Amharic Language, Literature and Folklore
Permanent URI for this collection
Browse
Browsing Amharic Language, Literature and Folklore by Author "ሀብታሙ ወንድሙ"
Now showing 1 - 1 of 1
Results Per Page
Sort Options
Item ባህልና ልማት በበርታ ብሔረሰብ(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2007-06) ስንቅነሽ አጣለ ; ሀብታሙ ወንድሙየዚህ ጥናት ዋነኛ ዓላማ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ነባር ብሔረሰቦች ከሚባሉት መካከል የበርታን ብሔረሰብ ባህል በማጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ታቅደው እንዲተገበሩ የሚሰራጩ የልማት ዕቅዶችን ለመተግበር የብሔረሰቡ ባህል ለአካባቢው ልማትም ሆነ በልማት ወደ ኋላ መቅረት ያደረገው አስተዋጽኦ ወይም ተፅዕኖ ይኖር እንደሆነ መመርመርና ባህላዊ ጉዳዮችን የልማት መሣሪያ በማድረግ የአካባቢውን ልማት ለማፋጠን የሚቻልበትን መንገድ ማሳየት ነው። ጥናቱ ዓይነታዊ (Qualitative) የአጠናን ዘዴን ተከትሎ የተደረገ ሆኖ ተንታኝ (Interpretative) የአጠናን ስልትን የሚከተል ነው። በጥናቱ የበርታ ብሔረሰብ ከሚኖርበት አሶሳ ዞን ስምንት ወረዳዎች ውስጥ አራቱን በመምረጥ በቃለ መጠይቅ፣ በተሳትፎአዊ ምልከታና በተተኳሪ ቡድን ውይይት መረጃዎች ተሰብስበው ተተንትነዋል። በመስክ ቆይታው እንዳጋጠመው ምቹ ሁኔታም በየቀበሌዎቹ የተለያየ ቁጥር ያላቸው ሃያ ስምንት ሴቶችና አርባ ስምንት ወንዶች በጠቅላላው ሰባ ስድስት ሰዎች መረጃ በመስጠት ተሳትፈዋል። ከነዚህ ውሰጥ አሥራ አንድ ሴቶችና ሃያ ሦስት ወንዶች በድምሩ ሰላሳ አራት ሰዎች በቃለ መጠይቅ የተሳተፉ ሲሆን በዋና መረጃ ሰጪነት የተሳተፉት ጥንት የማህበረሰቡ መሪዎች የነበሩት ሰዎች ቤተሰቦች ሶስት ወንዶችንና ሁለት ሴቶችን ይጨምራል። በጥናቱ የበርታ ብሔረሰብ የማንነቱ መገለጫዎችና የራሱ የሆኑ የጋብቻ፣ የልደትና ሞት ሥርዓቶች፣ ሀገረሰባዊ ልማዶች፣ ክብረበዓላት፣ የአምልኮ ሥርዓቶችና ባህላዊ መድሃኒቶችም እንዳሉት ተረጋግጧል። በብሔረሰቡ ባህል ቢያሳድጓቸውና ቢያጎለብቷቸው