ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በኩስሜ ብሔረሰብ

No Thumbnail Available

Date

2006-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

ይህ ጥናት ‹‹ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት በኩሰሜ ብሔረሰብ›› በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡በጥናቱ የግጭት አፈታት ገፅታና የብሔረሰቡ አባላት እርስ በእርስና ከአጎራባች ብሔረሰቦች ጋር የሚያጋጥሟቸውን ግጭቶች ተጋጪዎቹ ወደ ሀገረሰባዊው የፍትህ ተቋም እንዲያመጡ የሚያደርጋቸው ምክንያቶችና የባህላዊ የግጭት መፍቻ ሥርአቱን አጠቃላይ ሂደት ለማወቅ ይቻል ዘንድ በተለያየ መልኩ ከተለያዩ የብሔረሰቡ ክፍሎች መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በመረጃ መሰብሰቢያ መንገድነት ጥቅም ላይ የዋሉት ቃለ መጠይቅ ፣ የቡድን ውይይትና ምልከታ ናቸው፡፡ የተገኘው መረጃ በገላጭ ተንታኝ (Descriptive Analysis) ስልት ተተንትኗል፡፡ በዚህም ብሔረሰቡ ከቀላል እስከ ከባድ ወንጀሎች መፍትሄ ለመስጠት የሚሄድበትን መንገድ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በጥናቱ በኩስሜ ብሔረሰብ ዋነኛ የግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችም ተለይተዋል፡፡ከግጭቶቹም ዋና ዋና የሚባሉት ማለትም ድንበር መግፋት ፣ የቤተሰብ ጠብ ፣ ወንጀልና የቡድን ጠብ ተመርጠው ባህላዊው የእርቅ ስርአት እንዴት እንደሚፈታቸው ታይቷል፡፡ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ስርዓቱ ራሱን የቻለ የስልጣን ተዋረድ እንዳለውም በጥናቱ ታይቷል፡፡ በብሔረሰቡ የግጭት አፈታት ሥርዓት ውስጥ ሴቶች ሚና ባይኖራቸውም ከሰውም ሆነ ተከሰው ሲቀርቡ ከመሸንጎያው /ከሞራው/ ራቅ ብለው ግን ጉዳያቸውን የማስረዳት መብት አላቸው፡፡ የባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቱ ከመደበኛ ፍርድ ቤት ጋር ተቀራርቦ የሚሰራ ነው፡፡ በተለይ የሐሰት አጣሪ በሚል በብሔረሰቡ የተቋቋመው 16 አባላት ያሉት ኮሚቴ መደበኛ ፍርድ ቤት በተሳሳተ መልኩ ውሳኔዎችን እንዳይወስን መረጃን በሚገባ በመሰብሰብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በኩሰሜ ብሔረሰብ ዘንድ በተለይ ለግድያና ለብሔር ግጭት እርድ የእርቅ ሥነ ሥርዓት የመጨረሻው ስርዓት ነው፡፡ሌሎቹ ጉዳዮች ግን በካሳ ክፍያና በገንዘብ ቅጣት ብቻ እንደሚጠናቀቁ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ባህላዊ የግጭት መፍቻ ሥርዓቱ በትክክል ይፈርዳል ተብሎ ከመታመኑም በላይ ፍርዱን የማይቀበሉት ከብሔረሰቡ ስለሚገለሉ ተቀባይነቱ የጎላ ነው፡፡

Description

Keywords

የግጭት አፈታት ሥርዓት

Citation