በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን የመማር ብልሃቶች ትንተና (በሩፍሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

No Thumbnail Available

Date

2022-07

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Abstract

የዚህ ጥናት አብይ አላማ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የቃላት መማር ብልሃቶችን መለየትና መተንተን ነበር፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሩፍሴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ በአመቺ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 70 የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የጥናቱ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችም፡- የጽሁፍ መጠይቅ በዋናነት ሲሆን ቃለመጠይቅ በአጋዥ የመረጃ መሰብሰቢያነት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎችም በአይነታዊና መጠናዊ የመረጃ መተንተኛ ተተንትነው ገላጭ በሆነ ስልት ቀርበዋል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረትም በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቃላትን የሚለማመዱበት ስልት ቃላትን የመማር ብልሃት አጠቃቀማቸው በብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ተጠኚ ተማሪዎች በትውስታ ብልሃት ስር ከቀረቡላቸው ስድስት ብልሃቶች አብዛኞቹ 177(252.9%)ያህልጊዜ በመደጋገም አልፎ አልፎ እንደሚጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ አዕምሮታዊ ብልሃቶችን በተመለከተ ለተማሪዎች ከቀረቡላቸው አስራአንድ ጥቅል ብልሃቶች አብዛኞቹን ብልሃቶች 425(607%)ያህል ጊዜ ብልሃቱን በመደጋገም አልፎ አልፎ ተጠቅመዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ አካካሽ ብልሃቶችን በተመለከተ 101(144.3%)ያህል ጊዜ ደጋግመው ሁልጊዜ እንደተጠቀሙ ሲገልጹ፣ ልዕለአዕምሮታዊ ብልሃቶችን ደግሞ 122(174.2%) ያህልጊዜ ደጋግመው አልፎአልፎ እንደሚጠቀሙ መረጃው ያመለክታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም በስሜትነክ ቁጥጥር ብልሃቶች ስር ከቀረቡላቸው ሶስት ብልሃቶች አብዛኞቹ ተማሪዎች144(205.5%) ጊዜ በመደጋገም አልፎ አልፎ ሲጠቀሙ፣ማህበራዊ ብልሃቶችን በተመለከቱ ደግሞ 61(87.1%) ያህል ጊዜ አልፎ አልፎ በመደጋገም እንደሚጠቀሙባቸው የትንተናው ውጤት ያሳያል፡፡ በመሆኑም ተጠኚ ተማሪዎች በተደጋጋሚ አብዝተው የሚጠቀሙት አካካሽ ብልሃቶችን ሲሆን ሌሎቹን ብልሃቶች ግን ሁልጊዜ በመደጋገም አብዝተው እንደማይጠቀሙባቸው ውጤቱ ያሣያል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ተማሪዎች በራሳቸው ጥረት እንዲለማመዱ መንገድ ቢያመቻቹላቸውና ክትትል ቢያደርጉ፣ እንዲሁም የአማርኛ መማርያ መጽሐፍ አዘጋጆች የቃላት መማር ብልሃትን እንደ አንድ የቃላት ትምህርት ማቅረቢያ መንገድ ቢጠቀሙበት የሚልየመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡

Description

Keywords

የቃላት መማር ብልሃቶች፡ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ

Citation