የፅህፈት ችልታ ንፅፅራዊ ጥናት በሀድይኛና በስልጥኛ ቋንቋ አፋቸውን ፈትተው፣አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ በመማር ወደዘጠነኛ ክፍል በገቡ ተማሪዎች ተተኳሪነት

dc.contributor.advisorግርማ ገብሬ(ድ/ር)
dc.contributor.authorፀጋነሽ አየለ አያኖ
dc.date.accessioned2024-11-07T08:48:35Z
dc.date.available2024-11-07T08:48:35Z
dc.date.issued2023-08
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዋና ዓሊማ በሀድይኛ እና በስልጥኛ ቋንቋ አፊቸውን ፈትተው አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ ተምረው ወደ ዘጠነኛ ክፍል የገቡ ተማሪዎች የፅህፈት ችልታ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና የትኞቹ የተሻለ የፅህፈት ችሎታ እንዳላቸው በንፅፅር መመርመር ነው፡፡ ጥናቱም በሁለት ቡድኖች መካከል ያለውን የመጻፍ ችሎታ በንጽጽር ስለሚፈትሽ አወዳዳሪ ንድፍ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፣መጠናዊና አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ (Mixed approach) ነው፡፡ ይህ ጥናት የተካሄደው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን በአንሌሞ ወረዳ ከሚገኙ አምስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአጫሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም በ9ኛ ክፍል በመማር ያለ ተማሪዎች በዚህ ጥናት ተሳትፈዋል፡፡ የጥናቱ መረጃዎችም በመጻፍ ችሎታ ፈተናና ለተማሪዎች ከተሰራጨ የጽሁፍ መጠይቅ የተሰበሰቡ ሲሆን፣የትንተናውም ውጤት በማወዳደር ስልት ተብራርቷል፡፡ የጥናቱም ውጤት በሀድይኛ እና በስልጥኛ ቋንቋ አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች የተለያየ ችሎታ ያላቸው መሆኑን አመልክቷል፡፡ ከሆሄያትና ቃላት አጠቃቀም አኳያ የስልጥኛ ቋንቋ አፍ-ፈት ተማሪዎች የተሻለ ሲሆኑ፣ከአረፈተ ነገር አወቃቀር እና ከአንቀጽ አደረጃጀት አኳያ በሀድይኛ ቋንቋ አፈ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች ተሽለው መገኘታቸውን የጥናቱ ውጤት አረጋግጧሌ፡፡ ከስርዓተ ነጥቦች አጠቃቀም አኳያ በሀድይኛ እና በስልጥኛ ቋንቋ አፍ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች ተመሳሳይ ችሎታ ያላቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡ እንዱሁም ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ሇመጻፌ ያሊቸው ፌሊጎትና ችልታቸው የተቀራረበ ሲሆን፣ መምህራን ተማሪዎችን በአማርኛ ድርሰት በመጻፍ ሂደት ለማብቃት ያላቸው ሚና መካከለኛ መሆኑ ተረጋግጧሌ፡፡ በተጨማሪ በሀድይኛ እና በስልጥኛ ቋንቋ አፍ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች ለመጻፍ ያላቸው ችሎታ ደካማ መሆኑንም የጥናቱ ውጤት አመልክቷል፡፡ ስለሆነም የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በመማሪያ ክፍል ውስጥና ከመማሪያ ክፍል ውስጥ በሚሰሩት ተግባራ የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ ማሻሻል ላይ ልያተኩሩ ይገባል
dc.identifier.urihttps://etd.aau.edu.et/handle/123456789/3598
dc.language.isoam
dc.publisherAddis Ababa University
dc.titleየፅህፈት ችልታ ንፅፅራዊ ጥናት በሀድይኛና በስልጥኛ ቋንቋ አፋቸውን ፈትተው፣አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ በመማር ወደዘጠነኛ ክፍል በገቡ ተማሪዎች ተተኳሪነት
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ፀጋነሽ አየለ አያኖ.pdf
Size:
3.69 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: