በወላይታና ጋሞ ምሳሌያዊ ንግግሮች የሚታዩ ፆታ ተኮር አዎንታዊና አሉታዊ ተባልጦዎች ትንተና
No Thumbnail Available
Date
2006-07
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ አላማ በጋሞና በወላይታ ብሄረሰብ ቋንቋ የወንድና የሴት አዎንታዊ እና አሉታዊ ተባልጦን የሚያሳዩ ምሳሌያዊ ንግግሮችን ለይቶ በማመልከት የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በገላጭ የምርምር ዘዴ ሲሆን የጥናቱ የመረጃ ውጤት ትንተና ከቃለ-መጠይቅ ከተገኘው ውጤትና በክለሳ ድርሳናት ከተነሳው ሀሳብ ጋር በማስማማት ጽሁፋዊ ትንተና ተሰጥቷል፡፡ በትንተናው የተደረሰበት ውጤትም በሴቶች ላይ የሚነገሩ ምሳሌያዊ ንግግሮች በአብዛኛው አሉታዊ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ በመቀጠልም ጥናቱ የሚከተሉትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች በመጠቆም ተጠናቋል፡፡ ህብረተሰቡም በሴቶች ላይ በሚነገሩ አሉታዊ ምሳሌዎች ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው እና የህብረተሰቡን አመለካከት በመለወጥ ሴቶች ደራሲዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ተዋናዮች፣ ገበሬዎች፣ ሀኪሞች፣ አስተዳዳሪዎች፣ እናትም፣ እህትም፣ ሀገርም ከመሆን የማይታቀቡ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሆኑ በመግለጽ በአሉታዊ ይነገሩ የነበሩትን ምሳሌያዊ ንግግሮችን መለወጥ እንደሚገባቸው ማስገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
Description
Keywords
ምሳሌያዊ ንግግሮች