Amharic Language, Literature and Folklore
Permanent URI for this collection
Browse
Browsing Amharic Language, Literature and Folklore by Subject "ለውጥ ሰሞን የዘፈን ግጥሞች"
Now showing 1 - 1 of 1
Results Per Page
Sort Options
Item በለውጥ ሰሞን ላይ አተኩረው የተዘፈኑ የአማርኛ የዘፈን ግጥሞች ጭብጥ ትንተና (ከ1966-1986 ዓ.ም.)(አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ, 2022-06) ተሾመ ብርሃኑ; አየለ ፍቅሬ (PhD)ይህ ጥናት፥ በለውጥ ሰሞን ላይ አተኩረው የተዘፈኑ የአማርኛ የዘፈን ግጥሞች ጭብጥ ትንተና (ከ1966-1986 ዓ.ም) በሚል ርዕስ የተደረገ ነው። የጥናቱ ዋና ዓላማ፥ በለውጥ ሰሞን ላይ አተኩረው የተዘፈኑ የአማርኛ የዘፈን ግጥሞች ለውጡን በተመለከተ ያነሷቸውን አቢይ ጭብጦች በመተንተን የተገኘውን ውጤት ማቅረብ ነው። ጥናቱ ዓይነታዊ የጥናት ዘዴን (Qualitative) በመጠቀም የተሰራ ነው፡፡ አቀራረቡ ቴክስት ትንተና (textual analysis) ሲሆን፤ ስልቱ ፍካሬ (interpretative) ነው። የጥናቱ የመረጃ ምንጮች፡- አንድም ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(EBC) ክምችት ክፍል የተገኙ የሸክላና የካሴት የአማርኛ ዘፈኖችን ወደጽሁፍ በመቀየር የተገኘ ነው፡፡ አንድም ከተለያዩ የህትመት ውጤቶች (ለምሳሌ- መጽሐፍት፣ መጽሔቶች) የዘፈን ግጥሞችን በመሰብሰብ የተገኘ ነው፡፡ እነዚህ የዘፈን ግጥሞች በየተዘፈኑበት ዘመን በመከፋፈል ያነሷቸውን ዋና ዋና ጭብጦች ከተግባራዊነት (Functionalism) ንድፈ ሀሳብ አንጻር ተተንትነዋል፡፡ ጥናቱ በ1966 ዓ.ም. እና በ1983 ዓ.ም. ሁለት የለውጥ ጊዜያት ላይ ትኩረቱን በማድረግ የተሰራ ሲሆን፤ ይህም የለውጥ ዋዜማ፣ የለውጥ ጊዜና የለውጥ ማግስት በሚል ንዑሳን ክፍሎች የተከፋፈለ ነው፡፡ በዚህ ጥናት፤ የለውጥ ዋዜማ ማለት፥ ለውጥ ከመከሰቱ አንድ ዓመት በፊት ጀምሮ፤ ለውጥ እስከተካሄደበት ቀን ድረስ ያለውን ጊዜ የሚያካትት ነው። የለውጥ ጊዜ ሲባል ደግሞ፥ ለውጥ ከተከሰተበት እለት ጀምሮ ወደፊት ያሉትን ሁለት ዓመታት የሚመለከት ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደፊት የሚቆጠሩት ሌሎች ሁለት ዓመታት ደግሞ፤ የለውጥ ማግስት በሚል የተጠኑ ናቸው። በዚህ ጥናት ግኝት፥ በለውጥ ሰሞን ላይ የተዘፈኑ ዘፈኖች፥ በመጀመርያ በድጋፍና ያለፈውን ገዢ በመውቀስ የሚገለጹ ሲሆኑ፤ ሁለተኛው በጥርጣሬ፣ በኢኮኖሚ ጉዳይ፣ በኤርትራ ጉዳይ እና በሀገር ሰላምና አንድነት ላይ አተኩረው የተዘፈኑ ግጥሞች ናቸው፡፡