በጉሌህ ታይቷሌ፡፡ ሥነ ጽሐፌ እና ሥዕሌም፤ አንዴም በሥነ ጽሐፌ ዏውዴ ውስጥ፣ አንዴም ዯግሞ በውስጥ እና በሽፊን ገጽ ሥዕልች ትግግዜ፤ ሚና ሲጋሩ እንዱሁም ዒይነ-ሌቡናንም ሆነ ዒይነ-ሥጋን በምስሌ ሲሞለ ተስተውሎሌ፡፡Item ረዥም ልቦለድ መፃፍ ክሂልን ለማዳበር ያለውምና በጉለሌ ክፍል ከተማቤካቲት 12ትምርትቤትበ11ኛ ተማሪዎችላ የተካሄደውሙከራ ጥናት(Addis Ababa University, 2010-08) ቶላ, ራሔል; ገብሪ, ደረጀ(PhD)Item ራጋ ማጋ- ሀገረሰባዊ የግጭት አፈታት ስርዓት በማረቆ ብሄረሰብ(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2005-12) ታደሰ, ተመስገን; አዘዘ ዶ/ር, ፈቃደይህ ጥናት ራጋ ማጋ- ሀገረሰባዊ የግጭት አፈታት ስርዓት በማረቆ ብሄረሰብ በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡