ለአስረኛ ክፍል የተመረጡ የአማርኛ ቋንቋ የማስተማሪ ምንባቦች የብቃት ደረጃ
No Thumbnail Available
Date
1986-06
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዪንቨርስቲ
Abstract
ይህ ጥናት የታለመዉ በ1984 ዓ.ም ታትሞ ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ማገልገል የጀመረዉን የ10ኛ ኪፍል መማሪያ መጻህፍ ምንባቦች ብቃት ለመገምገም ናዉ፡፡ ግምገማዉን ለማካሄድ የመማሪያ መጻሀፉና የመርሃ-ትምህርቱ ግኑኙነት የመጹፉ ምንባቦች ለጸማራዎቹ ፊላጎት ያላቸዉ ቀረቤታ፤ የምንባቦቹ ተነባቢነትና ተማሪዎቹ አንብበዉ ለመረዳት ያላቸዉችሎታ ምን ያህል እንደሆነ የሚጠይቁ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
የመማሪያ መጽሐፉ መልመጃዎች ይዞታዎች የመርሃ-ትምህርቱ የተለያዩ ክፍሎች/ዝርዝር ዓላማዎች፤ይዘቶች፤ክንዉኖችና ግምገማዎች/በተዛምዶ ቀመር ተሰልተዉ የተገኙት ዉጤቶች በ”ቲ” ቴስት ሲፈተኑ ሁለቱ መሳሪያዎች ግንኙነት እንደለላቸዉ ለማርጋገጥ ተችሏል፡፡
የጽሐፉ መንባቦች ከጸማራች ፍላጎት ጋር ስላላቸዉ ቅርበት ለማዎቅ እንዲረዳ መጠይቆች ልመምህራንና ለተማሪዎች ተበትነዋል ፡፡
ከመጥይቆቹ በተሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ምንባቦቹ በቅኔ፤ተረትና ምሳሌዎች፤ዘይባዊ አነጋገሮች…ከሚጎዱሉዋቸዉ በስተቀር በከፊተኛ ደረጃ ለፍላጎታቸዉ እንደሚስማሙ የተማሪዎቹ መልሶች አመልክተዋል፡፡ከመምህራን የተሰጡ መልሶች የሚጠቁሙት ተማሪዎቹ አንብባዉ ባጥረዷቸዉና የተለያዬ ስልቶች /ዘይባዊ አነጋገሮች ፤ ፈሊጦች፤ተረትና ምሳሌዎች፤/ቢጎድላቸዉም ለተማርዎቹ ፍላጎት፤ዕድሜ ፤ችሎታ ልምድና አካባቢ በመካከለኛ ደረጃ እንደሚስማሙ ያስረዳሉ፡፡
ለሁለተኛ ደረጃ ምንባቦች ተነባቢነት መለኪያ ከሚያገለግሉ 4 ቀመሮች መካከል በፍላሽ በቀመር በፍሪ ግራፍ በመጠቀም ተነባቢነታቸዉን ለመለካት ተሞክፘል፡፡
3 ናሙና ምንባቦችን ከመጽሐፉ መጀመሪያ፤ መካከልና መጨረሻ በመዉሰድ በተደረገዉ ስሌት ከ2ቱም ቀመሮች የተገኘዉ ዉጤት የሚሳየዉ ምንባቦቹ ተነባቢነት እንደለላቸዉ ነዉ፡፡ምንባቦቹ በተናጠልም ሆነ በጋራ ሲታዪ ለድህረ-ምረቃና ለ7ት በላይ የክፍል ደረጃ ላላቸዉ ሰዎቸ ብቻ የሚነበቡ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡
ለመጨሻዉ ጥያቄ የተገኘዉ መልስ አሉታዊ ነዉ፡፡ከመማሪያ መጽሓፉ በተወሰዱ 3ት ዋና ዋና ምንባቦች አማካይነት የተማሪዎቹን አንብቦ የመረዳት ደረጃ ለማወቅ እንዲያስችል 90 ተማርዎች የግንዛቤ ሙከራ ተሰጥቶ ነበር፡፡በተገኘዉ ዉጤት አተረጓም መሰረት በጣት ከሚቆጠሩት ተማሪዎች በስተቀር አብዛኛዎቹ ምንባቦቹን አንብበዉ መረዳት አይችሉም፡፤
ከላይ ከተገኙት ዉጤቶች በመነሳት የመፍትሄ ሀሳቦች ተሰንዝሯል፡፡
1/የመማሪያ መጽሐፉና የመርሃ-ትምህርቱ የተለያዩ ክፍሎች ግንኙነት ስለላቸዉ፡የመጸሐፉን መልመጃዎች ይዞታዎች ከመርሀ-ትምህርቱ የተለያዩ ክፍሎች አንጻር በማዘጋጀት የግንኙነቸዉ ስፋት የሚጠብበት መንገድ መቀየስ አለበት፡፡
2//የመማሪያ መጽሐፉና ምንባቦች የሚጎድሏቸዉ የተለያዩ ስልቶች ለክፍሉ ደረጃ በሚመጥን ሁኔታ በመማሪ መጽሐፉ ዉስጥ የሚጨመርበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል፡፡
3/ቀመሮቹ ለአማርኛ መማሪያነት ማገልገል መቻል አለመቻላቸዉን በጥናት ማረጋገጥ፡የምንባቡ ተነባቢነት ከዚህ አንጻር ከፍ ለማድረግ መሞከር፡፡
4/የተማሪዎቹን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማጎልበት መጣርና የምንባቦቹንም ክብደት ከተማሪዎቹ አንብቦ የመረዳት ደረጃ ጋር ለማመጣጠን መሞከር፡፡
Description
Keywords
የአማርኛ ቋንቋ የማስተማሪ