Amharic Language, Literature and Folklore
Permanent URI for this collection
Browse
Browsing Amharic Language, Literature and Folklore by Subject "ሥነ ልቡናዊ ንባብ"
Now showing 1 - 1 of 1
Results Per Page
Sort Options
Item “ልጅነት” በማሕሌትና አለንጋና ምስር፤ ሥነ ልቡናዊ ንባብ(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2006-06) አለበል, ቴዎድሮስ; ገብሬ, ቴዎድሮስ (ረ/ፕ)ይህ ጥናት ልጅነት በማሕሌት እና አለንጋና ምስር፤ ሥነ ልቡናዊ ንባብ በሚል የተደረገ ነው፡፡ የጥናቱ ዘዴ በይነ-ቴክስታዊ ሲሆን ስልቱ ደግሞ ፍካሬ ነው፡፡ ጥናቱ በተመረጡት ቴክስቶች ውስጥ ልጅነት ከሥነ ልቡና ንድፈ ሃሳቦች አንጻር ቢፈተሽ መልካም ነው በሚል ዕምነት የተደረገ ነው፡፡ በቴክስቶቹ የተቀረጹ ልጆች ማኅበረ-ልቡናዊና ሳይኮሴክሿል ማንነት፣ Oedipus complex እና የልቡና ፍርቅነት፣ የጨቅላነት ግንትሮሽ እና የሁለት ሰብዕናዎች መቃየጥ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ሚቶሎጂዎች የተቀዱ መባያዎች ሰብዕናን መርምሮ ለማሳየት ትኩረት የተደረገባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡ ጥናቱ ወዲህ በቴክስቶቹ ውስጥ የተቀረጹ ገጸ-ልጆች የብቸኝነት፣ የመከዳትና የመጣል ስሜት የሚስተዋልባቸው እንደሆኑ፣ ወዲህ ደግሞ የአሳዳጊዎቻቸው ሚና አፍራሽ መሆኑ፣ የጨቅላነት ሳይኮሴክሿል ዕድገት ፊክሴሽንና sadistic displacement ማደሪያዎች እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡ ስለሆነም፣ በእነዚህና በትንተናው ውስጥ በ“ተዘነቁ” ሃሳቦች ልጆቹ ማኅበረ-ባህላዊ ኃላፊነትን መሸከም የማይችሉ እንደሆኑ ለማጠቃለል ተሞክሯል፡፡ በመጨረሻም በቴክስቶቹ ውስጥ ልጆቹ የተቀረጹት፣ ማኅበረ-ባህላዊ ሥርዓቶችና ተፈጥሯዊ ማንነቶች በመጎራበት ነው ብሎ ማጠቃለል ይቻላል፡፡ IV