የመማሪያ ክፍል የድርድር ዲስኩር መንስኤ፣ ብልሃትና መፍትሔ ትንተና

No Thumbnail Available

Date

2009

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚካሄደውን የድርድር ዲስኩር መንስኤ፣ ብሌሃትና መፌትሔ በመተንተን የመስተጋብሩን ሂደት መረዳት ነው፡፡ የጥናቱ መነሻ ጥያቄዎችም ለድርድር ክንውን መነሻ የሚሆኑት መንስኤዎች ምን ምን ናቸው? ለድርድር ክንውኑ መነሻ የሆኑት ችግሮች መፌትሔ የሚያገኙባቸው ብልሃቶችስ ምን ምን ናቸው? የዴርዴር ክንውኑ እንዲሳካ እና እንዳይሳካ የሚያደርጉት ተለዋዋጮች ምን ምን ናቸው? የሚሉት ናቸው፡፡ እነዙህን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ እንዲቻልም ዓይነታዊ የምርምር ዘዴን በመከተል የንግግር ልውውጥ ትንተና አቀራረብ ተግባራዊ ተደርጓሌ፡፡ በዚህ አቀራረብ መሠረት፣ በደብረብርሃን ከተማ በሚገኙ ሦስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ሰባት የዘጠነኛ ክፍል የአማርኝ ቋንቋ መምህራን በዓላማ ተኮር የንሞና ስሌት ተመርጠዋል፡፡ እነዚህ መምህራን በክፍል ውስጥ ገብተው ሲያስተምሩ ለሃያ አንድ ክፍለጊዛያት በመቅረጸምሥል ከተሰበሰበው መረጃ መካከል አስራ አራቱ ወደምዝግብ መረጃነት ተቀይረዋል፡፡ በድርድር ክንውን ሞዴል መሠረት ለትንተናው የሚሆኑ ውሁዳሃዶችም ከምዝግብ መረጃው ተለይተውና የጥናቱን ጥያቄዎች መመለስ በሚያስችለበት መንገድ በሦስት ከተከፈሉ በኋላ በመናገር ተራ ልውውጥ ሥርዓት ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤቶችም፣ በድርድር ክንውኑ መነሻ የሆኑት መንስኤዎች ሰዋስው ነክ ጉዳዮች፣ ተገቢ ያልሆኑ የቃላት ምርጫ፣ ቋንቋ ነክ ፅንሰሐሳቦች፣ የተባለውን በትክክል አለማዳመጥ፣ የግሌጽነት መጓደል፣ መላምትን ማረጋገጥ እና ተጨማሪ መረጃ መሻት ናቸው፡፡ ስለዚህ የድርድር ክንውን የተማሪዎቹን የቋንቋ ግብኣት፣ የቋንቋ አፍልቆትና የግብረመልስ ፍላጎት ለማሟሊት ሲባል ተከናውኗል፡፡ ችግሮቹ ተስተካክለው መፍትሔ ያገኙባቸው ብሌሃቶችም አእምሯዊና ማህበራዊ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ አእምሯዊ ብልሃቶች ማስተጋባት፣ ማውጣጣት፣ ማስሞላትና ማብራሪያ መጠየቅ ሲሆኑ ማኅበራዊ ብሌሃቶቹ ደግሞ ማመሳከር፣ እገዛ መሻት፣ አብሮ ማዋቀር፣ መደጋገፍ፣ መፍካከር፣ ሣቅና ዝምታ ናቸው፡፡ ስለዚህ ተሳታፊዎቹ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በድርድር ክንውን ለመፍታት እንዳስፈላጊነታቸው አእምሯዊና ማኅበራዊ ብልሃቶችን እያሰባጠሩ ተገልግለውባቸዋል፡፡ የድርድር ክንውኑ እንዲሳካ እና እንዳይሳካ ያደረጉት ተለዋዋጮችም ተገኝተዋል፡፡ የተሳካ ያደረጉት ለመረዳት እንከኖች ትኩረት መስጠት፣ ድጋፍ ማዴረግ፣ ትምህርታዊ ባህሪን መሊበስ፣ የንግግር ልውውጡን በአግባቡ መምራት፣ በፍሊጎት መሳተፍና በቂ የመናገሪያ ጊዜ መስጠት ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዙህ ብልሃቶች ለትምህርቱ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያደረጉ ጠንካራ ጎኖች ናቸው፡፡ በአንጻሩ ግልጽ እርማት፣ አስተካክሎ መድገም፣ መልመጃው ከተማሪዎቹ ችሎታ በላይ ወይም በታች መሆን፣ በተሳታፊዎቹ መካከል የችሎታ ልዩነት አለመኖር፣ የቆይታ ጊዜና የእገዛ ማነስ እንዲይሳካ ያደረጉት ተለዋዋጮች ናቸው፡፡ ስለሆነም እነዚህ ብሌሃቶች በመስተጋብሩ ላይ ችግር መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ የጥናቱን ውጤት መሠረት በማድረግም የመምህራን ትምህርት ሥልጠና ሲዘጋጅ በድርድር ክንውን ሳቢያ ለሚገኘው ትምህርታዊ ፊይዲ ትኩረት ቢሰጥ፣ መልመጃዎች የተማሪውን የአእምሮ ቀሪብ ዕድገት የሚመጥኑ ሆነው ቢዘጋጁ፣ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የክፍል ውስጥ መስተጋብራቸውን በመቅረጸምሥሌ በመቅረጽ፣ በመተንተንና በማንጸባረቅ የማስተማር ዘዴያቸውን ይበልጥ ያሻሽሉ ዘንድ ሥልጠና ቢሰጣቸው የሚሉ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡ በመጨረሻም የዴርዴር ክንውን በተለያዩ ዓውድች ጥናት ይደረግበት ዘንድ የሚያመለክቱ የምርምር ጉዲዮች ተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

Citation