የሰዋስው ይዘቶችን በማስተማር የኣሳታፈ ማስተማሪያ ዘዴ ኣተገባበር ፍተሻ፤በመቀሌ ከተማ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (በተመረጡ ዘጠነኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (በተመረጡ ዘጠነኛ ክፍሎች ናሙናነት)
No Thumbnail Available
Date
2004-05
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ
Abstract
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በመቀሌ ከተማ በሚገኙ ሐወልቲና ዓይደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዘጠነኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ መምህራን የሰዋስው ይዘቶችን ሲያስተምሩ አሳታፈ የማስተማሪያ ዘዴን አተገባበር መፈተሽ ነው፡፡መቀሌ ከተማ በዓላማ ተኮር የናሙና ዘዴ ሲመረጥ በከተማው ከሚገኙ ሶስት የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁለት እና ከሁለቱ ትምህረት ቤቶች ደግሞ አራት የ9ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ መምህራን በዕጣ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በናሙናነት የተመረጡ መምህራን ከሚገቡባቸዉ የ9ኛ ክፍል ምድቦች በዕጣ ናሙና ሰባት ምድቦች ለክፍል ምልከታ ተወስደዋል፡፡እንዲሁም ከሰባቱ ምድቦች በብድግ ብድግ ናሙና ዘዴ የተመረጡ 77 ተማሪዎች የፅሁፍ መጠይቅ እንዲሞሉ ተደርገዋል፡፡ከነዚህ መረጃ ሰጪዎችም በክፍል ውስጥ ምልከታ፤በቪድዮ ቀረፃ፤ በፅሁፍና፤ በቃል መጠይቅ፤ መረጃዎችን ተሰብስበዋል፡፡የተሰበሰቡት መረጃዎች ዓይነታዊና መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ተተንትጎዋል፡፡ በተጠቀሱት መሳሪያዎች በመታገዝ የተሰበሰቡት መረጃዎች ተጠናክረዉ ባስገኙት ዉጤት መሰረት በሁለቱ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን አሳታፈ የማስተማሪያ ዘዴ አዘውትረው ይጠቀማሉ፡፡ ይህም መምህራኑ የቡድን ዉይይት ፤ ጥያቄና መልስ እና የክፍል ስራ የማስተማሪያ ዘዴዎች በተደጋጋሚ ይተገብራሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪያ መምህራኑ በመማር ማስተማር ሂደት የዕለቱን ትምህርት ርዕስ በማስተዋወቅ፤ቅድመ ትምህርት ጥያቄዎችን በማቅረብ ተማሪዎችን በማበረታታት ወዘተ. ሚናቸው የተጫወቱ ሲሆን ተማሪዎች ድግሞ ንቁ ተሳታፈ በመሆን ሚናቸዉ የተጫወቱ ሲሆን ተማሪዎች ድግሞ ንቁ ተሳታፈ በመሆን ሚናቸዉን የተጫዉተዋል፡፡ ይሁን እንጂ መምህራን የዕለቱን ትምህርት ዓላማ አለማስተዋወቅ፤ እያንዳንዱ የቡዱን እባል በሰራዉ ላይ ያለውን ድርሻ እለማሳወቅ፤ የቡድን ዉይይት የሚፈጀዉን ጊዜ ቀድሞ አለማሳወቅ፤ የቡድን ዉይይት በተወሰኑ የተማሪዎች ብቻ መሰራት ፤የማይሳተፈ ተማሪዎች እንዲሞክሩ አለማድረግ፤መምህራን ዘዴዉን በተመለከተ ስልጠና አለመውሰድ ፤ የተማሪዎች ቁጥር መብዛት አና የመማሪያ ክፍሎቸ አቀማመጥ አመቺ አለመሆን የሚሉት ዘዴውን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የሚፀባረቁ ችግሮች ሆነዉ ከተገኙት መ መረጃዎች መረዳት ተችሏል፡፡ እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ አሳታፈ የማስተማያ ዘዴ በትምህርት ቤቶቹ አሁን ካለበት በተሻለ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የመፍትሄ ሀሳቦችን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡