Amharic Language, Literature and Folklore
Permanent URI for this collection
Browse
Browsing Amharic Language, Literature and Folklore by Author "ሀሰን, አህመድ"
Now showing 1 - 1 of 1
Results Per Page
Sort Options
Item በቀይት ንዑስ ወረዳ የሚከወኑ ሀገረሰባዊ እምነቶች(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ, 2007-01) ታደሰ, ፀዳለ; ሀሰን, አህመድይህ ጥናት ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በባሶና ወራና ወረዳ ስር በሚገኘው የቀይት ንዑስ ወረዳ ውስጥ በሚከወኑ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች ላይ ነው፡፡ የጥናት ወረቀቱ ርዕስ ‘በቀይት ንዕስ ወረዳ የሚከወኑ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች’ የሚል ሲሆን በስሩ አምስት ሀገረሰባዊ ዕምነቶች ተዳሰዋል፡፡ እነዚህም ዕምነቶች ጫት መቀቀል፣ ጭዳ፣ አድባር፣ ቦረንትቻ እና አቴቴ/ፈጫሳ ሲሰኙ መነሻቸው፣ ፋይዳቸው፣ ሀይማኖታዊ ትስስራቸው፣ ከበራቸው እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ለዕምነቶቹ ያለው አመለካከት በዚህ የጥናት ወረቀት ውስጥ ተዳሷል፡፡ ዋና አላማውም የእነዚህን ዕምነቶች መነሻ፣ ይዘትና አከባበር ማሳየት ነው፡፡ ለጥናቱ በግብዐትነት ያገለገሉት ከቀዳማይና ካልኣይ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ሲሆኑ በመረጃ መሰብሰቢያነት ደግሞ በዋናነት አገልግሎት ላይ የዋሉት ምልከታና ቃለምልልስ እንዲሁም የቡድን ውይይት ናቸው፡፡ በእነዚህ ሶስት ዘዴዎች ከ23 የመረጃ ሰጪዎች መረጃ የተሰበሰበ ሲሆን መረጃ ሰጪዎቹ የተመረጡት ባሳዩት ፈቃደኝነት ነው፡፡ ከመስክ የተሰበሰቡት መረጃዎች ደግሞ ገላጭ በሆነ የትንተና ዘዴ ተተንትነው እና በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች ተከፍለው ቀርበዋል፡፡ መረጃዎቹ የተተነተኑት በCathrine Bell የከበራ አይነቶችን እና በPascal Boyer & Pierre Liénard የከበራ መገለጫዎች ፅንሰ ሀሳቦች ተቃኝተው ነው፡፡ በተገኘው መረጃ መሰረት በተጠኚው አካባቢ የተጠቀሱት አምስት ሀገረሰባዊ ዕምነቶች