በአማርኛ ቋንቋ አፊቸውን የፈቱ ተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ፍተሻ፤ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ቦረና ዞን ነጌሌ ቦረና በ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት አብይ አላማ አፋቸውን በአማርኛ ቋንቋ የፈቱ የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው በምን ደረጃ ላይ እደሚገኝ ማወቅ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በነጌሌ ቦረና ከተማ ከሚገኙ የመንግስት አንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል ትምህርት ቤቶች ውስጥ በናሙናነት በተመረጠው አንድ ትምህርት ቤት የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ጥናቱን ለማካሄድ በጥቅም ላይ የዋሉት የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችም ለተማሪዎች የሚሰጠው የአንብቦ መረዳት ፈተና እና የጽሁፍ መጠይቅ ለጥናቱ ዋና መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ሲሆን አጋዥ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ደግሞ ለመምህሯ የቀረበ ቃለ መጠይቅ ናቸው፡፡ በእነዚህ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች የተገኙ መረጃዎች በጥናቱ ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ በጥናቱ የተገኙ መረጃዎች የሚያመለክቱት ተማሪዎች በአማርኛ የቀረቡት ጽሁፍችን የማንበብ ተነሳሽነት እና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል ፡፡ ለተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ዝቅተኛ መሆን ከሚጠቀሱት ውስጥ የንባብ ትምህርት አሰጣጥና የመማሪያ መጽሐፍት ይጠቀሳል ፡፡ ከመጠይቁ በተገኘው መረጃም ንባብን ከማስተማሩና ከመማሪያ መጽሐፍት አኳያ ችግሮች እንዳለ ነው ፡፡ በክፍል ውስጥ የሚሰጠው የንባብ ትምህርት ተማሪዎችን እደማያሳትፍ ማለትም አብዚኛውን ጊዜ በመምህራን የሚከናወን በመሆኑ ተማሪዎች በቂ ልምምዴ አለማድረጋቸውን ይገልጻሉ፡፡ የመማሪያ መጽሐፍም በበቂ ሁኔታ ለተማሪዎቹ አለመድረሱ እንደዚሁም የተማሪዎችም የንባብ ተነሳሽነት ከማጎልበት አንጻር ያለው አስተዋጽኦ አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል ፡፡ በመጨረሻም በዚህ ጥናት ውስጥ የተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማዳበር ያግዛለluተብለው በአጥኚዋ የቀረቡ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡

Description

Keywords

የማንበብ ተነሳሽነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው

Citation