መስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ መስማት በተሳናቸው ተማሪዎች የመጻፍ ክሂሌ ችሎታና የመማር ፍላጎት ላይ ያለው ተጽዕኖ (በሰባተኛ ክፍል ላይ የተካሄደ ሙከራዊ ጥናት)
No Thumbnail Available
Date
2016
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋነኛ ዓላማ መስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችን የመጻፍ ክሂሌ ችልታና የመማር ፍላጎት ከማሻሻል አንጻር ያለውን ተጽዕኖ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ በአንዴ የሙከራ ቡድን ንድፍ (Single Group Experimental Design) ላይ በመመስረት የተከናወነ ሲሆን ይህ የምርምር ንድፍም የጥናት ናሙናን በመምረጥ ሂደት የተጠኚዎች ቁጥር ለሁለት ቡድን ማለትም ለጥብቅ (Control) ለሙከራ (Exprmental) ሳይበቃ ሲቀር የሚመረጥ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በአዱስ አበባ መስተዲድር ስር ከሚገኙ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ትምህርት ቤቶች መካከል በአሌፋ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ትምህርት ቤት ሲሆን በትምህርት ቤቱ ከሚገኙ የክፍል ደረጃዎች መካከል ለጥናቱ የተመረጠው ክፍል ሰባተኛ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱንና የክፍል ደረጃውን በመምረጥ ረገድ አላማ ተኮር ናሙና (purposive Sampling) ተግባራዊ ተደርጓሌ፡፡ በጥናቱ ተሳታፊ የሆኑት ተማሪዎች በጠቅላይ ናሙና (Comprehensive Sampling) የተመረጡ ሲሆን በዘህም በክፍል ደረጃው የሚማሩ ሁሉም ተማሪዎች (ሰባቱም) በጥናቱ ተካተዋል፡፡ እነዘህ ተማሪዎች በቀጥታ በጥናቱ እንዲሳተፉ የተደረገበት ዋናው ምክንያት ቁጥራቸው ውስንና ከተጠቀሰው በላይ ባለመሆኑ ነው፡፡ለጥናቱ በመረጃ መስብሰቢያ ዘዴነት ተግባር ላይ የዋሉት ፈተና፣ የጽሑፍ መጠይቅና የተማሪዎች የቡድን ተኮር ውይይት ናቸው፡፡ ፈተናው ቅድመና ድህረ ትምህርት ፈተና ሲሆን ዋነኛ አላማውም ተጠኚ ተማሪዎች በመስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ ከመማራቸው በፈትና በኋላ የነበራቸው የመጻፍ ክሂል ትምህርት የመማር ፍላጎት ምን ያህል ጉልህ ልዩነት እንዳሳየ ማረጋገጥ ነው፡፡ ሌላኛው የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሆኖ ያገለገለው የቡዴን ተኮር ውይይት ሲሆን አላማው ደግሞ በፈተናና በጽሁፍ መጠይቅ ለተሰበሰቡት መረጃዎች ማጠናከሪያ ሀሳብ ማስገኘት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የመጻፍ ክሂል ፈተናውና የጽሁፍ መጠይቁ በቅድመና ድህረ ትምህርት ትግበራው ላይ ለተጠኚዎች ቀርበው መረጃ የተሰበሰበባቸው ሲሆን የተገኘው ውጤትም በጥንድ ናሙና ቲ- ቴስት (Paird sample t-test) መጠናዊ የመረጃ መተንተኛ ስሌት ተሰሌቶ ( P< 0.05) የሆነ የጉልህነት መለያ ውጤት ተገኝቷል፡፡ በአንጻሩ በቡድን ተኮር ውይይቱ የተሰበሰበው መረጃም በአይነታዊ የመረጃ
መተንተኛ ዘዴ ተተንትኖ በፈተናውና በጽሁፍ መጠይቁ የተገኘውን የሚደግፍ ውጤት አስገኝቷል ፡፡ በአጠቃላይ በሶስቱ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ተሰብስበው ከተተነተኑት መረጃዎች የተገኘው ውጤት የሚያመለክተው መስተጋብራዊ የማስተማሪያ ዘዴ መስማት በተሳናቸው ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ችሎታና የመማር ፍላጎት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ መኖሩንና ተጽዕኖውም አዎንታዊ መሆኑን ነው፡፡