ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት በሃላባ ብሄረሰብ

No Thumbnail Available

Date

2006-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

ይህ ጥናት “ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት በሃላባ ብሄረሰብ ” በሚል ርዕስ የተሰራ ነው፡፡ በጥናቱ ውስጥም ለጥናቱ የሚሆን መረጃ የተሰበሰበው የሀላባን ብሄረሰብ ባህል ጠንቅቀው ከሚያውቁ ሶስት ቁልፍና አስር ንዑሳን መረጃ ሰጪዎች እንደሆነ ተገልጿል፡፡ መረጃዎቹም የተሰበሰቡት ቃለ መጠይቅ በማድረግና የሀላባ ኦገቴ በሚሰበሰብበት ዐውድ ላይ በመገኘት በምልከታ መሆኑ ሰፍሯል ፡፡ የተሰበሰቡትን መረጃዎችም ገላጭ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡ መረጃዎቹም የሀላባ ኦገቴ ግጭቶችን ለመፍታት ከመጀመሪያ እስከማለቂያው ድረስ ምን አይነት ሂደት እንደሚከተሉ፣ ምን አይነት ስርዓት እንደሚከወን በማሳየት ቀርቧል፡፡ በመቀጠልም በሃላባ ብሄረሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶች ምን ምን እንደሆኑና እያንዳንዳቸውንም ለመፍታት የሚከወኑትን ሰርዓቶች በሚገልጽ መልኩ ቀርቦበታል፡፡ በሃላባ ብሄረሰብ ውስጥ ባህላዊው የግጭት መፍቻ ስርዓት በሃቀኝነትና በታማኝነት ህብረተሰቡን እያገለገለ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩትን ግጭቶች ስራዬ ብሎ በመስራቱ ምክንያት ባህላዊ ተቋሙ ከመደበኛው የፍርድ ተቋም ይልቅ በህዝቡ የተሻለ ተመራጭ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡ በስርዓቱም ከግጭት በኋላ ዕርቅ ሲፈጸም እንደ ጥፋቱ መጠን ካሳ ይከፈላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በዳይ ካሳውን እስኪከፍል ድረስ ዋስ(ሩበቴ) በመጥራት እንደሚቆይ ተገልጾበታል፡፡ በብሄረሰቡ የባህላዊ ተቋሙ ውሳኔ በጣም የሚከበርና የሚፈጸም ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን በባህላዊ ህጉም ሆነ በሽማግሌዎቹ እርግማን የከፋ ነገር እንደሚደርስ ተቀምጧል፡፡ የሃላባ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ስርዓት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩትን ግጭቶች በመፍታት፣ በብሄረሰቡ ውስጥ ያሉ ችግረኞችን በመርዳት፣ ከመደበኛው የፍትህ ተቋም ጋር በመተባበር ህዝቡ በሰላምና በመተሳሰብ እንዲኖር ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም መንግስትና የሚመለከተው ክፍል ባህላዊ ተቋሙ የላቀ ስራ እንዲሰራና ሃይማኖታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ና ማህበረ-ባህላዊ እሴትነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያመላክቱ አስተያየቶችም ተሰጥተውበታል፡፡

Description

Keywords

የግጭት አፈታት ሥርዓት

Citation