የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበር ግምገማ በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በሶስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች

No Thumbnail Available

Date

2023-10

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት ዐቢይ ዓላማ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል የክፍል ውስጥ አተገባበር በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር በሶስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መፈተሸ ነው፡፡ ጥናቱም ለመረጃ አሰባሰቡና አተናተኑ መጠናዊና አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ (Mixed approach) ነው፡፡ ይህ ጥናት የተካሄደው በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሊጋባ በየነ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ትግል ፍሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አብዮት ጮራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም በ 8ኛ ክፍል በመማር ያሉ ተማሪዎች እና የደረጃው መምህራን ተሳትፈዋል፡፡ ከእነዚህም ተማሪች እና መምህራን መረጃዎች የተሰበሰቡት ከክፍል ምልከታ፣ ለተማሪዎችና ለመምህራን ከተሰራጨ የጽሁፍ መጠይቅ ነው፡፡ የትንተናውም ውጤት በመቶኛ ተሰልቶ በገለጻ ስልት ተብራርቷል፡፡ የትንተናው ውጤቱም በተተኳሪ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ለንግግር ትምህርት ማስተማሪያ ዘዴዎች ትኩረት ያልሰጡ መሆናቸው፣ በተማሪ ተኮር አቀራረብ ትኩረት የተሰጣቸው ትብብራዊነት በተማሪዎች መካከል እንዲታይ ያለማድረጋቸው፣ ተማሪዎችን ለማነቃቃት መሰራት የነበረባቸው ተግባራት መረሳታቸው፣ የአውድ ዝግጅት ትኩረት የይድረስ መሆኑ፣ ሁሉንም ተማሪዎች በትምህርቱ እኩል ያለማሳተፍ እና ለመናገር የማይደፍሩ ተማሪዎችን እንዲሳተፉ ያለማድረግ እና የሚመረጡ የንግግር ማስተማሪያ ርዕሶች ከተማሪዎች የእለት ተእለት ህይወታዊ እንቅስቃሴ ጋር የማጣጣም ስራ አለመሰራቱን ተመላክቷል፡፡ ስለሆነም፣ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የታዩ ክፍተቶች ከመምህራን ትኩረት ማነስ የመጡ ናቸዉ፡፡

Description

Keywords

የአማርኛ ቋንቋ የመናገር ክሂል

Citation