የዝዋይ ደስያት ገዳምና አድባራት ተረኮችና ቁሳዊ ባህሎች ጥናት
No Thumbnail Available
Date
2006-01
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
ይህ ጥናት በዝዋይ ሐይቅ ውስጥ በሚገኙ ገዳምና አድባራት ላይ የተካሄደ ሲሆን ተረክና ቁሳዊ ባህል የሚባሉትን የፎክሎር ዘውጎች የሚመለከት ነው፡፡ ጥናቱ ይዞት የተነሳው ዋና ዓላማም ተረኮቹን በመተንተንና ቁሳዊ ባህሎቹን በመመርመር ያላቸውን ተምሳሌት ማሳየት ነው፡፡ ለርዕሰ ጉዳዩ መመረጥ እንደ ዓብይ ምክንያት የሚቀጠቀሱት የዝዋይ ደስያት በታሪክ አጋጣሚ የታቦተ ጽዮን መሸሸጊያ መሆናቸውን የሚናገሩ ተረኮችና ቁሳዊ ባህሎች በመኖራቸውና እንደ ገዳማውያን ሕይወታቸው ሀገዳምና አድባራቱ ጋር ያቆራኙ ማህበረሰቦች በመገኘታቸው ሲሆን በአጠቃላይ በእያተ ክርሲያናቱ የሀገራችን የታሪክ መዛግብት ሆነው የቆዮ መሆናቸውን የሚያስረግጡ መረጃዎች በስፍራው መታየታቸው ነው፡፡ የጥናቱ ዓላማ ግብ እንዲመታና የምርምር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከቤተ መጻህፍት፣ ከመረጃ መረብና ከመስክ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም የተሰበሰቡት በቃለመጠይቅና በምልከታ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ነው፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በመቅረጽ ድምጽ፣ በፎቶና ቪዲዮ ካሜራ እንዲሁም ማስታወሻ ደብተር ተይዘዋል፡፡