የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎቹን ለማጎልበት የሚኖረው ሚና (በቀርሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት፣ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

dc.contributor.advisorዳዊት ፍሬህይወት (ዶ/ር)
dc.contributor.authorሲሳይ ነጋሽ
dc.date.accessioned2023-12-13T07:30:35Z
dc.date.available2023-12-13T07:30:35Z
dc.date.issued2022-07
dc.description.abstractየዚህ ጥናት አብይ አላማ የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎቹን ለማጎልበት የሚኖረውን ጠቀሜታ መመርመር ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስም ጥናቱ የተከተለው ከፊል ሙከራዊ የምርምር ዘዴን ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በሞጆ ከተማ በሚገኘው ቀርሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን የተመረጠውም በአመቺ የንሞና አመራረጥ ዘዴ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በ2015ዓ.ም በመማር ላይ የሚገኙ 68 የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ በቀላል እጣ ናሞና ዘዴ ተመርጠው አስፈላጊው መረጃ ተሰብስቧል፡፡ መረጃው የተሰበሰበውም በቅድመ ትምህርት ፈተናና ቃለ-መጠይቅ እንዲሁም በድህረ ትምህርት ፈተና ነው፡፡ ጥናቱ ወደተግባር ሲገባ መጀመሪያ በሙከራ ቡድንና በቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች መካከል ጉልህ ልዩነት አለመኖሩን ለማረጋገጥ ቅድመ ፈተና ተሰጥቷል፡፡ በውጤቱ መሰረትም በቅድመ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና በተገኘው አማካይ ውጤት ሁለቱ ቡድኖች ከልምምዱ በፊት የጎላ የአንብቦ መረዳት ችሎታ ልዩነት እንደሌላቸው የስታትቲክ ስሌቱ (p>0.05) አረጋግጧል፡፡ የቅድመ ፈተና ውጤቱን በማስከተል የሙከራ ቡድኑ የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ በማስተማር ዘዴ አቀረራብ ስልት እንዲሁም የቁጥጥር ቡድኑ በተለመደው መንገድ ክሂሎቹን ነጥሎ በማቅረብ እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ ትምህርቱ ለተከታታይ ለስምንት ሳምንታት (ሁለት ወራት) ከተሰጠ በኋላ ድህረ ትምህርት ፈተና ተሰጥቷል፡፡ ውጤቱንም በገለጭ ሰታቲስቲክስና በባእድ የናሙናዎች ቲ-ቴስት ተተንትኗል፡፡ በዚህም መሰረት የሙከራ ቡድኑ በድህረ ትምህርት ፈተናው አማካይ ውጤት (26.8824) ከቁጥጥር ቡድኑ አማካይ ውጤት (19.5294) በስታትስቲክ ጉልህ ልዩነት (p<0.05) ሆኖ በመገኘቱ የጎላ ልዩነት መመዝገቡ ተረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ የማስተማር ዘዴ የተማሪዎቹን የማነንበብና የመጻፍ ክሂሎች ያሳድጋል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡ የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግም የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የማንበብና የመጻፍ ክሂሎችን ትኩረት በመስጠት በቅንጅት ቢያስተምሩ፤ የመርሐ ትምህርትና የመማሪያ መጻህፍት አዘጋጆችአዲስ መርሃ ትምህርትና የመማሪያ መጻህፍት በሚያዘጋጁበት ወቅት እነዚህን የቋንቋ ክሂሎች በቅንጅት የሚቀርቡበት መንገድ ቢኖርና ለልምምዱም በቂ ክፍለጊዜ ቢመደብለት እንዲሁም ተመራማሪዎች በዚህ ርዕስ ላይ በተለይ አራቱን የቋንቋ ክሒሎች አቀናጅቶ ከማስተማር አኳያ በስፋት ጥናት ቢያደርጉ የተሻለ ይሆናል የሚሉ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡
dc.identifier.urihttp://etd.aau.edu.et/handle/123456789/826
dc.language.isoam
dc.publisherአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
dc.subjectየማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎች
dc.titleየማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎቹን ለማጎልበት የሚኖረው ሚና (በቀርሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት፣ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)
dc.typeThesis

Files

Original bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
ሲሳይ ነጋሽ.pdf
Size:
1.92 MB
Format:
Adobe Portable Document Format
License bundle
Now showing 1 - 1 of 1
No Thumbnail Available
Name:
license.txt
Size:
1.71 KB
Format:
Item-specific license agreed to upon submission
Description: