በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን የመማር ብልሃቶች ትንተና (በሩፍሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

dc.contributor.advisorዳዊት ፍሬህይወት (ዶ/ር)
dc.contributor.authorያሲን አደም ጌታነህ
dc.date.accessioned2023-12-25T07:37:48Z
dc.date.available2023-12-25T07:37:48Z
dc.date.issued2022-07
dc.description.abstractየዚህ ጥናት አብይ አላማ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የቃላት መማር ብልሃቶችን መለየትና መተንተን ነበር፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሩፍሴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ በአመቺ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 70 የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የጥናቱ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችም፡- የጽሁፍ መጠይቅ በዋናነት ሲሆን ቃለመጠይቅ በአጋዥ የመረጃ መሰብሰቢያነት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎችም በአይነታዊና መጠናዊ የመረጃ መተንተኛ ተተንትነው ገላጭ በሆነ ስልት ቀርበዋል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረትም በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን የሚለማመዱበት ስልት ቃላትን የመማር ብልሃት አጠቃቀማቸው በብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ተጠኚ ተማሪዎች በትውስታ ብልሃት ስር ከቀረቡላቸው ስድስት ብልሃቶች አብዛኞቹ 177(252.9%)ያህልጊዜ በመደጋገም አልፎ አልፎ እንደሚጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ አዕምሮታዊ ብልሃቶችን በተመለከተ ለተማሪዎች ከቀረቡላቸው አስራአንድ ጥቅል ብልሃቶች አብዛኞቹን ብልሃቶች 425(607%)ያህል ጊዜ ብልሃቱን በመደጋገም አልፎ አልፎ ተጠቅመዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ አካካሽ ብልሃቶችን በተመለከተ 101(144.3%)ያህል ጊዜ ደጋግመው ሁልጊዜ እንደተጠቀሙ ሲገልጹ፣ ልዕለአዕምሮታዊ ብልሃቶችን ደግሞ 122(174.2%) ያህልጊዜ ደጋግመው አልፎአልፎ እንደሚጠቀሙ መረጃው ያመለክታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም በስሜትነክ ቁጥጥር ብልሃቶች ስር ከቀረቡላቸው ሶስት ብልሃቶች አብዛኞቹ ተማሪዎች144(205.5%) ጊዜ በመደጋገም አልፎ አልፎ ሲጠቀሙ፣ማህበራዊ ብልሃቶችን በተመለከቱ ደግሞ 61(87.1%) ያህል ጊዜ አልፎ አልፎ በመደጋገም እንደሚጠቀሙባቸው የትንተናው ውጤት ያሳያል፡፡ በመሆኑም ተጠኚ ተማሪዎች በተደጋጋሚ አብዝተው የሚጠቀሙት አካካሽ ብልሃቶችን ሲሆን ሌሎቹን ብልሃቶች ግን ሁልጊዜ በመደጋገም አብዝተው እንደማይጠቀሙባቸው ውጤቱ ያሣያል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ተማሪዎች በራሳቸው ጥረት እንዲለማመዱ መንገድ ቢያመቻቹላቸውና ክትትል ቢያደርጉ፣ እንዲሁም የአማርኛ መማርያ መጽሐፍ አዘጋጆች የቃላት መማር ብልሃትን እንደ አንድ የቃላት ትምህርት ማቅረቢያ መንገድ ቢጠቀሙበት የሚልየመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/1157
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.subjectየቃላት መማር ብልሃቶች፡ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ
dc.titleበኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን የመማር ብልሃቶች ትንተና (በሩፍሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ያሲን አደም ጌታነህ.pdf
Size:
1.81 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: