በቀይት ንዑስ ወረዳ የሚከወኑ ሀገረሰባዊ እምነቶች

dc.contributor.advisorሀሰን, አህመድ
dc.contributor.authorታደሰ, ፀዳለ
dc.date.accessioned2018-06-14T10:25:24Z
dc.date.accessioned2023-11-09T04:06:42Z
dc.date.available2018-06-14T10:25:24Z
dc.date.available2023-11-09T04:06:42Z
dc.date.issued2007-01
dc.description.abstractይህ ጥናት ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በባሶና ወራና ወረዳ ስር በሚገኘው የቀይት ንዑስ ወረዳ ውስጥ በሚከወኑ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች ላይ ነው፡፡ የጥናት ወረቀቱ ርዕስ ‘በቀይት ንዕስ ወረዳ የሚከወኑ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች’ የሚል ሲሆን በስሩ አምስት ሀገረሰባዊ ዕምነቶች ተዳሰዋል፡፡ እነዚህም ዕምነቶች ጫት መቀቀል፣ ጭዳ፣ አድባር፣ ቦረንትቻ እና አቴቴ/ፈጫሳ ሲሰኙ መነሻቸው፣ ፋይዳቸው፣ ሀይማኖታዊ ትስስራቸው፣ ከበራቸው እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ለዕምነቶቹ ያለው አመለካከት በዚህ የጥናት ወረቀት ውስጥ ተዳሷል፡፡ ዋና አላማውም የእነዚህን ዕምነቶች መነሻ፣ ይዘትና አከባበር ማሳየት ነው፡፡ ለጥናቱ በግብዐትነት ያገለገሉት ከቀዳማይና ካልኣይ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ሲሆኑ በመረጃ መሰብሰቢያነት ደግሞ በዋናነት አገልግሎት ላይ የዋሉት ምልከታና ቃለምልልስ እንዲሁም የቡድን ውይይት ናቸው፡፡ በእነዚህ ሶስት ዘዴዎች ከ23 የመረጃ ሰጪዎች መረጃ የተሰበሰበ ሲሆን መረጃ ሰጪዎቹ የተመረጡት ባሳዩት ፈቃደኝነት ነው፡፡ ከመስክ የተሰበሰቡት መረጃዎች ደግሞ ገላጭ በሆነ የትንተና ዘዴ ተተንትነው እና በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች ተከፍለው ቀርበዋል፡፡ መረጃዎቹ የተተነተኑት በCathrine Bell የከበራ አይነቶችን እና በPascal Boyer & Pierre Liénard የከበራ መገለጫዎች ፅንሰ ሀሳቦች ተቃኝተው ነው፡፡ በተገኘው መረጃ መሰረት በተጠኚው አካባቢ የተጠቀሱት አምስት ሀገረሰባዊ ዕምነቶችen_US
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/889
dc.language.isoamen_US
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲen_US
dc.subjectየሚከወኑ ሀገረሰባዊ እምነቶችen_US
dc.titleበቀይት ንዑስ ወረዳ የሚከወኑ ሀገረሰባዊ እምነቶችen_US
dc.typeThesisen_US

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ፀዳለ ታደሰ.pdf
Size:
1.06 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Plain Text
Description: