አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለማሰተማር የተዘጋጀውን መርሀ ትምህርት ትግበራ ግምገማ (በኦርሚያ ከልል 8ኛ ከፍል ናሙናነት)

No Thumbnail Available

Date

1993-05

Journal Title

Journal ISSN

Volume Title

Publisher

አዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Abstract

ይህ ጥናት በ1990 ዓ .ም ሥራ ላይ የዋለውንና አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለማሰተማር የተዘጋጀዉን የ8ኛ ከፍል መርሃ ትምህርት የገመገመ ነው፡፡በዋናነት ለመርሃ ትምህርቱና ለትግበራው የመምህራኑ አመለካከት ምን እንደሚመሰል፤ የሰልጠና ብቃታቸው ምን ያህል እንደሆነ፤ በተማረው ላይ የታየው የአሰራርና የአስተሳሰብ ለውጥ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መርሃ ትምህርቱን ሙሉ ለሙሉም ሆነ በከፈል ተግባራዊ አንዳይሆን የሚያደና ቅፍ ነገሮቸ ምን እንደሆኑ ተመልክቷል፡፡ የመርሃ ትምህርት ትግበራ ግምገማ አስፈላጊና በየጊዜው መካሄድ ያለበት መሆኑን በርካታ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ (Shiundu እና Omulando 1992:61) የሰርዓተ ትምህርት ዝግጅት ዑደታዊ መሆኑንና ግምገማም የዑደቱ አንድ አካል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ግምገማውን ለማካሄድ ደግም መረጃዎች በተለያየ መንገድ ይሰበሰባሉ፡፡ በዚህ ጥናት ርዕሳነ መምህራን ፤ መምህራንና ተማሪዎች በመረጃ ሰጪነት አገልግለዋል፡፡ የፅሁፍ መጠይቆች፤ የምልከታ ቅፆችና የብቃት መለኪያ ፈተና በመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያነት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ከመረጃ ሰጪዎቹ ወካይ ናሙና ለማግኘት ባለብዙ ደረጃ ቡድናዊ ናሙና አወሳሰድ ሰልት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በናሙናነት ከተመረጡት ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፤ መምህራንና ተማሪዎች በተገኘዉ መረጃ መሠረት መምህራን ሰለአዲሱ የትምህርትና ሰልጠና ፓሊሲ ያላቸዉ አመለካከት ዝቅተኛ መሆኑን፤መምህራኑ መረሃ ትምህርቱን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሰፈልጋቸው መሆኑን፤ በአንድ ከፍል የሚማሩ ተማራዎች ቁጥር በርካታ መሆን በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሆኑና፤ ለዓመቱ የቀርበዉን ትምህርት በወቅቱ ለማጠናቀቅ የተመደበው ከፍለ ጊዜ አነስተኛ መሆኑን ከቀረቡት ሦሰት የትምህርት ዓላማዎች የሥነ ልሳን ትምህርት በዝቅተኛ ደረጃ ተግባራዊ መሆኑን ይህም ከከተማ ይልቅ በገጠር ዝቅተኛ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል በመሆኑም ሰለ ፖሊሲው ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ መድረኮችን ማዘጋጀት፤ ሙያቸውን ለማሻሻል አሁን የተጀመረዉን የተልኮ ትምህርት በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል የከፍል ጥበትን ለማስወገድ ግንባታ ማካሄ፤ በሳምንት የተመደበውን ከፍለ ጌዜ ከሁለት ወደ ሦሰት ከፍ ማድረግ፤የታዩት ጠንካራ ጎናች ይበልጥ በማጎልበት የተሳካ የመርሃ ትምህርት ትግበራ ማካሄድ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

Description

Keywords

Citation