የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎቹን ለማጎልበት የሚኖረው ሚና (በቀርሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት፣ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)
No Thumbnail Available
Date
2022-07
Authors
Journal Title
Journal ISSN
Volume Title
Publisher
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
Abstract
የዚህ ጥናት አብይ አላማ የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎቹን ለማጎልበት የሚኖረውን ጠቀሜታ መመርመር ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስም ጥናቱ የተከተለው ከፊል ሙከራዊ የምርምር ዘዴን ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በሞጆ ከተማ በሚገኘው ቀርሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን የተመረጠውም በአመቺ የንሞና አመራረጥ ዘዴ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በ2015ዓ.ም በመማር ላይ የሚገኙ 68 የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ በቀላል እጣ ናሞና ዘዴ ተመርጠው አስፈላጊው መረጃ ተሰብስቧል፡፡ መረጃው የተሰበሰበውም በቅድመ ትምህርት ፈተናና ቃለ-መጠይቅ እንዲሁም በድህረ ትምህርት ፈተና ነው፡፡ ጥናቱ ወደተግባር ሲገባ መጀመሪያ በሙከራ ቡድንና በቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች መካከል ጉልህ ልዩነት አለመኖሩን ለማረጋገጥ ቅድመ ፈተና ተሰጥቷል፡፡ በውጤቱ መሰረትም በቅድመ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና በተገኘው አማካይ ውጤት ሁለቱ ቡድኖች ከልምምዱ በፊት የጎላ የአንብቦ መረዳት ችሎታ ልዩነት እንደሌላቸው የስታትቲክ ስሌቱ (p>0.05) አረጋግጧል፡፡ የቅድመ ፈተና ውጤቱን በማስከተል የሙከራ ቡድኑ የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ በማስተማር ዘዴ አቀረራብ ስልት እንዲሁም የቁጥጥር ቡድኑ በተለመደው መንገድ ክሂሎቹን ነጥሎ በማቅረብ እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ ትምህርቱ ለተከታታይ ለስምንት ሳምንታት (ሁለት ወራት) ከተሰጠ በኋላ ድህረ ትምህርት ፈተና ተሰጥቷል፡፡ ውጤቱንም በገለጭ ሰታቲስቲክስና በባእድ የናሙናዎች ቲ-ቴስት ተተንትኗል፡፡ በዚህም መሰረት የሙከራ ቡድኑ በድህረ ትምህርት ፈተናው አማካይ ውጤት (26.8824) ከቁጥጥር ቡድኑ አማካይ ውጤት (19.5294) በስታትስቲክ ጉልህ ልዩነት (p<0.05) ሆኖ በመገኘቱ የጎላ ልዩነት መመዝገቡ ተረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ የማስተማር ዘዴ የተማሪዎቹን የማነንበብና የመጻፍ ክሂሎች ያሳድጋል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡ የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግም የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የማንበብና የመጻፍ ክሂሎችን ትኩረት በመስጠት በቅንጅት ቢያስተምሩ፤ የመርሐ ትምህርትና የመማሪያ መጻህፍት አዘጋጆችአዲስ መርሃ ትምህርትና የመማሪያ መጻህፍት በሚያዘጋጁበት ወቅት እነዚህን የቋንቋ ክሂሎች በቅንጅት የሚቀርቡበት መንገድ ቢኖርና ለልምምዱም በቂ ክፍለጊዜ ቢመደብለት እንዲሁም ተመራማሪዎች በዚህ ርዕስ ላይ በተለይ አራቱን የቋንቋ ክሒሎች አቀናጅቶ ከማስተማር አኳያ በስፋት ጥናት ቢያደርጉ የተሻለ ይሆናል የሚሉ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡
Description
Keywords
የማንበብና የመፃፍ ክሂሎችን አቀናጅቶ ማስተማር ክሂሎች