በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ድርሰዕት ውስጥ የሚፈጽሙ ወና ወና የስህተት አይነቶችና ዋና ወና የስህተት ምንጮች ትንተና

No Thumbnail Available

Date

1986-05

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ወናዐላማ በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ድርሰዕት ውስጥ የሚፈጸሙ ዋና ወና የስህተት ዓይነቶችን በስተት ትንተና ዘዴ በመለየት መተንተንና የስተት ምንጮችን ማብራራት ነበር፡፡ ለጥናቱ ዓላማ በናሙናነት የተመረጡት አምስት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 390(በት/ቤቶቹ ዘጠነኛ ክፍል የሚማሩ 1559 ተማሪዎች ውስጥ የተመረጡ ተማሪዎች ነበሩ፡፡የጥናቱን ዐላማ ልማሳካትና መረጃዎችን ለማጠናክር ተማሪዎቸ4 ድርሰት የጻፉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማሰበሰብም ተማሪዎችና መምህራን መጠይቅ ሞልተዋል ፡፡ ድርሰቶችን በማረም የተገኙ መረጃዎችን በመለየትና በመተንተን የተገኝው ውጢት በድርሰዕት ውስጥ ከተፈጽሙ የተለያዪ ስህተቶች ከፍተኛ የስህተት መጠንና ድግግሞሽ ያላቸው ዋና ዋና የስህተት አይነቶች አምስት መሆናችውና ስተቶችም አጠቃላይ ብዛት 9393 መሆኑን አመልክቷል፡፡ከአጠቃላይ የስህተት መጠን ውስጥ 35 በመቶ (3276) የቋንቋ አጠቃቀም 30 በመቶ (2676) የቋንቋ አወቃቀር 27 በመቶ (2516) የሥርዓተ ነጥብ አጠቃቀም 6 በመቶ (676) ባይነት ለመለየት ያልቻሉና 3 በመቶ(249) የጽንሰ-ሀሳብ የስህተት ዐይነት መፈጸሙን የትናቱ ውጢት አሳይቷል፡፡ ከስተት ትንተና መጠየቆች የተገኙ መረጃዎችን በማገናዘብ በተገኝው የጥናቱ ውጢት መሰረት ዋና ዋና ሲሆኑ የሚችሉ የስተት ምንጮች የጹፍ ቋንቋ አጠቃቀምና አወቃቀር ደንብን አለማወቅ ጸፍትን አለመለማመድ እለታዊ መማርና የማስተማር ዝነባሌና የተሳሳተ የጽንሰ- ሃሳብ ገንዛቤ መሆናችው ተገፆል፡፡ በጥናቱ አጠቃላይ ውጤት ላይ በመመርኮዝም ክፍል ውስጥ ትምህርት ሂደት የሰዋሰው ትምህርት ይዘትን የመምህራን ስልጣን የማስተማር ዘዴ ን ስራተ-ትምርት ዝግጅትን የመገናኛ ብዙሃንና የአፍ መፍቻ ቋንቋን በሚመለከት ያጭርና የረጅም ጊዜ የመፍቴሄ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡

Description

Keywords

Citation