የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበር ግምገማ በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በሶስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች

dc.contributor.advisorዶ/ር ታደሰ ሲባሞ
dc.contributor.authorአማረ ግርማ
dc.date.accessioned2023-12-13T07:27:15Z
dc.date.available2023-12-13T07:27:15Z
dc.date.issued2023-10
dc.description.abstractየዚህ ጥናት ዐቢይ ዓላማ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበር በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በሶስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መፈተሸ ነው፡፡ ጥናቱም ለመረጃ አሰባሰቡና አተናተኑ መጠናዊና አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ (Mixed approach) ነው፡፡ ይህ ጥናት የተካሄደው በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሊጋባ በየነ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ትግል ፍሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አብዮት ጮራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም በ 8ኛ ክፍል በመማር ያሉ ተማሪዎች እና የደረጃው መምህራን ተሳትፈዋል፡፡ ከእነዚህም ተማሪች እና መምህራን መረጃዎች የተሰበሰቡት ከክፍል ምልከታ፣ ለተማሪዎችና ለመምህራን ከተሰራጨ የጽሁፍ መጠይቅ ነው፡፡ የትንተናውም ውጤት በመቶኛ ተሰልቶ በገለጻ ስልት ተብራርቷል፡፡ የትንተናው ውጤቱም በተተኳሪ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ለንግግር ትምህርት ማስተማሪያ ዘዴዎች ትኩረት ያልሰጡ መሆናቸው፣ በተማሪ ተኮር አቀራረብ ትኩረት የተሰጣቸው ትብብራዊነት በተማሪዎች መካከል እንዲታይ ያለማድረጋቸው፣ ተማሪዎችን ለማነቃቃት መሰራት የነበረባቸው ተግባራት መረሳታቸው፣ የአውድ ዝግጅት ትኩረት የይድረስ መሆኑ፣ ሁሉንም ተማሪዎች በትምህርቱ እኩል ያለማሳተፍ እና ለመናገር የማይደፍሩ ተማሪዎችን እንዲሳተፉ ያለማድረግ እና የሚመረጡ የንግግር ማስተማሪያ ርዕሶች ከተማሪዎች የእለት ተእለት ህይወታዊ እንቅስቃሴ ጋር የማጣጣም ስራ አለመሰራቱን ተመላክቷል፡፡ ስለሆነም፣ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የታዩ ክፍተቶች ከመምህራን ትኩረት ማነስ የመጡ ናቸዉ፡፡
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/823
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.subjectየአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል
dc.titleየ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበር ግምገማ በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በሶስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
አማረ ግርማ.pdf
Size:
717.37 KB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: