የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ጽሕፈት ለማስተማር የሚጠቀሟቸው የማስተማር ዘዴዎች ንጽጽር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአየር ጤና እና በክሩዝ 2ኛ ደረረጃ ት/ቤቶች
dc.contributor.advisor | ዶ/ር ጌታቸው አዱኛ | |
dc.contributor.author | እጅጋየሁ ተሾመ | |
dc.date.accessioned | 2024-09-30T10:58:50Z | |
dc.date.available | 2024-09-30T10:58:50Z | |
dc.date.issued | 2024-09 | |
dc.description.abstract | በመምህራን ውጤት መካከል ጉልህ ልዩነት መኖሩን እንረዳለን፡፡ በዚህም አማካኝ ስሌት ሆነ የቴ-ስሌት ውጤት በመንግስት ት/ቤት ከሚያስተምሩ መምህራን ይልቅ በግል ት/ቤት የሚያስተምሩ መምህራን ውጤት በልጦ በመገኘቱ የግል ት/ቤት መምህራን የተሻለ አተገባበር ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የመምህራን እቅድ አዘገጃጀት ለተማሪዎች የግል መመሪያ መስጠት፤ አፋጣኝ ምጋቤ ምላሽ አሰጣጥ፤ ማስተማሪያ ዘዴ ወዘተ..መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ ከተለዩት ችግሮች በመነሳት መመህራን ጽህፈት ለማስተማር ዘዴ ከማስተማር ሲያቅዱ በግል ማስተማሪያዎች እንደሚጠቀሙባቸው፤ የጽህፈት ችሎታን የሚያግዙ የተለያዩ መልመጃዎችን መስጠት እንደሚገባ ወዘተ.. የሚሉ አስተያየቶችም በጥናቱየዚህ ጥናት ዋና አላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የግልና የመንግስት ት/ቤቶች የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለ ጊዜ በተማሪዎች የጽህፈት ትምህርት ወቅት የትኞቹ መምህራን የማስተማር ዘዴ ጥሩ አተገባበር እንዳላቸው በመፈተሸና በመለየት ንጽጽራዊ ጥናት ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ጥናት የተመረጡት በ 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር በመንግስትና በግል ት/ቤት የ9ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ የሚያስተምተሩ መምህራን ናቸው፡፡ በመስተዳደሩ ከሚገኙት መምህራን መካከል በዚህ ጥናት አንድ የመንግስት እና አንድ የግል ት/ቤት ተመርጠዋል፡፡ ጥናቱ በሚካሄድባቸው ት/ቤቶች በተመረጠው የክፍል ደረጃ ከሚያስተምሩ መምህራን ከመንግስት ትምህርት ቤቶች አራት ከግል ት/ቤት አራት በድምሩ ስምንት መምህራን እንዲሁም ከግል ት/ቤቶች 40 ከመንግስት ት/ቤቶች 40 በድምሩ ሰማኒያ ተማሪዎች በክፍል ምልከታ እና የጽሁፍ መጠይቅ በመረጃ ሰጪነት ተካተዋል፡፡ ጥናቱ የተከተለው የአጠናን ስልት አይነታዊና እና መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በገለጻ ስልት ትንታኔ በመስጠት ነው፡፡ የክፍል ውስጥ ምልከታ እና የጽሁፍ መጠይቅ መረጃ የተሰበሰበባቸው መሳሪያዎች ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ከክፍል ምልከታ እና ከተማሪዎች የጽሁፍ መጠይቅ የተገኘው ውጤት በባለሙያ በመታገዝ በSPSS ተሰርቷል፡፡ በመሆኑም ምልከታ የተገኘ ውጤት በመንግስት ት/ቤት 3.797 ፤ በግል ት/ቤት 4.395 አማካኝ ውጤት ያለ ያስመዘገቡ የተማሪዎች የግምገማ ውጤት ደግሞ የመንግስት ት/ቤቶ 3.809፤ የግል ት/ቤት 4.25 አማካኝ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ በመምህራን መካከል ጽሕፈት በማስተማር ዘዴ የጎላ ልዩነት መኖርና አለመኖሩን ለማረጋገጥ በተደረገው ስሌት በክፍል ውስጥ ምልከታ የቴ- ስሌት ዋጋ 3-435 ሲሆን የቴ- የቴ- ጣሪያ ዋጋ ደግሞ 2-542 ነው፡፡ የተማሪዎች ግምገማ የቴ-ስሌት ዋጋ 4-320 ሲሆን የቴ-ጣቲያ ዋጋ ደግሞ 2-352 ነው፡፡ ከተገኘው ውጤት መረጃ በመነሳት የቲ - ስሌት ዋጋ ከቲ ጣሪያ ከበለጠ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ | |
dc.identifier.uri | https://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3479 | |
dc.language.iso | am | |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ | |
dc.title | የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ጽሕፈት ለማስተማር የሚጠቀሟቸው የማስተማር ዘዴዎች ንጽጽር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአየር ጤና እና በክሩዝ 2ኛ ደረረጃ ት/ቤቶች | |
dc.type | Thesis |