በለውጥ ሰሞን ላይ አተኩረው የተዘፈኑ የአማርኛ የዘፈን ግጥሞች ጭብጥ ትንተና (ከ1966-1986 ዓ.ም.)

No Thumbnail Available

Date

2022-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት፥ በለውጥ ሰሞን ላይ አተኩረው የተዘፈኑ የአማርኛ የዘፈን ግጥሞች ጭብጥ ትንተና (ከ1966-1986 ዓ.ም) በሚል ርዕስ የተደረገ ነው። የጥናቱ ዋና ዓላማ፥ በለውጥ ሰሞን ላይ አተኩረው የተዘፈኑ የአማርኛ የዘፈን ግጥሞች ለውጡን በተመለከተ ያነሷቸውን አቢይ ጭብጦች በመተንተን የተገኘውን ውጤት ማቅረብ ነው። ጥናቱ ዓይነታዊ የጥናት ዘዴን (Qualitative) በመጠቀም የተሰራ ነው፡፡ አቀራረቡ ቴክስት ትንተና (textual analysis) ሲሆን፤ ስልቱ ፍካሬ (interpretative) ነው። የጥናቱ የመረጃ ምንጮች፡- አንድም ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(EBC) ክምችት ክፍል የተገኙ የሸክላና የካሴት የአማርኛ ዘፈኖችን ወደጽሁፍ በመቀየር የተገኘ ነው፡፡ አንድም ከተለያዩ የህትመት ውጤቶች (ለምሳሌ- መጽሐፍት፣ መጽሔቶች) የዘፈን ግጥሞችን በመሰብሰብ የተገኘ ነው፡፡ እነዚህ የዘፈን ግጥሞች በየተዘፈኑበት ዘመን በመከፋፈል ያነሷቸውን ዋና ዋና ጭብጦች ከተግባራዊነት (Functionalism) ንድፈ ሀሳብ አንጻር ተተንትነዋል፡፡ ጥናቱ በ1966 ዓ.ም. እና በ1983 ዓ.ም. ሁለት የለውጥ ጊዜያት ላይ ትኩረቱን በማድረግ የተሰራ ሲሆን፤ ይህም የለውጥ ዋዜማ፣ የለውጥ ጊዜና የለውጥ ማግስት በሚል ንዑሳን ክፍሎች የተከፋፈለ ነው፡፡ በዚህ ጥናት፤ የለውጥ ዋዜማ ማለት፥ ለውጥ ከመከሰቱ አንድ ዓመት በፊት ጀምሮ፤ ለውጥ እስከተካሄደበት ቀን ድረስ ያለውን ጊዜ የሚያካትት ነው። የለውጥ ጊዜ ሲባል ደግሞ፥ ለውጥ ከተከሰተበት እለት ጀምሮ ወደፊት ያሉትን ሁለት ዓመታት የሚመለከት ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደፊት የሚቆጠሩት ሌሎች ሁለት ዓመታት ደግሞ፤ የለውጥ ማግስት በሚል የተጠኑ ናቸው። በዚህ ጥናት ግኝት፥ በለውጥ ሰሞን ላይ የተዘፈኑ ዘፈኖች፥ በመጀመርያ በድጋፍና ያለፈውን ገዢ በመውቀስ የሚገለጹ ሲሆኑ፤ ሁለተኛው በጥርጣሬ፣ በኢኮኖሚ ጉዳይ፣ በኤርትራ ጉዳይ እና በሀገር ሰላምና አንድነት ላይ አተኩረው የተዘፈኑ ግጥሞች ናቸው፡፡

Description

Keywords

ለውጥ ሰሞን የዘፈን ግጥሞች

Citation