በከምባትኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ሰዋስው ትምህርትን ለመማር የሚጠቀሙባቸው የመማር ብልሃቶች ትንተና (በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2022-06

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በከምባትኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የስዋሰው መማር ብልሃቶችን መተንተን ነው፡፡ ጥናቱ በዚህ አብይ ዓላማ ስር ከቋንቋ መማር ብልሃቶች መካከል የትኞቹን አዘውትረው በመጠቀም ትምህርቱን እንደሚከታተሉ መለየት ለሚለት ንዑሳን ዓላማዎቹ ጥናቱ ምላሽ አስገኝቷል። ጥናቱ በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን አንጋጫ ወረዲ ውስጥ ከሚገኙ ስድስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል በአመቺ የናሙና አመራረጥ ዘዴ በተመረጡ ሦስት ትምህርት ቤቶች ዘጠነኛ ክፍል የሚማሩ በከምባትኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ 106 ከሦስቱም ትምህርት ቤት ተማሪዎች በቀላል እጣ ናሙና (Simple Random Sampling) ዘዴ በመውሰድ፣ በዓይነታዊ የምርምር ዘዴ የተካሔደ ገላጭ ጥናት ነው። በዚህ መሰረት የሁለተኛ ቋንቋ በቀላል ለመማር በተለያየ መንገድ እገዛ ያደርጋሉ በሚባለት ርቱዕ እና ኢርቱዕ ብልሃቶች ስር በቀረቡ ንዑሳን ብልሃቶች ላይ በማተኮር የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ ሰዋስውን ሲማሩ ብልሃቶቹን ምን ያህል እንደሚጠቀሙባቸው ለመመርመር ተሞክሯል። ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በዋናነት በሁለት የተደራጀ የጽሁፍ መጠይቅ አገልግሎት ላይ ውሎል። እንደ አጋዥ መረጃ መሰብሰቢያነት ደግሞ ቃለ መጠይቅ ጥቅም ላይ ውሎል። በተሰበበው መረጃ የትንተና ውጤት መሰረትም፣ተማሪዎቹ የአማርኛ ቋንቋ ሰዋስውን የሚማሩበት መንገዴ ለሰዋስው መማሪያ እገዛ የሚያደርጉትን የመማር ብልሃቶች በስፋት በመገልገል ላይ የተመሰረተ አይደለም። በመረጃው መሰብሰቢያ መሳሪያዎች በሰጡት መረጃዎች መሰራት በትንተናው ውጤት አብዚኛዎቹ ተማሪዎች የታላሚውን ቋንቋ አዳዲስ ሰዋስዋዊ ብልሃቶችን በመጠቀም በአዕምሯቸው በመስተወስ የቀድመውን እውቀታቸውን ከአሁኑ ትምህርት ጋር እያስተሳሰሩ መማር፣ይዘቶችን በማቧደን፣የሀረጋትን አወቃቀር መተንተንና ልዩ ልዩ ምልክቶችን መጠቀም የሚከብደ መዋቅሮችን ከአፍ መፍቻ ቋንቋ በመፈለግ ማተካከት ለሰዋስው ትምህርታቸው ከመረጡአቸው ብልሃቶች ሰዋስውን ለመገንዘብ ዕቅድ ማውጠት አብዚኛዎቹ ተማሪዎች በፍጹም እንደመይጠቀሙ የተገኛው መረጃ ትንተና ውጤት ሲያመለክት እንደመፍትሄ የርቱዕና የኢ-ርቱዕ ብልሃቶችን የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች በመማር ማስተማር ይሁን በተግባቦት ሂደት ተማሪዎች የሚጠቀሙባቸውን መንጋድ መምህረን ጥቆማ ቢሰጡ እና ተማሪዎች በራሰቸው ጥረት ኃሊፊነት ወስደው ብልሃቶችን በሚገባ ቢያከነወኑ የተሸለ ነው፡፡

Description

Keywords

በከምባትኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ:የስዋሰው መማር ብልሃቶች

Citation