የግለመር የመማር ዘዴ አማርኛ ቋንቋን አንብቦ ከመረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ መፈተሽ፤ በሀዲያ ዞን በምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ጃርሶ ኦንጆጆ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት
dc.contributor.advisor | ግርማ መንግስቱ ዶ/ር | |
dc.contributor.author | አበበ ታሪኩ | |
dc.date.accessioned | 2024-09-30T11:00:14Z | |
dc.date.available | 2024-09-30T11:00:14Z | |
dc.date.issued | 2024-08 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት ዋና ተግባር በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የግለ መር መማር ዘዴ አንብቦ ከመረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ ሲሆን ፣ ይህንን አላማ ከዳር ለማድረስ ጥናቱ ተዛምዷዊ የምርምር ንድፍን ተከትሏል ። በሀዲያ ዞን በምዕራብ በደዋቾ ወረዳ ጆርሶ ኦንጆጆ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአመቺ የናሙና አመራረጥ ዘዴ ተመርጧል ። የጥናቱ ተሳታፊዎች የጆርሶ ኦንጆጆ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2015 ዓ.ም የሚማሩ በአመቺ ናሙና የተመረጡ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ፣ጥናቱ የተከተለው ቅንጅታዊ የምርምር ዘዴን ነው በፅሁፍ መጠይቅ እና በአንብቦ መረዳት ፈተና ለጥናቱ አሰፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ተሰብሰበውና ተጠናቅረው በመጠናዊ የምርምር ዘዴ በሆነው በድብልቅ የአተናተን ስልት ተተንትኖ ቀርቧል። ትንተናውን ለማካሄድ SPSS Software ተግባራዊ ሆኖዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት ተማሪዎች ንዑሳን የግለ መር መማር ዘዴዎችን ግብ ማስቀመጥ፣የመማር ፍላጎትና የመማር ዘዴ እንደሚጠቀሙ አመልክቷዋል ። በግለመር መማር ዘዴና አንብቦ በመረዳት ችሎታ መካከል አዎንታዊ የሆነ ግኑኝነት እንዳለም የጥናቱ ውጤት አማልክቷል ። ሌላው ግለ መር የመማር ዘዴዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታን የማሳደግ ድርሻቸው ከፍተኛ እንደሆነም የጥናቱ ውጤት ያመለክታል። በመጨረሻም በዚህ ጥናት ባልተጨማሩ በሌሎች የግለመር የመማር ዘዴ ንዑሳን ክፍሎች የተለያዩ ጥናት ቢያካሄዱ የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማሳደግ ያለው አስተዋጾ የተሻለ ውጤት እንደሚያመጡ የጥናቱ ውጤት አሳይቷል፡፡ | |
dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3482 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ | |
dc.title | የግለመር የመማር ዘዴ አማርኛ ቋንቋን አንብቦ ከመረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ መፈተሽ፤ በሀዲያ ዞን በምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ጃርሶ ኦንጆጆ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት | |
dc.type | Thesis |