በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት በሚፅፉበት ጊዜ የሚፈፅሟቸው ስህተቶችና የስህተት ምንጮች ትንተና፤ (በቀርሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-10

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዓላማ አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈፅማቸውን ስህተቶች እና የስህተት ምንጮችን መተንተን ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት በመረጃ መሰብሰቢያነት ያገለገሉ መሳሪያዎች በተማሪዎች የተጻፉ ድርሰቶች እና የመምህራን ቃለ- መጠይቅ ናቸው፡፡ መረጃዎች ከተሰበሰቡና አስፈላጊው አደረጃጀት ከተደረገ በኋላ በቲ- ቴስት ትንተና እና ገላጭ በሆነ መንገድ በመተንተን የቀረበ ሲሆን ከትንተናው የተገኘው ውጤትም በቲ- ቴስት ስሌት ተሰልቶ8.35 መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም የተገኘው ውጤት የሚያሳየው መምህራን ከድርሰት ልምምድ በፊትና በኋላ የሚገኘው ውጤት የተሻለ መሆኑን ሲሆን ድርሰት ሲያፅፉ ግብዓት የሚሆናቸውን ትምርት መስጠት የሚገባ መሆኑን ነው፡፡ ተማሪና መምህር የማይለያዩ በመሆናቸውም የ9ኛ ክፍልን አማርኛ ትምህርት ሲሚያስተምሩ መምህራን ቃለመጠይቅ በማቅረብ ስለተማሪዎቻቸው ድርሰት የመፃፍ ችሎታና በሚፅፉበት ጊዜም የሚሰሯቸውን ስህተቶች የተመለከቱ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው ሲሆን የተገነው መረጃ በሚገባ ተተንትኖ የተገኘው ውጤትም ሁኔታ ከስህተቶች በመነሳት ለዚህ ሁሉ ስህተቶች ምንጭ ይሆናሉ ተብለው ከሚታመኑት ውስጥ የቋንቋ ተጽእኖ፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ተጽእኖ፣ የመማር ማስተማር ሂደት እና የስነልቦናዊ ተጽእኖ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም ማጠቃያ እና የተከሰቱትን ስህተቶች ለመቅረፍ ያስችላሉ ተብለው የታመነባቸው የመፍትሔ ሀሳቦች ቀርበው ጥናቱ ተጠናቋል፡፡

Description

Keywords

አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ

Citation