የዋና ገፀባህሪ አሳሳል የአውሎ ንፋስ ዳንኪረኞች ረዥም ልቦለድ ውስጥ
No Thumbnail Available
Date
2001-06
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
Abstract
ይህ ጥናት የዋና የገፀባህሪ አሳሳል በ የአውሎ ንፋስ ዳንኪረኖች ረዥም ልቦለድ
ውስጥ በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ በተጠቀሰው ልቦለድ ውስጥ ዋና ገፀባህሪ እንዴት
እንደተሳለ ለማየት ተሞክሯል፡፡ ደራሲው ዋና ገፀባህሪ ሲስል አካላዊና ህሊናዊ መልኩን
ለአንባቢ በሚያቀርብበት ወቅት የተጠቀመበትን ዘዴ ለመጠቆም ድክመትና ጥንካሬውን
ለማሳየት ነው ጥናቱ የተካሄደው፡፡
ጥናቱ በሦስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ የተቀመጠ ሲሆን ርዕሱን በተመለከተ
በምዕራፍ ሁለት ንድፈ ሀሳባዊ ትንተና ተገልፆዋል፡፡ በምዕራፍ ሦስት ዋነኛ የጥናቱ
ትኩረት የሆነው የአውሎ ንፋስ ዳንኪረኖች ዋና ገፀባህሪ አካላዊና ህሊናዊ ገለፃ ትንታኔ
ተሰጥቶበታል፡፡
በመፅሀፉ ውስጥ ስለ ገፀባህሪው አካላዊ ገለፃ በዘርዛሪ/ርዕቱ አቀራረብ በመፀሀፉ
መግቢያ በአንድ ቦታ መገኝቱ ከድክመት የሚታይ ነው፡፡ ህሊናዊ መልክንም አብዛኛውን
ግዜ በተውኔታዊ መንገድ ከማቅረብ ይልቅ በተራኪው አማካኝነት ነው የሚያቀርበው፡፡
ሌላው ስለዋና ገፀባህሪው የተሳለ ገለፃ ማግኘት አልተቻለም በተለይ ሌሎች
ገፀባህሪያት ስላሉ የሚሉት ነገር ባለመኖሩ ተጨባጭ እና ተአማኒ ገፀባህሪ ለማግኘት
አልተቻለም፡፡ ገፀባህሪው በታሪኩ እድገት ላይ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ተደርጐ ተመርጦ
መቅረቡ በተለይ ህሊናው መልኩ በልቦለድ ውስጥ በዚያ መልክ መቀረፁ የታሪኩን
ዕድገት ወደፊት እንዲራመድ አድርጐታል፡፡ ነገር ግን ስለገፀባህሪው መገለፅ የሚገባቸው
ነገሮች በሙሉ ተሟልተው ባለመቅረባቸው የልቦለድ ታሪክ ዕድገት አዝጋሚ እንዲሆን
አድርጐታል፡፡
ሠ
Description
Keywords
የአውሎ ንፋስ ዳንኪረኞች