የእኔነት ሐተታ በተመረጡ የአማርኛ ረጅም ልቦለዶች
dc.contributor.advisor | አለማየሁ, ይደግ (PhD) | |
dc.contributor.author | ወልደኪዳን, ሰብለ | |
dc.date.accessioned | 2019-02-08T06:56:47Z | |
dc.date.accessioned | 2023-11-09T04:06:51Z | |
dc.date.available | 2019-02-08T06:56:47Z | |
dc.date.available | 2023-11-09T04:06:51Z | |
dc.date.issued | 2010-12 | |
dc.description.abstract | ሥነ ጽሑፍ በቋንቋ ይበጃል፤ ቋንቋ በሰው ልጅ ማንነት ስሪት ውስጥ ሰፊውን ድርሻ ይወስዳል፤ ይህ በመሆኑም በሥነ ጽሑፍ ጥናት ልማድ ውስጥ የሰውን ልጅ የማንነት ጥያቄ እና የራስ ማንነት ምስል ስሪት እንዴትነት መመርመር አንዱ አካሄድ ነው፡፡ ይህም ጥናት በሰው ልጅ ማንነት እና ለማንነቱም ባለው የራስ ምስል ንቃት ላይ የሚያተኩረውን የእኔነት/Subjectivity ፅንሰ ሃሳብ መሰረት በማድረግ፣ የተመረጡ የአማርኛ ረጅም ልቦለዶችን ለመፈተሸ የተደረገ ሙከራ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ምክንያት የሆነው፣ በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ላይ የተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ለእኔነት ፅንሰ ሃሳብ ቦታ እንዳለው የሚያመላክቱ ቢሆኑም፣ ሥነ ጽሑፉን ከዚህ ፅንሰ ሃሳብ አንፃር የተመለከተ ጥናት ባለመኖሩ በዘውጉ ጥናት ውስጥ የፈጠረውን ክፍተት መመልከት ነው፡፡ ጥናቱ በእኔነት ፅንሰ ሃሳብ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል የአንድ ሰው ማንነት እንዲሁም የራስ ማንነት ምስልን ምንጭ ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ በማንነት እና በእኔነት መካከል ስላለ ግንኙነት፣ በአንድ ሰው ማንነት እንዲሁም የራስ ማንነት ምስል ላይ ሌላ/Other፣ ስላለው ድርሻ ይህም በሥነ ጽሑፉ ውስጥ የቀረበበትን መንገድ ለመመልከት ሞክሯል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ የገፀባህሪያት ሕይወት ከተለያየ አቅጣጫ መመልከትን ስለሚጠይቅ ከሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ረጅም ልቦለድን መርጧል፡፡ በዚህ መሰረት የበዓሉ ግርማ፣ ከአድማስ ባሻገር፤ የአዳም ረታ፣ ግራጫ ቃጭሎች፤ የአለማየሁ ገላጋይ፣ የብርሃን ፈለጎች እና በፍቅር ሥም የእኔነትን ሐተታ ለማሳየት አመች ናቸው በሚል በጥናቱ ተካተዋል፡፡ በጥናቱ እነዚህን ልቦለዶች ለመተርጎም በተለያዩ የጥናት መስኮች የቀረቡ የእኔነት ፅንሰ ሃሳብን ማብራሪያዎች በመመርመር የJacques Lacan ትንተና የተመረጠ ሲሆን፣ ማብራሪያውን ያቅፋሉ ለልቦለዶቹም በጥልቀት መብራራት ይረዳሉ የተባሉት ፅንሰ ሃሳቦች ማለትም ፋለስ፣ ፍላጎት እና ባይተዋርነት የትኩረት ማዕከል ተደርገዋል፡፡ በእነዚህ ፅንሰ ሃሳቦች መሰረት ምንባባዊ የትንታኔን ዘዴን በመከተል የተብራሩት ልቦለዶች እንደሚያሳዩት፣ ለሰው ልጅ ማንነት እና ለሚኖረው የማንነት የራስ ምስል ወይም እኔነት መፈጠር ምክንያት የሆነ እና እኔ/Subject እንዲህ ነው ብሎ ሊገልፀው የማይችለው ድብቅ ኃይል አለ፡፡ ይህ ኃይል የሚመለከተውም ሕፃኑ/ኗ በልጅነት ከእናቱ/ቷ ጋር ያለውን/ያላትን ግንኙነት እና በዚህ ግንኙነት መካከል ጣልቃ የሚገባውን አባት ነው፡፡ በልቦለዶቹ ውስጥ ያሉ ገፀባህሪያት በልጅነት ሕይወታቸው በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በአባታቸው እንደተገፉ የታየ ሲሆን፣ ይህም ያሳጣቸው ነገር እንዳለ የሚያስቡ ሆነው መቅረባቸው ታይቷል፡፡ ይህም በመሆኑ የእናትን ወይም የመጀመሪያዋ ሌላን ትኩረት ለማግኘት ያጥራሉ፡፡ በመሆኑም፣ ገፀባህሪያቱ በአባት የተነጠቁትን ይህን እጦት ለመሙላት ወይም በሌላ ተፈላጊ ለመሆን የራስ ፍላጎታቸውን ወደ ጎን በማለት የሌላን ፍላጎት ፍላጎታቸው በማድረግ ይታያሉ፡፡ ትረካዎቹ እንደሚያሳዩት፣ ገፀባህሪያቱ የሌላን ፍላጎት ፍላጎት ማድረጋቸው፣ ራሳቸውን በመሆን እና ሌላ የሚፈልገውን አካል በመሆን መካከል የተከፈሉ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ በመሆኑ፣ ባይተዋርነት በትንታኔ የተካተቱት ገፀባህሪያት ሁሉ ዕጣ ፈንታ ሆኗል፡፡ በልቦለዶቹ፣ እነዚህ የሰው ልጅ ማንነት እና የራስ ማንነት ምስል ሃሳቦች በህልም እና በትረካ መዋቅር ስልት ቀርበዋል፡፡ | en_US |
dc.identifier.uri | http://etd.aau.edu.et/handle/123456789/16317 | |
dc.language.iso | am | en_US |
dc.publisher | Addis Ababa University | en_US |
dc.subject | ቋንቋ በሰው ልጅ ማንነት ስሪት ውስጥ ሰፊውን ድርሻ ይወስዳል | en_US |
dc.title | የእኔነት ሐተታ በተመረጡ የአማርኛ ረጅም ልቦለዶች | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |