Amharic Language, Literature and Folklore
Permanent URI for this collection
Browse
Browsing Amharic Language, Literature and Folklore by Subject "መረዳትና የመፃፍ ክሂሎት"
Now showing 1 - 1 of 1
Results Per Page
Sort Options
Item አንብቦ መረዳትና የመፃፍ ክሂል ቅንጅታዊ አቀራረብ ትንተና (በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በጢያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል መምህራን ተተኳሪነት)(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2016-12) ወንዱ ፀጋ; ተስፋዬ ሸዋዬየዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በጢያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍልአራት አማርኛ ቋንቋ መምህራን ትኩረቱን በማድረግ የአንብቦ መረዳትና የመፃፍ ክሂሎችን ቅንጅታዊ አቀራረብ መተንተን ነው፡፡ የዓላማውን ውጤት ለማስገኘትም ቃለ መጠይቅና ምልከታ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በዚህም አጥኚው ተምህርት ቤትን በአመቺ(የግኝት) ናሙና፣ የክፍል ደረጃን በወሳኝ ናሙና ፣ መምህራንን በጠቅላይ ንሙና ዘዴ መርጧል።በአራት ተተኳሪ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በክፍል ውስጥ በመገኘት ለአራት መማሪያ ክፍሎች ለእያንዳንዱ ሁለት ሁለት ምልከታ በማድረግና ለአራት መምህራን ቃለ መጠይቅ በማድረግ መረጃዎች ተሰብስበዋል። በእነዚህ መሳሪያዎች የተሰበሰቡት መረጃዎች ተተንትነው ውጤታቸው ተግምግሟል። ከጥናቱ ዓላማ በመነሳት በሚከተለው መልኩ ጥናቱን በማጠቃለል ማቅረብ ተችሏል፡፡ መምህራን የማብራራትና መተርጎም፣ መተንበይና መገመት፣ ጥያቄ የመጠየቅ እና የማጠቃለል ብልሃቶችን እየቀያየሩ ለመጠቀም እንደሚሞክሩ ነው ከቃለ መጠይቁ መረዳት የተቻለው። አንብቦ የመረዳትንና የመጻፍን ክሂሎችን አቀናጅቶ መስጠት ግን የሁለት ክሂሎችን ችሎታ እንደሚያጎናጽፍ ጥናቱ አረጋግጧል። በመሆኑም ለተማሪዎች ክሂሎች በተናጠል ከሚቀርቡ ይልቅ አንብቦ መረዳትና መጻፍ፣ ማዳመጥና መናገር ክሂሎች እየተቀናጁ እንዲማሩ እንድማሩ ቢደረግ የሚል አቅጣጫ ጥናቱ አስቀምጧል፡፡ እንዲሁም የማስተማሪያ ስልቶችን እየቀያየሩ መጠቀም ተማሪዎች ተነሳሽነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ እንደሆነ ጥናቱ የመላክታል።ስለዚህ መምህራን አንብቦ የመረዳትና መጻፍ ክሂሎችን አቀናጅተው ሲያስተምሩ በየትኛው ስልት ማቅረብ እንዳለባቸው ወስነው መቅረብ አለባቸው፡፡ ከቀረቡት የጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም ቀጥለው የሚቀርቡት የመፍትሔ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡ መምህራን አንብቦ የመረዳትና የመጻፍ ክሂሎችን በቅንጅት በሚያቀርቡበት ወቅት በቅንጅት የሚቀርቡበትን ዓላማ በመናገር ቢጀምሩ፣ አንብቦ መረዳትንና የመጻፍ ክሂልን ሲስተምሩ የማስተማሪያ ዘዴያቸውንና የአቀራረብ ስልታቸውን ከማስተማራቸው በፊት ወስነው ቢቀርቡ፤ መምህራን የማብራራትና መተርጎም፣ መተንበይና መገመት፣ ጥያቄ የመጠየቅ እና የማጠቃለል ብልሃቶችን እየቀያየሩ ለመጠቀም እንደሚጠቀሙ ከጥናቱ ውጤት መረዳት ይቻላል። ስለዙህ ክሂሎችን በተናጠል ከማስተማር ልምድ ወጥተው አንብቦ መረዳትንና መጻፍን አቀናጅተው ቢያሰተምሩ በአንድ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሁለት ክሂሎችን በማስተማር የአንብቦ መረዳትና መፃፍ ችሎታዎችንና ተግባቦቶችን ለተማሪዎች የሚያጎናጽፍ መሆኑን ይህ ጥናት ያሳያል