የግለመር የመማር ዘዴ አማርኛ ቋንቋን አንብቦ ከመረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ መፈተሽ፤ በሀዲያ ዞን በምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ጃርሶ ኦንጆጆ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

No Thumbnail Available

Date

2024-08

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

ይህ ጥናት ዋና ተግባር በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የግለ መር መማር ዘዴ አንብቦ ከመረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ ሲሆን ፣ ይህንን አላማ ከዳር ለማድረስ ጥናቱ ተዛምዷዊ የምርምር ንድፍን ተከትሏል ። በሀዲያ ዞን በምዕራብ በደዋቾ ወረዳ ጆርሶ ኦንጆጆ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአመቺ የናሙና አመራረጥ ዘዴ ተመርጧል ። የጥናቱ ተሳታፊዎች የጆርሶ ኦንጆጆ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2015 ዓ.ም የሚማሩ በአመቺ ናሙና የተመረጡ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ፣ጥናቱ የተከተለው ቅንጅታዊ የምርምር ዘዴን ነው በፅሁፍ መጠይቅ እና በአንብቦ መረዳት ፈተና ለጥናቱ አሰፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ተሰብሰበውና ተጠናቅረው በመጠናዊ የምርምር ዘዴ በሆነው በድብልቅ የአተናተን ስልት ተተንትኖ ቀርቧል። ትንተናውን ለማካሄድ SPSS Software ተግባራዊ ሆኖዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት ተማሪዎች ንዑሳን የግለ መር መማር ዘዴዎችን ግብ ማስቀመጥ፣የመማር ፍላጎትና የመማር ዘዴ እንደሚጠቀሙ አመልክቷዋል ። በግለመር መማር ዘዴና አንብቦ በመረዳት ችሎታ መካከል አዎንታዊ የሆነ ግኑኝነት እንዳለም የጥናቱ ውጤት አማልክቷል ። ሌላው ግለ መር የመማር ዘዴዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታን የማሳደግ ድርሻቸው ከፍተኛ እንደሆነም የጥናቱ ውጤት ያመለክታል። በመጨረሻም በዚህ ጥናት ባልተጨማሩ በሌሎች የግለመር የመማር ዘዴ ንዑሳን ክፍሎች የተለያዩ ጥናት ቢያካሄዱ የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማሳደግ ያለው አስተዋጾ የተሻለ ውጤት እንደሚያመጡ የጥናቱ ውጤት አሳይቷል፡፡

Description

Keywords

Citation