የኢትዮጲያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በአማርኛ አንብቦ የመረዳት ችሎታ በተመረጡ የአዲስ አበባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች

No Thumbnail Available

Date

2001-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዓቢይ ዓላማ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ማጥናት ነዉ፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ ውሰጥ ከሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በናሙናነት በተመረጡት ሦስት ትምህርት ቤቶች የዘጠነኛ ከፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ሁሉንም የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎቸ በጥናቱ ውስጥ ማካተትም ከአቅም በላይ ስለሆነ የተወሰኑ ተማሪዎች በናሙናነት ተመርጠው ጥናቱ ተካሂዳል፡፡ ለጥናቱ ያገለገሉት የመረጃ ማሰባሰቢያ መሣሪያዎእን ለመምህራን የተሠራጨ የጹሑፍ መጠይቅ፤ የክፍል ውስጥ የንባብ ትምህርት ምልከታ እና አንብቦ የመረዳት ፈተና ናቸው፡፡ መምህራንን የጹሑፍ መጠይቅ በማስምላት፤ በክፍል ውስጥ በሚሰጠው የንባብ ትምህርት ላይ ምልከታ በማካሄድ፤ ለተጠኝ ተማሪዎቹ አንብቦ የመረዳት ፈተና በመፈተን መረጃዎችን ተሰባስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎችም ተተንትነዋል፡፡ በጥናቱ የተገኘው ውጤት ጥናቲ የሚመለከታችው ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ለተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ዝቅተኛ መሆን ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋንኞቹ የትምህርቲ አሠጣጥና የመማሪያ መጽሐፍ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ በመጠይቅ በተሰበሰቡት መረጃዎች መሠረት ንባብን ከማሰተማሩና ከመማሪያ መጽሐፍ አኳያ ችግሮች አሉ፡፡ በክፍል ውስጥ የሚሰጠው የንባብ ትምህርት ተማሪዎችን እንደማያሳትፍ፤ አብዛኞቹ ተግባራት በመምህሩ እንደሚከናወኑ፤ ተማሪዎቹ በቂ ልምምድ እንደማያደርጉ በምልከታ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

Description

Keywords

Citation