Amharic Language, Literature and Folklore
Permanent URI for this collection
Browse
Browsing Amharic Language, Literature and Folklore by Author "ለምለም ከበደ"
Now showing 1 - 1 of 1
Results Per Page
Sort Options
Item የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎችን ለማሻሻል ያለው ሚና ትንተና (በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ 9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተከሪነት)(አዲስ አበባ ዩኒቨርስት, 2016-11) ለምለም ከበደ; ዳዊት ፍሬህይወት (ዶ/ ር )የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በጉራጌ ዞን በገደባኖ ሁለተኛ ደረጃ ትምህረት ቤት የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎችን ለማሻሻል ያለው ሚና መተነን ነው። የጥናቱ የአጠናን ዘዴ ቅይጥ የምርምር ዘዴ ሲሆን በዋናነት አይነታዊ ምርምርና በደጋፊነት ደግሞ መጠናዊ ምርምር ዘዴን አካቷል፡፡ የጥናቱ ሂደትም ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የክፍል ውስጥ ምልከታ፣ ለተማሪዎች የቅድመና የድህረ ትምህርት ፈተና እና ቃል መጠይቅ ፤ ለመምህራን ደግሞ በቃለ-መጠይቅ መረጃ ተሰብስባል፡፡ የተገኙት መረጃዎችም በሰንጠረዥ ተደራጅተው በቁጥርና በመቶኛ ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ እንዲደዚሁም በቃል መጠይቅ የተገኙ መረጃዎችም በምልከታ ለተገኙ መረጃዎች አጋዥ ሆነው ተተንትነዋል፡፡ የመከራ ቡድኖቹም ቅድመ ትምህርት ፈተና ተፈትነዋል። ለእንድ ወር በእቅድ የተደገፍ ትምህርት ተምረው ድህረ ህርት ፈተና ተፈትናዋል። በቡድኖቹ መካከል ያለውን ልዩነት ለማረጋገጥ የፈተናእ ውጤት በአማካይ ተስልቶ ተነፃፅሯል ። ከተማሪው የተገኘው ቃለ መጠይቅምላሽና ክንውን ምልከታው ተመሳሳይነት አረጋግጧል ።ሰለዚህ የማንበብና ይመፃፍ ክሂሎች ካላችው ትስስርና ዝምንድና አንፃር በተናጥል ከመቅረብ ይልቅ በቅንጅት ቢቀርብ ለክሂሌችን መጒልበት የላቀ እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል።በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች አመካይነት በተገኘ የውጤት ትንተና መሰረትም መምህራን የማንበብና የመፃፍ ክሂልን በቅንጅት ለማስተማር እየተገበሩት ያለው አካሄድ ክሂሎቹን ለማቀናጀትና ለማዳበር ያላቸው ሚና ዝቅተኛ እንደሆነ መምህራን ከተማሪዎች ችሎታ፣ ዳራና ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ ይዘቶች፲ን እንደማያቀርቡ፣ ከመማሪያ መጽሀፍ በተጨማሪ ለዓላማው ተስማሚ የሆኑ አጋዥ መሳሪያዎችን እንደማይሰጡ ተረጋግጧል፡፡ የመማሪያ መጽሐፍ የማንበብና የመፃፍ ክሂልን በቅንጅት ለማቅረብ አመቺ እንደልሆነና ለ፸፻መምህራን ስለኪሂሎች ቅንጅታዊ አቀራረብ አጫጭር ስልጠናዎችንና ዋረክሽፖችን አለሰመስጠት ተፅእኖ እንዳሳደረባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተገኘው የትንተና ውጤት እንደሚያሳየው የማንበብና የመፃፍ ክሂልን በቅንጅት ማስተማር ዘዴ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡