በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በአራት ትምህርት ቤቶች የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበር ግምገማ
No Thumbnail Available
Date
2010-08
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
Addis Ababa University
Abstract
የቋንቋ ክሂሎች የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ክንውን በተገቢው መንገድ የሚተገበር
ከሆነ የቋንቋውን ትምህርት ዓላማ ለማሳካትና በተማሪዎች ላይ የተፈለገውን ለውጥ ለማምጣት
ያለው አስተዋፅኦ አሌ የማይባል ነው፡፡ የዚህም ጥናት ዓላማም የመናገር ክሂል ትምህርት
የክፍል ውስጥ አተገባበርን መመርመር ነው፡፡ በዚህ መሰረት በዋናነት በመምህራን ላይ ትኩረት
ያደረገ የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ምልከታ ተከናውነዋል፡፡ በተጨማሪም መምህራንና
ተማሪዎችም የጽሑፍ መጠየቅ እንዲሞሉ የተደርጓል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ስድስት
የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አራት በመምረጥና ከአራቱ ትምህርት ቤቶች
አራት የአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በአላማዊ ናሙና አማካይነት ተመርጠዋል፡፡
የአራቱ ትምህርት ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ መምህራንና ከየትምህርት ቤቱ የተመረጡ 120
የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የጽሑፍ መጠይቅ እንዲሞሉ ተደርጓል፡፡ ከመልክታና ከጽሑፍ
መጠይቅ ከተገኙት መረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው ጥቂት መምህራን በክፍል ውስጥ
የመማር ማስተማሩን ሂደት በጥንድ ወይም በቡድን ሥራ እንዲታገዝ አለመሞከራቸውን'
በቋንቋው ተጠቅመው በንግግር ሀሳባቸውን በነፃ የሚገልጹበትን ሁኔታ አለማመቻቸታውን'
የመናገር ማስተማሪያ ደረጃዎችን በተገቢው መንገድ አለማከናወናቸውን' በተጨማሪም
ከመማሪያ መጽሐፉ ጎን ለጎን የተማሪዎችን ፍላጎት ሊያነሳሳ የሚችል ተግባር በጥንቃቄ
አለመመረጡ' የዕለቱን የመናገር ክሂል ትምህርት ርእሰ ጉዳይ ግልጽ በሆነና በማይረሳ መልኩ
አለመቅረቡ' ለሁሉም ተማሪዎች እኩል እድል አለመስጠቱ እና ለመናገር የማይደፍሩ
ተማሪዎችን ለማበረታታት የተሻለ ሙከራ አለመደረጉ፤ በመጨረሻም በመማር ማስተማሩ
ሂደት የመናገር ክሂሉን ለማዳበር ያሉበትን ችግሮች ለማቃለል የመናገር ክሂል ተግባር
ከመከናወኑ በፊት የትምህርት ዓላማ በዝርዝር እንዲቀርብ ቢደረግ፣ተማሪዎች ወደዋናው
የመናገር ክሂል ትምህርት ከመግባታቸው በፊት የማነቃቂያ ትምህርት ቢሰጣቸው፣ የመናገር
ክሂልን ለማሳደግ የቀረቡትን ተግባራት ለማለማመድ የሚሰጠው ጊዜ ከመልመጃዎቹ ስፋት
ጋር መታየት እናዳለበት የመፍትሄ ሃሳብ ቀርቧል፡፡
Description
Keywords
የመናገር ክሂሎት ትምህርት የክፍል ውስጥ አተገባበርን መመርመር ነው፡፡