በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎች የማንበብ ብልሃቶች አጠቃቀም ፣ የማንበብ ተነሳሽነት እና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ (በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2023-09

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋነኛ አላማ የማንበብ ብልሀቶች ፣ የማንበብ ተነሳሽነት እና አንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶን መፈተሸ ነው፡፡ጥናቱ መጠናዊ የምርምርና ተዛምዷዊ የንድፍ አይነት ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህ ጥናት የተካሔደው በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ በወረኢሉ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ ካሉት አራት የክፍል ደረጃዎች መካከል የዘጠነኛ ክፍል አመች የንሞና መረጣ ሂደት ተመርጧል፡፡ በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ በሚገኙ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ውስጥ በቀላል ዕጣ ንሞና ዘዴ ወንድ 65 ሴት 75 በድምሩ 140 ተማሪዎች በተጠኝነት ተወስደዋል፡፡ መረጃ በፅሑፍ መጠይቅና በፈተና ተሰብስቧል፡፡ መረጃዎች አማካይ ውጤት፣ መደበኛ ልይይት፣ በፒርሰን ተዛምዶ መወሰኛ ቀመር እንድሁም በህብረ ድኅረ ፒርሰን ትንተና ስሌት ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤትም እንደሚያሳየው የተማሪዎች የማንበብ ብልሀቶች ከአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል((r=0.621, p<0.05) አወንታዊ ተዛምዶ እንዳለው እና ተዛምዶውም ጉልህነቱ (p=0.000) መሆኑ ታውቋል፡፡ይህምየተማሪዎች የማንበብ ብልሀቶች አጠቃቀም ከፍ ሲል የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን በተመሳሳይ ከፍ እንደሚል አመላካች ነው፡፡ የተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል (r2=0.461,p<0.05) አዎንታዊ ተዛምዶ እንዳለውና ጉልህነቱም (p=0.000) ሆኖ ተረጋግጧል፡፡ ይህ ማለት የተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት ከፍ ሲል የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውም በተመሳሳይ አቅጣጫ እንደሚጨምር የሚያሳይ ነው፡፡ በተጨማሪም የተማሪዎች የማንበብ ብልሀቶችና የማንበብ ተነሳሽነት የአንብቦ የመረዳት ችሎታን በመተንበይ ረገድ ያላቸውን ድርሻ የፈተሸ ነበር፡፡ ውጤቱም ቀጥተኛና አወንታዊ ነው። ሁለቱ ትንበያ ተለውጦዎች አንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው የሚጠቁም ነው፡፡ ከሁለቱ ተላውጦዎች በበለጠ የማንበብ ብልሃት የመተንበይ አቅም እንዳለው ትንተናው አሳይቷል። ከመረጃው ወይም ከግኝቱ በመነሳት የተማሪዎች የማንበብ ብልሀቶች አጠቃቀምን ማሳደግ እና የማንበብ ተነሳሽነታቸውን ከፍ ማድረግ ለአንብቦ መረዳት ችሎታቸው መዳበር አስተዋፅዖ ያደርጋሉ ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ በማስከተልም ሌሎች አጥኝዎች በርዕሱ ዙሪያ ተጨማሪ ጥናቶችን ቢያካሂዱ የሚል አስተያየት ተሰንዝሯል፡፡

Description

Keywords

የማንበብ ብልሀቶች ፣ አንብቦ መረዳት ችሎታ

Citation