ስግ ሥርዓት (cloze procedure)በአማርኞ ትምህርት አቀራረብ ዉስጥ የአንብቦ መረዳትን ብሎም አጠቃላይ የቋንቋ ችሎታን ለማበልፀግ ያለዉ ሚና

No Thumbnail Available

Date

1991-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት የስግ ሥርዓት የሚታገዝ የንባብ ማስተማሪያ ዘዴ የአማርኞ ቋንቋ ችሎታ ላይ ምን ያህል ማስከተል ይችላል? የሚለዉን የጥናቱ አብይ ጥያቄና ከዚህ ጋራ የተያያዙትን ንዑሳን ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚሞክር ሲሆን፤ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመሻት አጥኚዉ የተከተለዉ ዋና የአጠናን መንገድ የሙከራ ምርምር (Experimental Research)ነዉ፡፡ የሙከራ ምርምሩ ከተጠናቀቀ ቡኃላም ከዚህ የተገኘዉን ዉጤት ለማጠናከር ለተጠኚ ተማሪዎችና ለታዛቢ መምህራን የጽሑፍ መጠይቅ በማሰራጨት መረጃዎችን በማሰባሰብ የድህረ ሙከራ ተደርጓል፡፡ በሙከራ ምርምሩ ዉስጥ የሁለት ቡድን ቅድመና ድህረ ፈተና ንድፍ (two group pre-test post-test design) ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፤አጥኚዉ ስታትስትካዊ የናሙና መረጣን መርህ በመጠበቅ አንድ የቁጥጥርና አንድ የሙከራ ምድብ በማደራጀት ፤ በስግ ሥርዓት በሚጻገዝ የንባብ ማስተማሪያ ዘዴ የሙከራ ምድቡን ማስተማር በአንብቦ መረዳትም ሆነ በአጠቃላይ የቋንቋ ችሎታ ላይ ልዩነት አያስከትልም የሚል ባዶ መላምት (H0) እና የዚህ ተቃራኒ መላምት (Hl) ይዞ ተነሳ፡፡ ከመነሻ የቁጥጥርና የሙከራ ምድቡ የችሎታ ልዩነት የሌላቸዉ መሆኑን ለማረጋገጥ ቅድመ -ፈተና (pre-test) ተሰጥቶ ሁለቱ ምድቦች በአንብቦ መረዳት ንዑስ ክፍልና በአጣቃላይ ፈተና ያስመዘገቡት ዉጤት በ"t"-ሙከራ (t-test) ሲሰላ፤ በዚሁ ቅደም ተከተል 0.73 እና 0.06 ሆኖ በመገኘቱ ሁለቱ በስሌት የተገኙየ"t" -ዋጋዎች በP < 0.05 የጉልህነት መጠን በ"t"- ሰንጠረዥ ላይ ተመዝግቦ ከሚገኘዉ ከ1.96 ያነሱ በመሆናቸዉ ከመነሻ በሁለቱ ምድቦች መካከል በአንብቦ መረዳትነና በአጠቃላይ የቋንቋ ችሎታ( ስታቲስቲካዊ ተቀባይነት ያለዉ) የጎላ ልዩነት እንዴለለዉ ታዉቋል፡፡ በመቀጠል ለስድስት ሳምንታት በክፍል ደረጃ የትምህርት ይዘት ላይ በመመርኮዝ ለቁጥጥር ምድቡ በተለመደዉ የአማርኞ ትምህርት አቀራረብ መንገድ ትምህርት ሲሰጥ ፤ ለሙከራ ምድቡ በሳምንት ዉስጥ ካሉት ሶስት ክፍለ ጊዚያት በመገመሪያዉና በመጨዉ በአጥኚዉ አማካይነት በስግ ሥርዓት የሚቀርብ የንባብ ትምህርትና በቀሪዉ በመደበኛዉ መምህር አማካኝነት በስግ ሥርዓት ያልተሸፈኑ ይዘቶች በተለመደዉ መንገድ ቀርበዋል፡፡ የሙከራ ጊዜ እነደተጠናቀቀም ድህረ- ፈተና (post-test) ተሰጥቶ ሁለቱ ምድቦች በአንብቦ መረዳት ንዑስ ክፍልና በአጠቃላይ ፈተና ያስመዘገቡት ዉጤት በ"t " - ሙከራ ሲሰላ የ''t'' -ዋጋዎች በዚሁ ቅደም ተከተለል 5.23 እና, 5.47 ሆነዉ በመገኘታቸዉ፤ እነኝህ የ"t " ዋጋዎች በP< 0.05 የጉልህነት መጠን በ"t " ሰንጠረዥ ላይ ከተገኘዉ ከ l. 96 የበለጡ ሆነዋል፡፡ይህም የሙከራ ምድቡ የአንብቦ መረዳት ሆነ በአጠቃይ የቋንቋ ችሎታ ከቁጥጥር ምድቡ ልቆ መገኘቱን የሚያመለክት በመሆኑ አጥኚዉ ይዞት የተነሳዉ ባዶ መላምት (Ho) ማስወገድ ችሏል፡፡ በድህረ ጥናት ለተጠኚ ተማሪዎችና ተግባራዊ የተደረገዉን የንባብ ትምህርት ከ2 እስከ 3 ክፍለ ጊዜ በታዛቢነት በመገኘት ለተመለከቱ መምህራን የጹሑፍ መጠይቆች በማሰራጨት መረጃዎች የተሰበሰቡ ሲሆን፤ ተጠኚ ተማሪዎቹም ሆኑ ታዛቢ መምህራኑ የማስተማሪያ ዘዴዉ የአንብቦ መረዳትንም ሆነ አጠቃላይ የቋንቋ እሎታን ሊያዳብር መቻሉን የሚያመለክት አስተያት እንደሰጡ ከመረጃዎቹ ማወቅ ተችሏል፡፡ይህ ዉጤት ቀደም ሲል ከተገለፀዉ የሙከራ ምርምር ዉጤት ጋር የሚጣጣም በመሆ የጥናቱ ጥቅል ዉጤት በስግ ሥርዓት የሚታገዝ የንባብ ትምህርት የአንብቦ መረዳትን ብሎም አጠቃላይ የአማርኞ ቋንቋ ችሎታን የማዳበር ብቃት እንዳለዉ አመልክቷል፡፡

Description

Keywords

የስግ ሥርዓት (cloze procedure)

Citation