መስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ መስማት በተሳናቸው ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ችሎታና የመማር ፍላጎት ላይ ያለው ተጽዕኖ (በሰባተኛ ክፍል ላይ የተካሄደ ሙከራዊ ጥናት)
No Thumbnail Available
Date
2024-05
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህጥናትዋናኛዓላማ መስተጋብራዊ የማስተማሪያዘዴመስማት የተሳናቸው ተማሪዎችንየመጻፍክሂል ችሎታና የመማር ፍላጎት ከማሻሻልአንጻርያለውንተጽዕኖመመርመርነው፡፡ጥናቱ በአንድ የሙከራ ቡድን ንድፍ(Single Group Experimental Design) ላይ በመመስረት የተከናወነ ሲሆንይህየምርምርንድፍምየጥናት ናሙናን በመምረጥ ሂደት የተጠኚዎች ቁጥር ለሁለት ቡድን ማለትም ለጥብቅ (Control) ለሙከራ (Exprmental) ሳይበቃ ሲቀር የሚመረጥ ነው፡፡ጥናቱየተካሄደው በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ከሚገኙ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ትምህርት ቤቶች መካከል በአልፋ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ትምህርት ቤት ሲሆን በትምህርትቤቱከሚገኙ የክፍል ደረጃዎች መካከል ለጥናቱ የተመረጠው ክፍል ሰባተኛ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱንና የክፍል ደረጃውን በመምረጥ ረገድ አላማ ተኮር ናሙና (purposive Sampling)ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በጥናቱ ተሳታፊ የሆኑት ተማሪዎች በጠቅላይ ናሙና(Comprehensive Sampling)የተመረጡ ሲሆን በዚህም በክፍል ደረጃው የሚማሩ ሁሉም ተማሪዎች (ሰባቱም) በጥናቱ ተካተዋል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ በጥናቱ እንዲሳተፉ የተደረገበት ዋናው ምክንያት ቁጥራቸው ውስንና ከተጠቀሰው በላይ ባለመሆኑ ነው፡፡ለጥናቱ በመረጃመስብሰቢያዘዴነት ተግባር ላይ የዋሉት ፈተና፣የጽሑፍመጠይቅናየተማሪዎች የቡድን ተኮር ውይይት ናቸው፡፡ ፈተናውቅድመናድህረ ትምህርት ፈተና ሲሆን ዋነኛ አላማውም ተጠኚ ተማሪዎችበመስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ ከመማራቸው በፊትና በኋላ ያላቸውየመጻፍክሂልችሎታ ጉልህ ልዩነት ማሳየት አለማሳየቱን ለማወቅ ነው፡፡ የጽሁፍ መጠይቁም በቅድመና ድህረ ትምህርቱ ትግበራ ወቅት የሚሞላ ሲሆን አላማው ተጠኚ ተማሪዎች በመስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ ከመማራቸው በፊትና በኋላ የነበራቸው የመጻፍ ክሂል ትምህርት የመማር ፍላጎት ምን ያህል ጉልህ ልዩነት እንዳሳየ ማረጋገጥ ነው፡፡ ሌላኛው የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሆኖ ያገለገለው የቡድን ተኮር ውይይት ሲሆን አላማው ደግሞ በፈተናና በጽሁፍ መጠይቅ ለተሰበሰቡት መረጃዎች ማጠናከሪያ ሀሳብ ማስገኘት ነው፡፡በዚህም መሰረት የመጻፍ ክሂል ፈተናውና የጽሁፍ መጠይቁ በቅድመና ድህረ ትምህርት ትግበራው ላይ ለተጠኚዎች ቀርበው መረጃ የተሰበሰበባቸው ሲሆን የተገኘው ውጤትም በጥንድ ናሙና ቲ- ቴስት (Paird sample t-test) መጠናዊየመረጃ መተንተኛ ስልት ተሰልቶ ( P< 0.05)የሆነ የጉልህነት መለያ ውጤት ተገኝቷል፡፡ በአንጻሩ በቡድን ተኮር ውይይቱ የተሰበሰበው መረጃም በአይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ተተንትኖ በፈተናውና በጽሁፍ መጠይቁ የተገኘውን የሚደግፍ ውጤት አስገኝቷል፡፡በአጠቃላይ በሶስቱ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ተሰብስበው ከተተነተኑት መረጃዎች የተገኘው ውጤት የሚያመለክተው መስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ መስማት በተሳናቸው ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ችሎታና የመማር ፍላጎት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ መኖሩንና ተጽዕኖውም አዎንታዊ መሆኑን ነው፡፡