የዲዚ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓተ ክዋኔ
dc.contributor.advisor | አስፋው, ዘሪሁን | |
dc.contributor.author | ወ/መስቀል, ደስታ | |
dc.date.accessioned | 2018-06-14T09:44:56Z | |
dc.date.accessioned | 2023-11-09T04:06:40Z | |
dc.date.available | 2018-06-14T09:44:56Z | |
dc.date.available | 2023-11-09T04:06:40Z | |
dc.date.issued | 2006-06 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ የዲዚ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓተ ክዋኔ በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ ጥናቱ የሚያተኩረው በዲዚ ብሄረሰብ የለቅሶ ስነ ስርዓት ላይ ነው፡፡ የጥናቱ አላማ የዲዚ ብሄረሰብ የለቅሶ ስርዓተ ክዋኔ ላይ ገላጭ ትንተና በማድረግ ስርዓቱን ማሳየት ነው፡፡ አላማውን ለማሳካት በዋናነት ምልከታ፣ ቃለመጠይቅ፣ የተተኳሪ ቡድን ውይይት ተካሂድዋል፡፡ በሶስት ተፈጥሯዊ የለቅሶ መቼቶች ላይ በመገኘት መረጃው ተሰብስቧል፡፡ በተገኘው መረጃ መሰረት የዲዚ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓተ በአራት ተከፍሎ እንደሚከወን ታውቋል፡፡ በዲዚ ብሄረሰብ በእድሜ፣ በጾታና በማህበራዊ ደረጃ አንፃር የተለያዩ የለቅሶ ክዋኔዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከማህበራዊ ደረጃ አንጻር ስንመለከተው ሟች የጎሳ መሪ፣ የሐገር ሽማግሌ፣ የእምነት መሪ ወዘተ ከሆኑ የሚከወንላቸው ስርዓት የሟችን ተግባርና ማንነት የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ የለቅሶ ስርዓተ ክዋኔውን ከዕድሜ እንዲሁም ከጾታ አንጻር ስንመለከተው የሴት እና የወንድ በቀብር ቦታ አቆፋፈርን እና የቀብር አቅጣጫን እንደሚወስኑ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ የጥናቱ ግኝት የለቅሶ ስርዓቱ የባላባት ስርዓት ሽግግርን የሚያጠናክሩበት እና የሚገነቡበት፣ ማህበራዊ አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት እንዲሁም የማህበረሰቡን ታሪክ፣ እምነትና አመለካከት የሚገልጹበት መንገድ መሆኑን ያሳያል፡፡ በክዋኔ ውስጥም የሚተላለፉ መልዕክቶች እና ትርጓሜዎች በጥናቱ ውስጥ ተካትተዋል፡፡ | en_US |
dc.identifier.uri | http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/877 | |
dc.language.iso | am | en_US |
dc.publisher | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ | en_US |
dc.subject | ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓተ | en_US |
dc.title | የዲዚ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓተ ክዋኔ | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |