ተሳታፊነት ጭምትነት የሰብእና አይነት ከድርሰት መጸፍና ከአንብቦ መረዳት ችሎታት ጋር ያለው ተዛምዶ፤ በሶስት ኮሌጀች ተማሪዎች ላይ የተደረገ ጥናት

No Thumbnail Available

Date

1988-05

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

በአዲሰ አበባ ዪኒቨርሲቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና አላማ በተሳታፈነት -ጭምትነት የሰብእና አይነት (EXtroversion-Lntroversion) እና በድርሰት መጸፍና አንብቦ መረዳት ችሎታዎች መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡ተጠኝዎቹ በ1988 ዓ.ም የኮተቤና የባህር ዳርመማ ኮሌጀች የመደበኛው ፕርግራምና የቋንቋዎች ጥናት ተቋም የማ ታው ፕርግራም የአማርኛ ትምህርት ክፍል የዲፕሎማ ፕሮግራም የአንደኛ አመት ተማሪዎች ናቸው፡፡ በሶስቱ ኮሌጀች በተጠቀሰው ፕሮግራም የሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ በጥናቱ ታቅፈው፡፡ የአይሲንክ የሰብእና መሊያን እንዲምሉ፤ ድርሰት እንዲጽፍና የአንብቦ መረዳት ፈተና እንዲወስዱ ተደርጎ ለጥናቱ አሰፈላጊ መረጃዎች ተሰብሰበዋል፡፡ ተሳታፊነት -ጭምትነት ከድርሰት መጸፍና ከአናብቦ መረዳት ችሎታ ጋረ ባለው ዝምድና ላይ እድሜና ጾታ ያላቸውን ተጽእኖ ለመመርመር test ተግባራዊ ተደርጓ ል፡፡በዚህም እድሜና ጾታ በተሳታፊነት -ጭምትነትና በድርሰት መጻፍና በአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ያላቸው ተጽአኖ አስተማማኝ አለመሆኑን የጥናቱ ውጤት አመልክቷል፡፡ የሶስቱም ኮሌጆች ተጠኝዎች ዳራ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ፤ባህላዊ፤ ወዘተ… የተለያየ እንደመሆኑ የተጠኝዎች የሰብእና አይነትና የድርሰት መጸፋና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ በተናጠል ተሰልቷል፡፡ ተሳታፊነት - ጭምትነት ከአርብቦ መረዳት ችሎታ ጋረ ያለውን ዝምድና አሰመልክቶ በሶስቱም ኮሉጆች ተጠኝዎች ላይ የተሰላው በሁለቱ መካከል አሰተማማኝ ተዛምዶ አለመኖሩን አመልክቷል፡፡ በባህር ዳር መማ ኮሌጅና በቋጥ ተቋም በድርሰት መጻፍ ችሎታ ጭምቶች ከተሳታፊዎች በልጠው ተገኘተዋል፡፡ ይሁን እንጃ በሁለቱም ኮሌጀች የታየው የጭምቶች የችሎታ ልቀት ቀመር ሲሰላ አሰተማማኘ ሆኖ አልተገኘም፡፡ በኮተቤ መማኮሎጅ ግን በድርሰት መጸፋ ችሎታ ጭምቶች አሰተማማኘ በሆነ ደረጃ ከተሳታፊዎች በልጠዋል፡፡ ምንም እንኳን አስተማማኝ ባይሆንም በባህር ዳር መማ ኮሌጅና በቋጥ ተቋም የተገኝው የጭምቶች በድርሰት መጸፍ ችሎታ ከተሳታፊዎች የበለጠ ውጤት ማስመዝገብና በኮተቤ መማኮሌጅ የተገኘው አሰተማማኝ ልዩነት ተደምሮ የጥናቱን ውጤት ጭምቶች ከተሳፊዎች የበለጠ የድርሰት መጻፍ ችሎታ እንዳላቸው እንዲያመለክት አድርጎታል፡፡ በዚህም የተነሳ የዚህ ጥናት መደምደሚያ፤ ዖታና እድሜ ከተሳታፊነት ጭምትነት የሰብእና አይነትና ከድርሰት መጸፍም ሆነ ከአንብቦ መረዳት ችሎታ አሰተማማኝ ልዩነት አለመኖሩንና በድርሰት መጸፍ ችሎጻ ጭምቶች ከተሳታፊዎች የተሻሉ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡ ከዚህ በመነሳት በየደረጃው ያሉ የቋንቋ መምህራንና የቋንቋ ማስተማሪያ መጸህፍት አዘጋጆች የሰብእና አይነት ከተለያዩ የቋንቋ ክሒሎች ችሎታዎች ጋር በተለያ የደረጃ ዝምድና ሊኖረው እንደሚችል በመገመት በክፍል ውስጥ የማስተማር ክንውን ቅደም ተከተልና በመማሪያ መጸሀፍት የይዘት አደርጃጀት ላይ ጥናትን መሠረት ያደረገ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

Description

Keywords

Citation