የድጋፍ ብልሃቶች በአንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ተፅዕኖ፤ በ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
| dc.contributor.advisor | ፕሮፌሰር ተስፋየ ሸዋየ | |
| dc.contributor.author | ራሔል ሲሳይ ተገኘ | |
| dc.date.accessioned | 2025-07-23T07:35:38Z | |
| dc.date.available | 2025-07-23T07:35:38Z | |
| dc.date.issued | 2016 | |
| dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዓላማ የድጋፍ ብልሃቶች የተማሪዎችን በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ መፈተሸ ነበር፡፡ ጥናቱ በዓይነቱ ቅደምተከተላው ቅይጥ (በአመዛኙ መጠናዊ) ሲሆን ቅድመና ድህረ ትምህርት በለቁጥጥር ቡድን ፍትነት ቡድን ፍትነት መሰል ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ በ2015 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር፡ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአድስተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ መረጃዎችን ለመሰብሰብም አንብቦ የመረዳት ችሎታ ፈተናና የግለመር ማንበብ መጠይቅ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ሌላው በአግዥነት ድህረቡድን ተኮር ውይይት ተግባራዊ ሆኗል ፡፡ እንዲሁም ሁለቱ ቡድኖች በተቀመጠላቸው የማስተማሪያ መንገድ መማርቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ምልከታ ተካሂዷል ፡፡በቅድመ ፈተናና መቅድመ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድና ነፃ ቲ-ትስቶች የትንተና ስልት እንዲሁም በድኀረ ፈተናና በድኀረ የጽሑፍ መጠይቅ የተገኙ ውጤቶች በጥንድ፡ ነፃ ቲ- ትስቶችና በአበር ልይይት ትንተና ስልቶች ተተንትነዋል፡፡ በተጨማሪም ከድህረቡድን ተኮር ውይይት የተገኙት ውጤቶችም እንደሚያመለክቱት በቅድመፈተናና በቅድመየጽሑፍ መጠይቅ ቡድኖች ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡ ሲሆን በድኀረ የጽሑፍ መጠይቅ ገለመር ማንበብ የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች ከቁጥጥት ቡድኑ ተማሪዎች ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይተዋል (P= <0.05):: ይህም ውጤት በድጋፍ ብልሀቶች መማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና ግለመር ማንበብን ከማሻሻል አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁሟል፡፡ በተገኙት ውጤቶች በመመስረት የመፍትሄ ሀሳቦችና የጥናት ጥቆማዎች ተሰጥተዋል፡፡ | |
| dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/5675 | |
| dc.language.iso | am | |
| dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ | |
| dc.subject | የድጋፍ ብልሃቶች በአንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ተፅዕኖ | |
| dc.title | የድጋፍ ብልሃቶች በአንብቦ የመረዳት ችሎታ እና ግለመር ማንበብ ላይ ተፅዕኖ፤ በ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት | |
| dc.type | Thesis |