ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል በተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብ እና አደረጃጀት ከመርሀ-ትምህርቶቹ ጋር ያላቸውን ተጣጥሞሽ መፈተሽ

No Thumbnail Available

Date

2022-08

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ በ2014 ዓ.ም. በ ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አማካኝነት በታተሙት የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብ እና አላረጃጀት ከመርሀ-ትምህርቶቹ ጋር ያሊቸውን ተጣጥሞሽ መፈተሸ ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት ሰነድ ፍተሻ የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ በመሆኑ የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል መማሪያ መጻህፍትና የመምህሩ መምሪያ እንዲሁም ለደረጃው የተዘጋጁ መርሀ-ትምህርቶች በመረጃ ምንጭነት አገልግለዋል፡፡ ጥናቱም ቅይጥ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በሰነድ ፌተሻ የተገኙ መረጃዎች በክለሳ ድርሳን ከተነሱ ንዴፈ-ሃሳቦች አኳያ በገላጭ የምርምር ስልት ተተንትነዋል፡፡በተተኳሪዎቹ መጻህፌትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ ያለ የሰዋስው ይዘቶች በመርሀ-ትምህርቱ ውስጥ ከተካተቱት ይዘቶች ጋር በአብዛኛው የሚጣጣሙ መሆናቸውን ከሰነድ ፍተሻው ለማረጋገጥ ተችሎል፡፡ በተተኳሪዎቹ ሰነድች ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች ከሰዋስው ትምህርት አቀራረብ መርሆዎች አኳያ ሲፈተሹ በአብዛኛው ግልጽ፣ ትክክለኛ፣ተገቢነትና ተመጣጣኝነት ያላቸው ቢሆኑም አልፎ አልፎ ግን ግልጽነት የጎደላቸው ማብራሪያዎች፣ ትእዛዞች፣ ምሳሌዎችና መልመጃዎች፤ ስህተት ያለባቸው የሰዋስው ይዘቶች፤ ከክፍል ደረጃው በላይ የሆኑ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች እና ያልተመጣጠኑ ንኡሳን ይዘቶች እንዳሉ በተደረገው ሰነድ ፍተሻ ለማረጋገጥ ተችሎል፡፡ በተተኳሪዎቹ ሰነድች ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶችና አደረጃጀት በአብዛኛው ተከታታይነትና ተለጣጣቂነት ያላቸው ሲሆኑ አንዳንድ ይዘቶች ግን ምንም ስፋትና ጥልቀታቸው ሳይጨምር የተደገሙ መሆናቸው በደካማ ጎን የሚያይ ነው፡፡ እንዲሁም ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝርና ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ አደረጃጀትን የተከተለ ቢሆንም በአመዛኙ ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ አደረጃጀት ጎልቶ ታይቶባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የ7ኛና የ8ኛ ክፍሌ መማሪያ መጻህፍትና የመምህሩ መምሪያ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት በአብዛኛው በመርሀ-ትምህርቱ ላይ የተመሠረቱ ቢሆንም የተወሰኑ የሰዋስው ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ዳግሞ በሚገባ መርሀትምህርቱ ላይ ተመስርተው ያለመቅረባቸውን ከተደረገው ሰነድ ፍተሻ ለማረጋገጥ ተችሎል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግም በጥናቱ ማጠናቀቂያ ላይ ክፍተቱን ለመሙላት ያስችላሉ የተባለ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

Description

Keywords

የሰዋስው ትምህርት:የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት

Citation